ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በተለያየ ዓይነት ርዕዮተ ዓለም ምክንያት የሚቃጡትን በደሎች ፍቅር ያሸንፋል”

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከግንቦት 23-25/2011 ዓ.ም ድረስ 30ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በሮማኒያ እያደርጉ እንደ ሚገኙ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ቅዱሰንታቸው በግንቦት 25/2011 ዓ.ም በሮማኒያ በነባራቸው  የሐዋሪያዊ ጎዞ ማብቂያ ላይ በሮማኒያ ዋና ከተማ በቡካሬስት መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በመስዋዕተ ቅዳሴው ላይ ለእመነታቸው ሲሉ መስዋዕትነትን የከፈሉ ሰባት የግሪክ-ካቶሊክ ጳጳሳትን የሰማዕትነት ማዕረግ እንደ ተሰጣቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደርጉት ስከት እንደ ገለጹት “በተለያየ ዓይነት ርዕዮተ ዓለም ምክንያት የሚቃጡትን በደሎች ፍቅር ያሸንፋል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኋልን ተከታተሉን።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

መምህር ሆይ: ይህ ሰው ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ወይስ ወላጆቹ? ብለው አሰቡ. "(ዮሐ 9፡ 2). ደቀመዛሙርቱ የወንጌል ዘገባውን ተንተርሰው. ወደ ኢየሱስ ያቀረቡት ጥያቄ. የሰዎችን ልብ. ምን ያህል ዝግና ድብቅ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ. ልክ እንደ ደቀመዛሙርቱ። ሲወለድ ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ተመልክቷል. ይህም ሰው የእየሱስን ትኩረት ስቧል. እንዲሁም እየሱስም ለዓይነ ስውሩ ሙሉ እውቅና ሰጥቶታል።

 ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የሰውየውም ዓይነ ሥውርነት. የኀጢአት ውጤት እንዳልሆነ. ግልፅ ካደረገ በኋላ ምራቁን ከአቧራ ጋር ቀላቅሎ. የሰውየውን አይኖች በማሸት. ከዚያም በሰሊሆም መጠመቂያ ውስጥ እንዲታጠብ ኣዘዘው. እሱም እየሱስ እንደነገረው ካደረገ በኋላ. እይታው ሙሉ በሙሉ ተመለሰለት።

 ከውልደቱ ጀምሮ ዓይነ ስውር ሆኖ የተፈጠረው ሰው ታሪክ ሁለት ነገሮችን ያመላክተናል. የመጀመሪያው ከውልደቱ ጀምሮ ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ታሪክ ሲሆን. በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የእርሱን መፈወስ ተከትለው በዙሪያው ከነበሩ ሰዎች የተነሱት ጥያቄዎችና ክርክሮች ናቸው። የዚህ ሰው መፈወስ እንዳለ ሆኖ የእርሱ መዳን ግን በሌሎች ላይ ክርክር መረበሽና ቁጣ ኣስነስቷል።

ይህ ዕውር ሆኖ የተወለደውና. በኃላም በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተፈወሰው ዓይነ ስውር. በመጀመሪያ በሁኔታው እጅግ በተገረሙት በዙሪያው በተሰበሰቡት ሰዎች ተመረመረ. ከዚያም በፈሪሳውያን በመቀጠልም በገዛ ወላጆቹን ሳይቀር እንዴት ሊከሰት እንደቻለ. ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥያቄዎች ቀረቡለት. የፈወሰውም ሰው ማን እንደሆነ ማንነቱን በግልጽ እንዲያስቀምጥ ተገደደ፣ ይህንን የሚያደርጉት ግን እግዚኣብሔርንና መልካም ሥራውን ለማመስገን ሳይሆን. እግዚአብሔር በሰንበት ቀን ይህንን ኣያደርግም ብለው.  በዚሁም ምክንያት የእግዚአብሔርን ድንቅ ተዓምር ለመካድ ነው. ይባስ ብለውም እንዲያውም የእግዚኣብሔርን ክብር ለመቀነስ. ሰውየው ዓይነ ስውር ሆኖ እንደተወለደ እስከ ጥርጣሬ ድረስ ሄዱ።

የታሪኩን ኣጠቃላይ ገጽታ ስንመለከት. ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ለነገሮች እንዴት ትኩረት እንደሚስጥና. ሰውን ከተራና ዝቅ ካለ ቦታ. አንዴት ከፍ ወዳለ ቦታ እንደሚያሸጋግር ያሳየናል። ይህ ነገር. በተለይ የሰው ልጆች ሁሉ እንዲድኑ ከሚፈልግ ኣምላክ ይልቅ. ሰንበትን ከፈጣሪ በላይ ለሚመልከት ሰው. ይህንን እውነታ ለመረዳት እጅግ በታም ኣስቸጋሪ ነው 1ጢሞ 2፡4።

ይህ ዓይነ ስውር ሰው የሚወክለው. የራሱን ዓይነ ስውርነት ብቻ ሳይሆን. በዙሪያው ያሉትን የዓይነ ስውራን ማለትም. ክርስቶስን እየተመለከቱ ያላወቁትን ሁሉ ይወክላል. በሊላ መልኩ ይህ ምሳሌ. ለኣንድ ሰው መልካም በመደረጉ ምክንያት በሌሎች ሰዎች ልብ ውስጥ ተቃውሞና ጥላቻ ሊጸነሱ እንደሚችሉ ያመላክተናል, ሰዎችን በሚገባቸውን ቦታ ከማስቀመጥና ከመንከባከብ ይልቅ. ለራሳችን ልዩ ትኩረት, ልዩ ቦታና ደረጃ ልዩ ስያሜ, ልዩ የሆነ የራሳችን ፅንሰ-ሓሳብ በመፍጠር. በዙሪያችን ብቻ የራስን ማንነት ለመገንባት እንጥራለን።

የክርስቶስ አቀራረብ ግን ልዩ ነው. እሱ እራሱን ከመመልከትና. ዝናና ክብር በራሱ ዙሪያ ከመገንባት ይልቅ. ሰዎችን ዓይናቸው ውስጥ ይመለከታል. ሥቃያቸውንም ሆነ ታሪካቸውን ይጋራል. እነርሱን ለመገናኘት ወጥቷልና. በችግራቸው ሊደርስላቸው መቷልና. የራሱን ክብርና ዝና ወደጎን በመተው. ትክክለኛና ኣስፈላጊ ለሆነው ነገር ቅድሚያ ይሰጣል።

ምድር በውስጧ በሚኖሩ ሰዎች ኣማካኝነት በሚፈጠሩ የተለያዩ ኣመለካከቶች. ወይንም ኣንድ ገዢ መንግሥት. የሃገሪቱ ብቸኛ ባለቤትና ሕግ ኣርቃቂ. ሕግ ኣስከባሪ ከሆነ. የሰዎችን መብትና ፍላጎት ይጫናል. ስብኣዊ መብታቸውን ሁሉ ይጋፋል. ይህም ሰዎችን ወዳልተፈለገ ግጭትና እልቂት ይመራል። በዚህም ጉዳይ በቅርብ ጊዜ በደስታ ብጽዕናቸውን ያወጅኩት. የሰባቱ የግሪክ ካቶሊክ ጳጳሳት ምሳሌነትና. የሰጡንን ምስክርነት ማንሳቱ ተገቢ ነው።

እነዚህ ብጹኣን ጳጳሳት በታላቅ ድፍረት እና ውስጣዊ ጥንካሬ. ለሚወዱት ቤተክርስትያን. ታማኝነታቸውን ኣስመስክረዋል. ጠንከር ላለ እሥራትና በደል ቢዳረጉም. ሁሉንም በትዕግሥት በማለፍ. የሚጠበቅባቸውን ሁሉ በብቃት ተወጥተዋል። እነዚህ አውነተኛ ሰማዕታት ለሮማኒያን ህዝብ. ውድ የሆነ ውርስን. በሁለት ቀለል ባሉ ቃላት ጠቅለል አድርገው ያወርሳሉ. እነሱም ነጻነትና እና ምህረት ናቸው።

ነጻነትን በተመለከተ. ሁላችንም እዚህ ተገኝተን የምናካሂደው ሥርዓተ-ኣምልኮ የሃይማኖት ነፃነት በመኖሩና በመረጋገጡ ነው። በዚህ ቦታ መገኘታችን ትልቅ ትርጉም ኣለው. ይህ ሥፍራ በተለያዩ የሃማኖት ተከታዮች ቢሞላም ቅሉ. ሁሉም በኣንድነት ሆነው የሕዝቧን ኣንድነት ያንፀባርቃሉ። እነዚህ ሁሉ እንቅስቃሴዎች የሮማኒያን ባህልና ብሔራዊ ማንነትን የሚያበለፅጉ እሴቶች ናቸው።

 አዲሶቹ ብጹኣን ሰማዕታት. የሰውን ልጅ ያስጨንቀውን። መሠረታዊና ሰብአዊ መብቱን የሚጋፋውን ኣላስፈላጊ ሥርዓት ለመቃወም ሲሉ ሕይወታቸውን ሰጥተዋል. በዚያ አሳዛኝ ወቅት. ይህ አምባገነናዊና አምላክ የለሽ ስርዓት. በተለይም በካቶሊክ ኅብረተሰብ ላይ አሰቃቂና የከፋ በትር ኣሳርፏል. ሁሉም የግሪክ እና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳትና. የላቲን-ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አባላት ላይ. ስደት እና እስራት እንዲሁም ተመሳሳይ ግፍ ፈጽሞባቸዋል።

ሁለተኛው የእነዚህ ብጹኣን ጳጳሳት ቅርስ. ምህረት ነው. ለክርስቶስ ታማኝነታቸውን በመግለጽ ያሳዩዋቸውን ጽናት. ለኣሳዳጆቻቸው ጥላቻ ሳያሳዩና. በትልቅ ገርነት ምላሽ በመስጠታቸው. ለመሠቃየትና ክርስቶስን ለመምሰል ዝግጁ መሆናቸውን ያሳያል. በተለይም ኢዩሉዩ ሆሱ የተባሉት ጳጳስ በተሰቀሉበት ወቅት. የተናገሯቸው ቃላት አንደበተ ርቱዕነታቸውንና ለእውነት የቆሙ ሰማዕታት መሆናቸውን የሚያመላክት ነው. እሳቸውም እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል. እግዚአብሔር ይቅርታን ለመስጠትና. ለሁሉም ሰዎች ለውጥ ይመጣ ዘንድ እንድንጸልይ. ወደዚህ የጨለማና ሥቃይ ሥፍራ ልኮናል."

እነዚህ የብጹኣኑ ሰማዕታት ቃላቶችና ማበረታቻዎች. ሕዝቡ በሥቃይ በተፈተነበት ወቅት. እምነቱን በሙሉ ልብ እንዲጠብቅና. ለእምነቱ እንዲቆም ከፍተኛ ማበረታቻ ሆኖታል። ለተጋረጠባቸው ከባድ ፈተና ያሳዩት ምህረት. ዛሬ ሁላችንም ቁጣንና ጥላቻን. በፍቅርና በይቅርታ እንድናሸንፍ. ብሎም ክርስቲያናዊውን እምነታችንን. በሙሉነትና በድፍረት እንድንኖር የሚጋብዘን. ትንቢታዊ መልዕክት ነው።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ. ዛሬም ቢሆን ህዝቦችን ከባህላዊና ሃይማኖታዊ ኣመለካከታቸው ለማስወጣትና. አዲስ የሆኑ ያልተገቡ ሀሳቦችን እንዲይዙ የሚያደርጉ ሙከራዎችን እንመለከታለን. በተለይም ህይወትን ሰብኣዊነትን, ጋብቻንና ቤተሰብን በተመለከተ(Amoris Laetitia, 40) ልብ ሊባል ይገባል።  ከሁሉ በላይ ደግሞ የቀድሞዉን መልካምነት መተው. ኣዳጊውንና ወጣቱን ትውልድ ይጎዳል. ሊደርሱበት ከሚችሉት መልካም ጎዳና ውጭ ያደርጋቸዋል. ሥር መሠረትም ያሳጣቸዋል (cf. Christus Vivit, 78)።

ሁሉም ነገር በተገቢው ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውል ካልሆነ. የማይጠቅም ነገር ሆኖ ይቀራል. ኣንዳንዶች ሌሎችን ይጠቀማሉ. በእነርሱም ላይ ጥቅማቸውን ይጫናሉ. ሌሎችንም የእነርሱ መጠቀሚያ ኣድርገው ይቆጥሯቸዋል (Laudato Si’ ላውዳቶ ሲ, 123-124). እነዚህ ነገሮች ደግሞ. የኣንድን ሃገር ሰላም በማደፍረስ. ፍርሃትና መለያየትን ይዘራሉ. ሃገሪቱ ለረጅም ዓመታት ያፈራችውን መልካም እሴቶችን ሁሉ ያጠፋሉ. ለምሳሌ ያህል, በ 1568 የወጣው የቶርዳው መምሪያ ሕግ. ሁሉንም ዓይነት ቀኖናዊነት ከልክ ያለፈ እንዳይሆን ከመከልከሉም  በላይ. በአውሮፓ ውስጥ ሃይማኖታዊ መቻቻልን ለመግለጽ። የመጀመሪያው እንደሆነ ይጠቀሳል።

የወንጌልን ብርሀን በዘመናችን ለማንፀባረቅና. አሁን የሚነሱትን ኣዳዲስ አዝማሚያዎች ለመቋቋም. በፊት እንደጠቀስናቸው. እንደ ብጹኣን ጳጳሳቱ. ጠንካሮችና ልበ ሙሉዎች ሆናችሁ መቀጠል እንድትችሉ ላበረታታችሁ እወዳለሁ። የነፃነትና የምህረት ምስክር ትሆኑ ዘንድ. በወንድማማችነትና በመወያየት ችግሮችን ሁሉ ትፈቱ ዘንድ.  በመከራ ጊዜ ውስጥ የተከሰተውን የወንድማማችነት መንፈስ በማጎልበት. ክርስትያኖች ሁሉ እርስ በርስ ይበልጥ እንዲቀራረቡና. ልዩነታቸውን ኣጥብበው ወደ አንድነት ጉዞ አንዲያደርጉ ኣሳስባለው።

ለዚህም በጉዟችሁ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እናታዊ እርዳታና የኣዲሶቹ ብጹኣን ጳጳሳቱ ኣማላጅነት በጉዞኣችሁ ሁሉ ይርዳችሁ።

02 June 2019, 09:23