ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ዮሴፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቴድራል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ዮሴፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቴድራል  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ማርያምን መገናኘት ደስታን በውስጣችን ይፈጥራል” አሉ!

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ማርያምን መገናኘት ደስታን በውስጣችን ይፈጥራል” አሉ!

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከግንቦት 23-25/2011 ዓ.ም ድረስ 30ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በሮማኒያ እያደርጉ እንደ ሚገኙ መዘግባችን የሚታወስ ሲሆን ቅዱሰንታቸው በግንቦት 23/2011 ዓ.ም በሮማኒያ በነባራቸው የመጀመሪያ ቀን ቆይታ በአገሪቷ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ተገኝተው በእዚያው ለተገኙ የአገሪቷ ርዕሰ ብሔርን ጨምሮ የአገሪቷ ባለስልጣናት፣ የሲቪክ ማኅበረሰብ አባላት እና የተለያዩ አገራትን ልዑካን በተገኙበት ቅዱስነታቸው ንግግር ማድረጋቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ከእዚያም በመቀጠል በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ 10፡15 ላይ በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ መኖሪያ ሕንጻ በማቅናት በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ የሆኑት ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል ደማቅ አቀባበል ተድርጎላቸው እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእዚያው ለተገኙ በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል እና በአገሪቷ የምትገኘው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ቋሚ አባላት ንግግር ማድረጋቸው መዘገባችን ያታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ከእዚያን በመቀጠል አዲስ በተገነባው በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካቴድራል አቅንተው በእዚያው በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል እና በአገሪቷ የምትገኘው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ቋሚ አባላት ጋር “አባታችን ሆይ!” የሚለውን ጸሎት መድገማቸው እና በእዚሁ ጸሎት ዙሪያ ቅዱስነታቸው አስተንትኖ ማደርጋቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ከእዚያ በመቀጠል ደግሞ አመሻሹ ላይ በሮማኒያ በሚገኘው የቅዱስ ዮሴፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቴድራል ውስጥ ተገኝተው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ኤልሳቤጥን ልትጎበኝ የኤደችበት እለት ዓመታዊ በዓል በማሰብ መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸውን ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደረጉትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አቅርበነዋል ተከታተሉን

በክርስቶስ የተውደዳችሁ ወንድሞቼና አህቶቼ ዛሬ የሰማነው ወንጌል በሁለት ቅድስት ሴቶች መካከል ስለነበረው የደስታና የዉዳሴ እንዲሁም የመከባበርና ኣንዱ ለኣንዱ የነበራቸው የተቀደሰ ሰላምታ ማለትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚኣብሔር ድንቅ ነገር በእርሷ ውስጥ በማድረጉ በዚህም መክንያት በውስጧ የተሰማትን ደስታና ቅድስት ኤልሳቤጥ ደግሞ በዚህ በተቀደሰ ሰላምታ ምክንያት በማህጸኗ ያለው ሕፃን በደስታ መዝለሉን ይነግረናል።

ይህ ደግሞ ዛሬ እኛም የዚህ ደስታ ተካፋዮች እንድንሆን በተለይም በ 3 ነገሮች ማለትም በማርያም ጉዞ በማርያም የተቀደሰ ጉብኝትና በማርያም ደስታ ውስጥ ተሳታፊ እንድንሆንና ይህንንም ሁል ጊዜ በውስጣችን ይዘን በማስተንተን ይዘነው እንድንጓዝ ያስተምረናል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጉዞ ስንል በመጽሓፍ ቅዱስ ሰፍሮ እንደምናገኘው ሕፃኑ እየሱስን ከመውለዷ በፊት ከገሊላ እስከ ቤተልሔም የሕፃኑ እየሱስን ሕይወት ከጨካኙ ሄሮድስ እጅ ለማትረፍ ከቤተልሔም እስከ ግብፅ እንዲሁም በሉቃስ ወንጌል 2፡31 ላይ እንደተገለጸው በየዓመቱ የኣይሁድ ፋሲካን ለማክበር ሕፃኑ እየሱስን ይዛ ወደ እየሩሳሌም በስተመጨረሻም ከፍርድ ኣንስቶ እስከ ጎልጎታ ድረስ ያደርገችውን ጉዞ ያስታውሰናል። ኣንድ ልብ ልንለው የሚገባ ነገር ኣለ ይኸውም በእነዚህ ሁሉ ጉዞዎች ውስጥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መንፈሳዊ ጥንካሬና ትዕግሥት ብርታት ሆነዋት ኣብረዋት ይጓዙ ነበር።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ኣቀበት መውጣትም ሆነ ቁልቁለት መውረድ በችግር ውስጥ በተስፋ መጓዝና   በጭንቀት ውስጥ ትዕግሥት ማድረግን እሳምራ ታውቃለች። ስለዚህ እኛም  በችግር ውስጥ በተስፋ መጓዝና በጭንቀት ውስጥ ትዕግሥት ማድረግን እንድንችል እጃችንን ይዛ ትመራናለች። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅር በየዕለቱ በሚገጥመን ትናንሽ የሕይወት ገጠመኞች ውስጥ እንደሚያድግ ኣሳምራ ታውቃለች ይህም እኛም ዛሬ በሴቶች እህቶቻችንና እናቶቻችን ኣያቶቻችንም ጭምር ላይ ያለንን ኣዎንታዊ ኣመልካከት በማሳደግ በሚገጥሙን ፈተናዎች ሁሉ ይህንን ፍቅር መፈልግና ማሳደግ ብሎም ፍሬ ማፍራት ያስፈልገናል።

በሉቃስ ወንጌል 1፡39-56 ላይ የምናገኝው ቅዱስ ታሪክ የማርያም ከቅድስት ኤልሳቤጥ ጋር መገናኝት ማለትም ታናሺቷ ታላቂቱን ለመጠየቅ መሄዷን በዚህም ምክንያት ደግሞ ታላቂቱ በመንፈስ ተሞልታ በማሕጸንዋ ያለው ሕፃን በደስታ መዝለሉንና ሰለ ታናሺቱም የጌታዬ እናት ብላ መመሥከሯንና የዓለም ኣዳኝ ይሆናል ብላ መተንበዩኣን ታናሺቱም በእግዚኣብሔር መንፈስ ተሞልታ በደስታ መዘመሯን ተመልክተን እኛም በዚእ መንፈስ ተሞልተን እግዚኣብሔር ታላቅ ነገር ኣድርጓል ብለን በደስታ  እንድንመሰክር ይህንንም ምሥክርነት በሕይወታችን እንድንተገብር ይጋብዘናል።

ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደ እናት ሆና ሁሉንም የተከዙትን ያዘኑትን ተስፋ የቆረጡትን ሁሉ በእቅፎችዋ እንደምተሰበስብ ለተከዙት እፎይታን ላዘኑት መፅናናትን ተስፋ ለቆረጡት ብሩህ ተስፋ የሚሰንቁበትን መንገድ እንደምታመቻች ሁሉ እኛም የእርሷን ኣብነት በመከተል ይህንን መልካም ተግባር ልንፈጽመው ይገባል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት ያደረገችው ጉዞ እግዚኣብሔር በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ውስጥ እንደምናገኘውና ይህም የደስታችን ምክንያት እንደሚሆን ያስተምረናል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅድስት ኤልሳቤጥ እንዲሁም ቅድስት ኤልሳቤጥ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጉብኝት ደስታቸው ሙሉ እንድሆነ እኛም በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ውስጥ የምናገኘው እግዚኣብሔር የደስታችን ምንጭ ይሆንልናል እኛም የተቀበልነውን ደስታ ለሌሎች በማስተላለፍ ልክ እንደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅድስት ኤልሳቤጥ የደስታና የፍቅር ድልድዮች እንሆናለን።

ደስታን ያጣች ነፍስ ሁልጊዜ የደካማ ባህሪና የጭንቀት ተገዥ ናት። የኣንድ ክርስቲያን ደስታ ሁሌም በእግዚኣብሔር መንፈስ ውስጥ መጓዝ ነው ይህንንም እውነታ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና በቅድስት ኤልሳቤጥ ሕይወት ውስጥ በግልጽ ኣይተነዋል ለዚህም ደግሞ እምነት በክርስትና ሕይወታችን ውስጥ ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል እምነት ከሌለ ጥርጣሬ በላያችን ላይ ዘሩን ይዘራል ተስፋ መቁረጥን ያብብና ኃጢኣትና ሞትን እንድናጭድ ያደርገናል የእግዚኣብሔር ፍቅር ግን ደስታና ሃሴትን ተስፋና እርካታን እንድንሰንቅ ያደርገናል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ኤልሳቤጥን ያደረገችው ጉዞ ለእርሷና ለቅድስት ኤልሳቤጥ እንዲሁም ለሰው ልጆች ሁሉ የደስታና የፍቅር የብሩህ ተስፋ የምሥራች እንደሆነ ሁሉ ይላሉ ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ እኛም ይህንን የደስታ የፍቅርና የብሩህ ተስፋ የምሥራች ወደ እዚህ ምድር ይዘን ስንመጣ ደስተኛ መሆናቸውንና የሩማንያም ሕዝብ ይህንን ጸጋ በመቀበል የግዴለሽነት እና የመከፋፈልን መንፈስ በማስወገድ ይህ ምድር የጌታን ደስታና ምህረት እንዲዘምርና እንዲያመሰግን ይሁን ብለው ስብከታቸውን ቋጭተዋል።

31 May 2019, 12:24