ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በሮማኒያ በሚገኘው የሮማ ጎሳ ላይ ስለሚደርሱት ያልተገቡ ሁኔታዎች ይቅርታ ጠየቁ

 ትላንትና እሁድ ማለትም ግንቦት 25 ቀን 2011 ዓ.ም. እ.ኢ.ዘ.ኣ. ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ የ3 ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን በሮማኒያ ከሚገኘው የሮማ ጎሳ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ማጠናቀቃቸውን ታውቋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በባልካን ሀገር ውስጥ በአንዳንድ የአገሪቱ ግዛቶች እና በመላው በዓለም ላይ በአብዛኛው በሚገለሉና አድልዎ በሚደረግባቸው ሰዎች ላይ ስለሚፈጸመው የፍትህ መጓደል በቤተክርስቲያኒቱ ስም ይቅርታ መጠየቃቸው ታውቋል።

ይህም የይቅርታና የማህበራዊ ተሳትፎ ጥሪ ይፋ የሆነው የሮማኒያን ሕዝብ 10 በመቶ ማለትም በአሃዝ ሲሰላ ወደ 20 ሚሊየን የሚጠጋውን ሕዝብ በሚወክለው የሮማ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በተደረገው የሁለትዮሽ ስብሰባ ላይ መሆኑ ታውቋል።

በተለይም በአብዛኛው የሮማ ጎሳዎች በሚኖሩበት በሮማኒያ በብሉይ ከተማ ውስጥ በባርቡ ላውታሩ መንደር ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በታሪክ ዘመናት ሁሉ ቤተክርስቲያን በዚህ ሕዝብ ዙሪያ ስላሳየችው ቸልተኝነትና በሚደርስባቸውም የተለያየ መገለልና መድልዎ የበኩሏን ኃላፊነት በሚገባ ባለመወጣትዋ የተሰማቸውን ቅሬታ ጠቅሰው ለዚህም ይቅርታ ጠይቀዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ, ቤተክርስቲያን የሁሉም ሰው መገናኛና ለሁሉም ሰው የሚሆን ቦታ መኖሩን ካብራሩ በኋላ ይህም እውነታ የክርስቲያናዊ ማንነታችን አካልና መገለጫ እንደሆነ በኣንክሮት ተናግረዋል።

አክለውም ይላሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ, "ልቤ በዚህ ማህበረሰብ ላይ በተጋረጡት የተለያዩ ተግዳሮቶች ማለትም የአድልዎ የመለያየት እና የማጎሳቆል ጫናዎች እጅጉን ዝሏል. " ለዚህም የክርስቶስ በሆነችው ቤተክርስቲያን ሥም ይቅርታችሁን እጠይቃለሁ ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ, ይህ የሚጠቁት ይቅርታ ልክ እንደ ኣቤል ቀና ቀናውን መልካሙንና የተቀደስውን የእግዚኣብሔርን መንገድ በመተው በኣንፃሩ የቃኤልን መንገድ ማለትም ክፉውን መሥመር የአድልዎና የመለያየትን መንፈስ በመከተል ይህ ማኅበረሰብ የሚገባውን ክብርና እውቅና ባለመስጠታችን ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ, "ጭፍን ጥላቻን በማራመድ ቁጣንና ቅሬታን በመቀስቀስ ኣንድን ሕብረተሰብ ወደፊት ማራመድ ኣይቻልም ምክንያቱም በእነዚህ እክሎች ኣማካኝነት እድገቱ ወደፊት እንዳይቀጥል የእድገቱን ጉዞ ስለሚገታው ነው። በመቀጠልም ይላሉ ቅዱስ ኣባታችን ፍራንቼስኮስ, ከሰብአዊ ኣመለካከትና ሰዎችን በስብዕና ሊሰጣቸው ከሚገባው ሰብአዊ ክብር ኣስቀድመን የራሳችንን ፍርድና ጭፍን ጥላቻዎች የምናንፀባርቅ ከሆንን በእርግጥም እኛ ክርስቲያኖች አይደለንም በየትኛውም መሥፈሪያ ጥሩ ሰብዓዊ ፍጡሮችም አይደለንም ብለዋል።

በመቀጠልም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ, በጎ ፈቃድ ያላቸው ወንዶች እና ሴቶች ሁሉ ከጥላቻ ሥልጣኔ ይልቅ የፍቅር ሥልጣኔ እንዲሰፍን ያላሰለስ ጥረት ማድረግ እንደሚገባና ይህንን መሥመር እንዲከተሉ ኣሳስበው ምንም እንኳን ጉዳዩ የሁላችንን ጥረትና መረባረብ ከመጠአቁም በላይ የሰላም ዋና መሠረት ነውና ልንከተለው ይገባል ብለው ይህንንም ሁሉም የክርስቶስ ተከታይ በታማኝነት እንዲተገብሩ ተማጥነዋል።

በመቀጠልም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ, ይህ የሮማ ማኅበረሰብ በዚህ ረገድ ብዙ የሚጫወተው ሚና እንዳለና በዓለም ዙሪያ ያሉትን ሕዝቦቻቸውን በሚወክሉ ስብሰባዎችና የውይይት መድረኮች ምንም ዓይነት ፍራቻ እንዳይኖራቸውና በሚያገኙት ኣጋጣሚና ሁኔታ ባህላቸውንና ታሪካቸውን በሚገባ እንዲያስተዋዉቁ ሓሳባቸውን ሰንዝረዋል።

ከዚሁ ማኅበረሰብ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ተደራሽ ከሆኑት ኣስተያየቶች መካከል የሰው ልጆች ህይወትና የመኖር መብት በተመለከተ የቤተሰብን ዋጋ በተመለከተ, ከኅብረተሰቡ ውስጥ ለአደጋ ለተጋለጡ ሰዎችና ኣረጋውያን ኣስፈላጊው ድጋፍና ትኩረት የሚሉትና ሌሎችም ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች መነሳታቸው ታውቋል።

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በየትኛውም በሚገኙበት ሥፍራ ሁሉ እነዚህን በመካከላቸው ሲያዳብሯቸው የኖሩትን መልካም እሴቶች ክህሎቶችና ስጦታዎች ለሌሎች እንዲያካፍሉና ሌሎች የሚያበረክቱላቸውን መልካም ስጦታዎች ሁሉ በደስታ መቀበል እንዲችሉ ኣሳስበው  ከሁሉ በማስቀደም የሰብአዊነትንና የወንድማማችነትን ዓለም እንዲገነቡ በዚህም ረገድ አብረዋቸው እንዲጓዙ ኣሳስበው ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል።

02 June 2019, 16:42