ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “እኔ ወደ እናንተ የምመጣው ከእናንተ ጋር በመንፈሳዊነት አብሮ ለመጓዝ ነው”

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከግንቦት 23-25/2011 ዓ.ም ድረስ 30ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ሮማኒያ እንደ ሚያቀኑ ተገልጹዋል። ቅዱስነታቸው እንደ ተለመደው ማነኛውንም ሐዋርያዊ ጉብኝት ከመጀመራቸው በፊት ሐዋርያዊ ጉብኝት ወደ ሚያደርጉባቸው አገራት ከማቅናታቸው በፊት በቪዲዮ መልእክት እንደ ሚያስተላልፉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው ወደ ሮማኒያ ለሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት “እኔ ወደ እናንተ የምመጣው ከእናንተ ጋር በመንፈሳዊነት አብሮ ለመጓዝ ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከግንቦት 23-25/2011 ዓ.ም ድረስ በሮማኒያ የሚያደርጉትን 30ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት አስመልክተው በቪዲዮ ያስተላለፉትን መልእክት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

በሮማኒያ የምትገኙ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ!

ወደ እናንተ መጥቼ በመካከላችሁ ለመገኘት ጥቂት ቀናት ይቀሩኛል። ይህንን ሳስብ እጅግ በጣም ደስ እያለኝ ከወዲሁ ለሁላችሁም ሰላምታዬን አቀርባለሁኝ።

ውብ እና እንግዳ ተቀባይ ወደ ሆነችው ወደ ሮማኒያ የምመጣው እንደ ወንድማችሁ እና እንደ መንፈሳዊ ነጋዲ በመሆን ሲሆን ይህንን ጉብኝት እንዳደርግ የጋበዙኝን እና ጉብኝቱን ያስተባበሩትን የአገሪቷን ርዕሰ ብሔር እና ባለስልጣናት ጭምር ለማመስገን እወዳለሁ። በሮማኒያ በማደርገው ጉብኝት በአግሪቷ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክን እና እንዲሁም ቋሚ የሲኖዶስ አባላትን፣ እንዲሁም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቄሳውስትን እና ምዕመናን ለመገናኘት መምጣጤን ሳስብ ከአሁኑ ደስታ ይሰማኛል። እኛን የሚያገናኝ  የእምነት መሰትጋብር ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የነበረ ሲሆን በተለይም በቱፊት እንደ ሚነገረው በአገራችሁ የክርስትናን እምነት ያስተዋወቁ ጴጥሮስና እንድርያስ ለየት ባለ መልኩ ትስስራችንን ያጠናክሩታል። እነዚህ የደም ትስስር ያላቸው ወንድማማቾች ይህንን ምስክርነት እውን ያደርጉት ደማቸውን ለጌታ በማፍሰስ ጭምር ነው። በእናንተ መካከል በጣም ብዙ የሚባሉ ሰማዕታት እንደ ነበሩ የሚታወቅ ሲሆን በቅርብ ጊዜ እንኳን የሰማዕትነት ማዕረግ በደስታ የምሰጣቸውን ሰባት የግሪክ-ካቶሊክ ጳጳሳትን ጨምሮ በጣም ብዙ ሰማዕታት ከመካከላችሁ ተገኝተዋል። ሕይወታቸውን አሳልፎ እስከ መስጠት ድረስ የደረሰባቸው ከፍተኛ ስቃይ ሊረሳ የማይችል ውድ የሆነ ውርስ ነው። እናም ይህ ሕይወት ከእኛ ጋር ከሚጋራው ወንድማችን ራሳችን እንዳናርቅ የሚያመለክት የጋራ ቅርስ ነው። ወደ እናንተ የምመጣው በጋራ ለመጓዝ ነው። እኛ ከሥር መሰረታችን የወረስነውን ትምህርት በማስታወስ ሥር መሰረታችንን እና ቤተሰቦቻችንን መንከባከብ በመማር፣ በአከባቢያችን የሚኖሩትን ሕጻናትን እና ወንድሞቻችንን መንከባከብ በመማር፣ ከጥርጣሬ እና ከፍርሃት ባሻገር በመሄድ፣ ከሌሎች ጋር እንዳንቀራረብ የሚያደርጉንን መሰናክሎች በማስወገድ በጋራ ወደ ፊት አብረን ልንጓዝ ይገባል። ብዙዎቻችሁ የእኔ ሐዋርያዊ ጉብኝት የተሳከ ይሆን ዘንድ በትጋት እየሰራችሁ መሆናችሁን አውቃለሁ ለዚህም ከልብ አመሰግናለሁ። ሁላችሁን በጸሎቴ እንደ ማስታውሳችሁ እያረጋገጥኩኝ ሐዋርያዊ ቡራኬዬ በእያላችሁበት ይደረሳችሁ። እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ! በሰላም ቆዩኝ።

28 May 2019, 15:45