ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ  

በቡርኪና ፋሶ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተቃጣውን ጥቃት ቅዱስነታቸው አወገዙ።

በግንቦት 04/2011 ዓ.ም እለተ ሰንበት ላይ በቡርኪና ፋሶ መስዋዕተ ቅዳሴ በማካሄድ ላይ በነበረው በአንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ በአሸባሪዎች በተቃጣው ጥቃት በምዕመናን እና በእለቱ መስዋዕተ ቅዳሴ በማስረግ ላይ በሚግኙት ካህን ላይ በደረሰው ከፍተኛ አደጋ ማዘናቸውን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንቸስኮስ ከ40 ሚልዮን በላይ ተከታዮች ባሉት እና @pontifex በመባል በሚታወቀው የቲውተር ገጻቸው በላኩት መልእክት ይፍ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በቡርካና ፋሶ የሚገኙ አካራሪ የእስልምና ተከታዮች ይህንን በምንም ዓይነት መስፈር ተቀባይነት የሌለውን ጥቃት በመፈጸም ምዕመኑ እግዚኣብሔርን ለማመስገን በሚሰበሰብበት እለተ ሰንበ ሽብር ለመንዛት እና የንጹሐንን ደም ለማፍሰስ እለቱን መጠቀማቸው የሚያሳዝን ተግባር መሆኑን በመልእክታቸው ገልጸዋል። በእለቱ በተፈጸመው ጥቃት መስዋዕተ ቅዳሴ በማሳረግ ላይ የነበሩ አንድ ካህንን ጨምሮ ሌሎች አምስት ምዕመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን አሸባሪዎቹ ይህንን ጥቃት ካደረሱ በኋላ ቤተ ክርስትያኑን በእሳት ማጋየታቸውም ከስፍራው ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በቡርኪና ፋሶ በአንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ በአሸባሪዎች የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቲውተር ገጻቸው ላይ ያስተላለፉትን የሐዘን መግለጫ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የቅዱስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ጽህፈት ቤት ምክትል ዳሬክተር የሆኑት አቶ አሌክሳንድሮ ጂዞቲ እንደ ገለጹት “በዚህ በአሸባሪዎች የተቃጣውን ጥቃት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ በሰሙበት ወቅት እጅግ ማዘናቸውን፣ የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑት ሰዎች እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በአገሪቷ ለሚገኙ የክርስቲያን ማኅበርሰቦች ጸሎት  እንደ ሚያደርጉ ቅዱስነታቸው መግለጻቸውን” አውስተዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
12 May 2019, 16:13