ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ጳጳሳት ለካህናቶቻቸው እና ለእግዚኣብሔር ሕዝብ ቅርብ ሊሆኑ ይገባል” አሉ

በግንቦት 13/2011 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከጣሊያን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባሄ አባላት ጋር መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ለብጹዐን ጳጳሳት ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት “ጳጳሳት ለካህናቶቻቸው እና ለእግዚኣብሔር ሕዝብ ቅርብ ሊሆኑ ይገባል” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው አድርገውት የነበረው ንግግር መሰረቱን የጋራ መንፈሳዊ አስተዳረ እና ኅበረት በሚሉት ሁለት ጭብጦች ዙሪያ ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ በተለይም ለቫቲካን ዜና ከደረሰው ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተጨመሪም ምስጢረ ተክሊልን እና በብጹዐን ጳጳሳት እና በካህናት መካከል ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት በተመለከተ አንስተው መወያየታቸው ተገልጾዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

73ኛው የጣሊያን ብጹዐን ጳጳሳት አጠቅላይ ጉባሄ “ሚስዮናዊነትን የሚያቀላጥፉ አዲስ መንገዶች እና መሳሪያዎች” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ እንደ ሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ይህ አጠቅላይ ጉባሄ ዛሬ ግንቦት 15/2011 ዓ.ም የተለያዩ ውሳኔዎች ካሰተላለፈ በኋላ እንደ ሚጠናቀቅ ተገልጹዋል።

“ይህ ጉባሄ በጣሊያን በአዲስ መልክ መካሄድ ስለሚገባው ሐዋርያዊ ተግባር እና የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ላይ በማስተማር ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ለማድረግ የሚረዳ ወሳኝ ጊዜ ነው” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ብጽዐን ጳጳሳት በአኑ ወቅት በተለያዩ አቅጣጫዎች፣ ሁኔታዎች እና ተግዳሮቶች ውስጥ በማለፍ እያበረክቱ የሚገኙትን ሐዋርያዊ ተግባር ቅዱስነታቸው ያደነቁ ሲሆን በተለይም አሁን በጣም መሰረታዊ የሚባሉ ጥያቄዎች በሚነሳበት በአሁኑ ወቅት በጣሊያን ያለውን ቤተክርስቲያን ወደ ፊት ለማሻገር የምታደርጉትን ጥረት ከምዕመናን እና ከካህናቶቻችሁ ጋር በመሆን በርትታችህሁ እንድትቀጥሉ አደራ እላለሁ ብለዋል።

ኅብረት እና አንድነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደርጉት ንግግር እርሳቸው የካቶሊክ ቤተክርስትያን 266ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኋላ የካቶሊክ ቤተክርስትያንን መዋቅር ውስጥ የሚታዩትን አንዳንድ ብልሹ የሆኑ አስራሮችን ለማስተካከል አንዳንድ የማሻሻያ ሥራዎችን በማከናውን ላይ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን የማሻሻያ እቅዳቸውን እውን ለማደረግ በማሰብ በተደጋጋሚ ኅበረት እና አንድነት የሚሉትን ቃላት በመሰረታዊነት እንደ ሚጠቀሙ የሚታወስ ሲሆን አሁን በዚሁ የጣሊያን ብጹዐን ጳጳሳት 73ኛው አጠቃላይ ጉባሄ ላይ ተገኝተው ያደርጉት ንግግር ኅበረት ማለትም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያየ የሥራ እርከን ላይ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት (ብጹዐን ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ደናግላን፣ ዲያቆናት እና ምዕመናን ወዘተ) ተቀናጅተው እና ተናበው በጋራ የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ ማስቀጥል ይኖርባቸዋል በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ ባደርጉት ንግግር ይህ ደግሞ “የጣሊያን የካቶሊክ ቤተክርስትያን የጤና ሁኔታ መግለጫ ካርድ ነው” ብለዋው የቤተክርስትያኗን ሐዋርያዊ እና መዋቅራዊ ተግባር ጤናማ መሆን አለመሆኑ የሚለካበት መስፈርት ነው ብለዋል።

አንድነት የሚለውን ሁለተኛውን ጭብጥ ቅዱስነታቸው በዳሰሱበት ወቅት እንደ ገለጹት በዚህ ረገድ የጣሊያን ብጹዐን ጳጳሳት እርስ በእርሳቸው እና ከዚያም ባሻገር ከእርሳቸው ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በጋራ የእያንዳንዱ አገረ ስብከት ጳጳሳት ራሱን ችሉ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ስልጣኑ እንዳለ ሆነ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ በጋራ ጉዳዮች ላይ በመመካከር መሥራት እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው አብክረው የገለጹ ሲሆን ከታች ወደ ላይ ማለትም በሀገረ ስብከት ደረጃ ከሚገኙ ቁምስናዎች ከቁምስናዎች፣ ምዕመናን ከምዕመናን፣ ሀገረ ስብከቶች ከሀገረ ስብከቶች፣ ሀገረ ስብከቶች ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያልቸው መስተሳሰር እና መስተጋብር ተጠናክሮ መቀጠል እንደ ሚገባው የገለጹ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከሀገረ ስብከቶች እና ከቁምስናዎች ጋር በተዋረድ ያላቸውን ግኙነት ማጠናክር እንደ ሚገባ ገልጸው ይህ ከላይ ወደ ታች ከታች ወደ ላይ የሚፈጠረው መስተጋብር በሐሳብ ላይ ሳይሆን በተግባር ላይ መስረቱን ያደርገ ግንኙነት እንዲኖረን ያስችለናል ብለዋል።

በጳጳሳትና በካህናት መካከል ሊኖር ሰለሚገባው ግንኙነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ሚስዮናዊነትን የሚያቀላጥፉ አዲስ መንገዶች እና መሳሪያዎች” በሚል መሪቃል በመካሄድ ላይ ባለው 73ኛው የጣሊያን ብጹዐን ጳጳሳት አጠቅላይ ጉባሄ ላይ ያደርጉት ንግግር ሦስተኛው ጭብጥ አሳብ የነበረው ብጹዕን ጳጳሳት ከካህናቶቻቸው ጋር ሊኖራቸው ሰለሚገባው ግንኙነት አንስተው እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “ያለ አድልዎ እና ያለ ምርጫዎች” ካህናቶቻቸውን መቅረብ ይኖርባችኋል ያሉት ቅዱስነታቸው አንዳንድ ጳጳሳት ከካህናቶቻቸው ጋር መልካም የሆነ ግንኙነት ለመመሥረት እንደ ሚከብዳቸው የገለጹ ሲሆን የዚህ ዓይነት ባሕሪይ ያለው ጳጳስ የካህናቱን ሕይወት አደጋ ላይ ስለሚጥል ጥንቃቄ ማደርግ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

21 May 2019, 15:32