ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ቅዱስ ቁርባን የኢየሱስን አጠቃላይ ሕልውና ያሳየናል አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው  የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 16/2011 ዓ.ም ያደርጉት አስተንትኖ በእለቱ የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የተከበረውን የክርስቶስ ክቡር ሥጋ እና ክቡር ደም የሚዘከርበተ አመታዊ በዓል ከግምት ባስገባ መልኩ እና ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መመገቡን በሚገልጸው (ሉቃስ 9፡10-17) ላይ በተጠቀሰው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ አስተንትኖ እንደ ነበረ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ቅዱስ ቁርባን የኢየሱስን አጠቃላይ ሕልውና ያሳየናል ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ በጣሊያን እና በአንዳንድ የዓለማችን ክፍሎች ውስጥ የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደሙ አመታዊ በዓል እየተከበረ ይገኛል። በእለቱ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል ደግሞ ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን በገሊላ ባሕር አጠገብ እንደ መገበ ይገልጻል (ሉቃስ 9፡11-17)። ኢየሱስ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመፈወስ እና ለማስተማር ፈልጎ ነበር። ቀኑም ሊመሽ ሲል፣ ዐሥራ ሁለቱ ወደ እርሱ ቀርበው፣ “ያለ ነው በምድረ በዳ ስለ ሆነ፣ ሕዝቡ ወደ አካባቢው መንደርና ገጠር ሄደው ማደሪያና ምግብ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው” አሉት (ሉቃስ 9፡12)። ደቀ-መዛሙርቱም ደክመው ነበር። በእርግጥ እነርሱ አንድ ገለልተኛ በሆነ ቦታ ላይ ነበሩ፣ ሕዝቡ ምግብ ለመግዛት  በአቅራቢያ ወዳሉ መንደሮች በእግራቸው በመሄድ ምግብ መግዛት ነበረባቸው። ኢየሱስ ይህንን ጉዳይ በመገንዘቡ የተነሳ “እናተ ራሳችሁ የሚበላ ነገር ስጡዋቸው” በማለት ይናገራል። እነዚህ ቃላት ደቀ መዛሙርቱን አስደንቆዋቸዋል። ጉዳዩ አለገባቸውም ነበር፣ ምን አላባትም ተናደው ሊሆን ይችላል፣ በእዚህ የተነሳ “ለእነዚህ ሁሉ ሰዎች ምግብ ካልገዛን በስተቀር አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ብቻ አለን” በማለት ይመልሱለታል።

ይልቁንም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ "እያንዳንዱ ሰው በግሉ” ካለው አመክንዮ በመውጣት እውነተኛው የሆነ መንፈሳዊ ለውጥ እንዲያደርጉ ኢየሱስ ጥሪ ያቀርባል። ወዲያውኑ ምን ማድረግ እንዳለበት በግልጽ ያሳያል። ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን፣ “ሕዝቡን በአምሳ በአምሳ ሰው መድባችሁ አስቀምጧቸው” አላቸው። እርሱም አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ እያየ ጸሎት አደረገ ባረካቸው። ከእዚያም እንጀራውን መቆራረስ ጀመረ፣ ዓሳውንም ቆራረሰ ለደቀ-መዛሙርቱ ሰጣቸው ደቀ-መዛሙርቱ ደግሞ ለሕዝቡ አከፋፈሉ። ሁሉም ወስደው በልተው እስኪጠግቡ ድረስ ያ እንጀራ አላለቀም ነበር።

ይህ ተአምር - በጣም አስፈላጊ የሆነ ተአምር ነው፣ ሁሉም ወንጌላውያን እንደ ሚተርኩት -ይህ ተአምር መሲሁ ያለውን ኃይል ያሳያል፣ በተመሳሳይ ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡ ያለውን ርህራሄውን ያሳያል-ኢየሱስ ለሰዎች ርኅራኄ አለው። ይህ ታላቅ የሆነ ተአምር ኢየሱስ በእዚህ ምድር በነበረበት ወቅት የፈጸመው አንደኛው እና የመጨረሻው ተአምር ብቻ ሳይሆን በእርሱ ምድራዊ ሕይወት ማብቂያ ላይ የመሥዋዕቱ መታሰቢያ የሆነውን ቅዱስ ቁርባንን ማለትም የእሱ ሥጋ እና ደም ለአለም ደኅንነት የተሰጠው ቅዱስ መስዋዕት ምን እንደሚሆን አስቀድሞ የገለጸበት ተአምር ነው።

ቅዱስ ቁርባን የኢየሱስን አጠቃላይ ሕልውና ያሳየናል፣ እሱም ለአባቱ እና ለወንድሞቹ ያለውን ፍቅር የገለጸበት የፍቅር ድርጊት ነው። እንደዚሁም ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን በመገበበት ወቅት ኢየሱስ እንጀራውን በእጁ ያዘ፣ ለአባቱ የምስጋና ፀሎት አቀረበ፣ እንጀራውን ቆረሰ፣ ለደቀ-መዛሙርቱ ሰጠ፣ የመጨረሻ እራት ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር በበላበት ወቅት ያደርገው ከእዚህ ጋር በሚመሳሰል መልኩ ነበር። ነገር ግን በዚያ ምሽት እርሱ መከራ ከመቀበሉ በፊት ባለው ምሽት የአዲሱና የዘለአለም ቃል ኪዳን መገለጫ የሆነውን የእርሱ ሞት እና ትንሳኤ መታሰቢያ የሆነውን ምስጢር ትቶልን ሊሄድ ፈለገ። የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን የሚዘከርበትን አመታዊ በዓል በእየ አመቱ በምናከብርበት ወቅት ኢየሱስ የሰጠን ታላቅ የሆነውን ቅዱስ ቁርባን በደስታ እንዘክራለን። ልማዳዊ በሆነ መልኩ ሳይሆን በምስጋና እና በነቃ መንፈስ እንቅበለው። ቅዱስ ቁራባንን ልማዳዊ በሆነ መልኩ እንዲሁ ጥንቃቄ ሳናደርግ መቀበል በፍጹም አይገባንም። በማነኛው ጊዜ የኢየሱስን ቅዱስ ሥጋውን እና ደሙን ለመቀበል ወደ መንበረታቦት በምናቅርብበት ወቅት ሁል “አሜን” በማለት ለኢየሱስ ያለንን ትማኝነት ማደስ ይኖርብናል። በእዚህም መሰረት ካህኑ “ይህ የክርስቶስ ሥጋ ነው” ብሎ በሚሰጠን ወቅት እኛም “አሜን” ብለን መመለስ ይኖርብናል፣ ይህ “አሜን” ከልባችን ውስጥ የመነጨ ሊሆን ግን ይገባዋል። እኔን ያዳነኝ ኢየሱስ ነው፣ እንድኖርም ኃይል እና ጉልበት የሚሰጠኝ ኢየሱስ ራሱ ነው። ኢየሱስ  ሕያው ነው።

የእግዚያብሔር ህዝብ በቅዱስ ቁርባን ላይ ያለውን እምነትን በመግለጽ፣ ለእዚህ ቅዱስ ለሆነው ምስጢር ያለንን አክብሮት በመግለጽ በመላው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሚከበር አመታዊ በዓል ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የኢየሱስን ፍቅር በታማኝነት መከተል እንችል ዘንድ እና ቅዱስ ቁራባንን በሚገባ ማምለክ እንችል ዘንድ እርሷ ትርዳን።

23 June 2019, 18:08