ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 27/2011 ዓ.ም በቡላጋሪያ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 27/2011 ዓ.ም በቡላጋሪያ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ክርስቶስ ሕያው ነው፣ እኛም ሕያዋን እንድንሆን ይፈልጋል” አሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቡልጋሪያን እና ሰሜን መቀዶኒያን ከሚያዝያ 27-29/2011 ዓ.ም ድረስ በቅደም ተከተል የሚያደርጉትን 29ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመጀመር በሚያዝያ 27/2011 ዓ.ም የዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የመጀመርያ መዳረሻ ወደ ሆነችው ወደ ቡልጋሪያ ማቅናታቸውን ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወሳል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው በሚያዝያ 27/2011 ዓ.ም በቡላጋሪያ ዋና ከተማ በሶፊያ በሚገኘው በቅዱስ አሌክሳንደር ኔቫስኪ አደባባይ ላይ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውና በተለይም ክርስቶስ ከሙታን ከተነሳበት የትንሳኤ በዓል ጀምሮ እስከ በዓለ ሃምሳ ድረስ የሚደገመውን “የሰማይ ንግስት ሆይ ደስ ይበልሽ”  የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ እንደ ተለመደው በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ባደርጉት አስተንትኖ እንደ ገለጹት “­­­ለእናንተ ሁላችሁ ለመናገር የምፈልገው የመጀመሪያው ቃል ይህ ነው፡ “ክርስቶስ ሕያው ነው፣ እኛም ሕያዋን እንድንሆን ይፈልጋል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሚያዝያ 27/2011 ዓ.ም በቡላጋሪያ ዋና ከተማ በሶፊያ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው ያደርጉትን አስተንትኖ ውሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተናዋል ተከታተሉን።

ተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ !

ክርስቶስ ከሙታን ተነስቱዋል!

የኦርቶዶክስ እና የካቶሊክ አብታየ ክርስቲያናት ምዕመናን - እዚህ ቡልጋሪያ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ በፋሲካ በዓል ወቅት ክርስቶስ ከሙታን ተነስቱዋል! በመባባል ሰላምታ ይለዋወጣሉ እኔም እነዚህን ቃላት ተጠቅሜ ሰላምታዬን አቀርባለህ።

እነዚህ ቃላት ኢየሱስ ክርስቶስ በክፋትና በሞት ላይ የተጎናጸፈውን ድል በማሳየት እጅግ ደስ የሚል ደስታን ይፈጥራሉ። እነሱ የእምነታችን ዋነኛው ማረጋገጫ እና ምስክር ናቸው፣ ክርስቶስ ሕያው ነው! እርሱ ተስፋችን ነው፣ በአስደናቂ መንገድ ወጣቶችን ወደ ዓለማችን ያመጣል። እርሱ የሚነካቸው ነገሮች ሁሉ ወጣት፣ አዲስ፣ ሙሉ ህይወት ያለው ይሆናሉ። ለእናንተ ሁላችሁ ለመናገር የምፈልገው የመጀመሪያው ቃል ይህ ነው፡ ክርስቶስ ሕያው ነው፣ እኛም ሕያዋን እንድንሆን ይፈልጋል። እርሱ በእናንተ ውስጥ ነው፣ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፣ እርሱ እናንተን በፍጹም ብቻችሁን አይተዋችሁም። እሱ ከእናንተ ጋር ይራመዳል። ሆኖም ግን ምንም ያህል ብትቅበዘበዙም እንኳን ከሙታን የተነሳው እርሱ ሁሌም ከእናንተ ጋር ነው። እርሱ ያለማቋረጥ ይጠራሃል ወደ እርሱ እንድትመለስ እና እንደገና ጉዞህን በአዲስ መልክ እንድትጀምር ይጠብቅኃል። እንደገና በአዲስ መልክ ለመጀመር ፈጽሞ አይፈራም፣ እንደ ገና በአዲስ መልክ ለመጀመር፣ እንደገና ለመነሳት እና እንደገና በአዲስ መልክ ለመጀመር እንችል ዘንድ እጁን ይዘረጋልናል። በሐዘን የተነሳ የእርጅና ስሜት እየተሰማህ ከሆነ--አዎን ሐዘን ያስረጀናል--ቅሬታ ወይም ፍርሀት፣ ጥርጣሬ ወይም ውድቀት ውስጥ በምንገባበት ወቅት ጥንካሬያችንን እና ተስፋዎቻችንን ለመመለስ ሁል ጊዜ እርሱ እዚያ ይኖራል። እርሱ ሕያው ነው፣ አንተም ሕያው እንድትሆን ይፈልጋል፣ ስለዚህም እርሱ ከአንተ ጋር ይራመዳል።

ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ለመስጠት በተጠሩ እና የራስ ወዳድነትን መንፈስን በማስወገድ ቅዱስ ወንጌልን ለማሰራጨት ለተጉ ለበርካታ ለጋሽ ለሆኑት አማኝ ሚስዮናዊያን ጥረት ምስጋና ይግባውና የክርስቶስ ከሙታን መነሳት በመላው ዓለም ውስጥ ለሁለት ሺ አመታት ያህል ተስብኩዋል። በቤተ ክርስቲያ ታሪክ ውስጥ እዚህም በዚሁ በቡልጋሪያ ውስጥ ጨምሮ ማለት ነው ሕይወታቸውን ለቅድስና ያስገዙ ብዙ ግሩም የሆኑ እረኞች እንደ ነበሩ ይታወቃል። ከእነዚህም መካከል እ.አ.አ ከ1925-1934 ዓ.ም ድረስ በዚህ አገራችሁ ውስጥ የኖሩት እና በዚህ አገራ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ክብር ተሰጥቱዋቸው የነበሩት “የቡልጋሪያ ቅዱስ" በማለት የምትጠሩዋቸው ከዚህ ቀደም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ቅዱስ ዮሐንስ 23ኛ ም ይገኙበታል። እዚህ በነበሩበት ወቅት የምስራቃውያን ቤተ ክርስትያንን ወጎች ማክበርን ተምረው የነበረ ሲሆን በዚህም የተነሳ ከሌሎች ሐይማኖቶች ጋር የጠበቀ በጓደኝነት መንፈስ የተሞላ ግንኙነት ፈጥረው ነበር። በቡልጋሪያ የነበራቸው የዲፕሎማሲ እና ሐዋርያዊ ልምድ በእርሳቸው ልብ ውስጥ ጥልቅ የሆነ የእረኝነት ስሜት እና ትስስር ጥሎ ያለፈ ሲሆን በቤተክርስቲያኗ ውስጥ አንድነትን የሚያጠናክሩ ውይይቶች እንዲደረጉ እና እንዲስፋፉ አደረገ፣ ይህም በሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ውስጥ ለየት ባለ ሁኔታ የሚታይ እና ጉልህ በሆነ መልኩ እርሳቸውም ተሳተፊ በመሆን ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ውይይት ይደረግ ዘንድ በሩን ከፈተ። በተወሰነ መልኩ ይህንን በጥበበኞች የተሞላ ምድራችሁን “መልካሙ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመባል የሚታወቁትን ዮሐንስ 23ኛን” በመንፈስ ስላነሳሳቸው ምስጋናችንን እናቀርባለን።

በዚህ የሐይማኖት ኅበረት ለመፍጠር በሚደረገው ጉዞ ላይ ቀጥቂት ጊዜ በኋላ የቡልጋሪያ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ተወካዮችን ተገናኝቼ ሰላምታ መለዋወጤ ደስታን ይፈጥርልኛል፣ ይህ አገራችሁ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆነ በመሆኑ የተነሳ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ተቋማት እርስ በርስ ተገናኝተው የሚወያዩባት መስቀለኛ የሆነች መንገድ ናት። በእዚህ የተለያዩ ማኅበረሰቦች ተወካዮች ግንኙነቶች ውስጥ እንኳን ደስ በሚል መልኩ “የመግባባት ባሕልን ለመገንባት ያለውን ፍላጎት፣ እርስ በእርስ የመተባበር ባሕል እና ደንብ ለማጎልበት ያለው ተነሳሽነት፣ በመሰረታዊ ደረጃ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያላችሁን ፍላጎት” ሊደነቅ ይገባል።

እኛ አሁን የምንገኘው ሥፍራ ከቅዱስ አሌክሰንደር ኔቪስኪ አጠገብ በሚገኘው ቤተክርስቲያን አቅራቢያ በሚገኘው ጥንታዊ በሆነው በቅዱስ ሶፊያ ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ሲሆን በዚያ በሚገኘው ለስላቭ ሕዝቦችን ቅዱስ ወንጌልን በቀዳሚነት ባበሰሩት ቅዱሳን ቀሬሊዮስን እና  መቶድየስ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ጸሎት አቅርበናል። ለዚህ በቡልጋሪያ ለምትገኘው የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ያለኝን ክብር እና ፍቅር ለመግለጽ ወንድሜ የሆኑትን ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ኔዎፊት እና ቅዱስ ሲኖዶሱን ተገናኝቼ ሰላምታዬን ማቅረቤ በጣም አስደስቶኛል።

አሁን ደግሞ የሰማይ እና የምድር ንግሥት ወደ ሆነችው ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመመለስ ከሙታን የተነሳው እና ሕያው የሆነው ጌታ ለዚህ ለተወደደው ለእናንተ ምድር ለግንኙነት ምቹ የሆነች መሬት ትሆን ዘንድ እንዲረዳን በፊቱ ሆና ታማልድልን ዘንድ እንማጸናት። በየትኛውም ባህል ውስጥ የሚገኙ ሐይማኖቶች እና የጎሳ ልዩነት ሳይበግራችሁ የአንዱ ሰማያዊ አባት ልጆች እንደሆናችሁ እውቅና በመስጠትና በመከባበር ትኖሩ ዘንድ ይርዳችሁ። ይህንን ጸሎታችንን ጥንታዊ በሆነው እና “የሰማይ ንግሥት ሆይ” በሚለው ውዳሴ እናቀርባለን። ይህንን ጸሎታችንን የምናደርገው በሶፊያ በሚገኘው እና “የሰማይ ደጃፍ” በመባል በሚታወቀው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምስል ስር ሆነን ሲሆን በቡላጋሪያ ለዚህ የማርያም ምስል ከፍተኛ የሆነ ክብር ይሰጡ የነበሩት እና እንዲሁም በሞታቸው ቀን ያንን ምስል አቅፈው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ 23ኛ በማስታወስ ጸሎታችንን እናቀርባለን።

የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ! ሀሌሉያ!

05 May 2019, 18:16