ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ቄሳውስት “ለሕዝቡ ቅርብ መሆን ይኖርባችዋል” አሉ!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ከትንሣኤ በዓል ቡኋላ የሚገኘው 4ኛው ሰንበት “የመልካም እረኛ” ሰንበት በመባል ይታወቃል። ይህ እለተ ሰንበት በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 04/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን በእለቱ 19 አዲስ ካህናት ማዕረገ ክህነት መቀበላቸውን ተያይዞ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ይህ መዕረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጣችሁ ነጻ ስጦታ በመሆኑ የተነሳ እባካችሁን ጥቃቅን የሆኑ የግል ፍላጎቶቻችሁን ማስጠበቂያ አድርጋችሁት አትጠቀሙ፣ በተቃራኒው እናንተ ለምዕመኑ ቅርብ ለመሆን ሞክሩ” ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የጎርጎሮርሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ከዚህ ከትንሣኤ በዓል በኋላ በሚገኘው በ4ኛው ሳምንት እለተ ሰንበት ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል “በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔ ዐውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል፤ እኔ የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤ ከቶ አይጠፉም፤ ከእጄም ሊነጥቃቸው የሚችል ማንም የለም። እነርሱን የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፤ ከአባቴም እጅ ማንም ሊነጥቃቸው አይችልም። እኔና አብ አንድ ነን” (ዩሐንስ 10፡27-30) ተወስዶ የተነበበው እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን በእለቱ በተመሳሳይ መልኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ  56ኛው ዓለማቀፍ ለመንፈሳዊ ጥሪ ጸሎት የሚደረግበት እለት በጸሎት ታስቦ ማለፉም ተገልጹዋል።

የክርስቶስ ምስጢር ተካፋዮች ናችሁ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ የማዕረገ ክህነት የተቀበሉትን 19 አዳዲስ ካህናት ከግምት ባስገባው  ስብከት እንደ ገለጹት “የቅዱሱ የሐይማኖት አስተምህሮ አገልግሎት አስፈጻሚዎች በመሆናችሁ የተነሳ፣ እናንተ ብቸኛው ጌታ በሆነው በክርስቶስ ተልዕኮ ውስጥ ተስታፊ መሆናቸውን እንዲገነዘቡ” ጥሪ ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን የዚህ የክህነት ምስጢር ተካፋይ መሆን ማለት የአንድ የባሕል ማኅበር አባል መሆን ማለት ሳይሆን ነገር ግን የክርስቶስ ምስጢር ተካፋይ መሆን ማለት ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በስብከታቸው ካህናቱ “የጌታን ቃል በትጋት እንዲያነቡና እንዲያሰላስሉ ያበረታቱ” ሲሆን “አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ በእጁ ይዞ ብዙ ጸሎት ካላደረገ በስተቀር መልካም የሆነ ስብከት ማድረግ አይችልም” ብለዋል። “ስብከቶቻችሁ ለእግዚኣብሔር ሕዝብ መንፈሳዊ ምግብ ይኑን ዘንድ በትጋት መስራት” መዘንጋት የለባችሁም በማለት አጽኖት ሰጥተው የተናገሩት ቅዱስነታቸው የምታስተምሩት መነኛው ዓይነት የሐይማኖት ትምህርት “ከልባችሁ ውስጥ ሲወጣ እና በጸሎት መንፈስ የተወለደ ከሆነ ፍሬያም እንደ ሚሆን” መዘንጋት አይኖርባችሁም ብለዋል።

ጌታ የሚያድነን በነጻ ነው

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት በወቅቱ ማዕረገ ክህነት ለተቀበሉ 19 አዳዲ ካህናት ሊከተሉት የሚገባውን አዲስ የሕይወት መንገድ በተመለከተ እንደ ገለጹት ካሕናት በሕይወታቸው “የጸሎት ሰዎች መሆን ይኖርባቸዋል” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው ምክንያቱንም ሲያስረዱ “በቃላት እና በተግባር የእግዚኣብሔር ቤት የሆነውን ቤተ ክርስቲያን መገንባት ስለሚቻል” እንደ ሆነም ጨምረው ገልጸው “በተለይም ደግሞ ለመስዋዕተ ቅዳሴ ትኩረት መስጠት በፍጹም እንዳትዘነጉ በማለት ጨምረው ገልጸዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .”ጌታ በነፃ ሊያድነን ፈለገ። እርሱ ራሱ በቃሉ እንደ ተናገረው “በነጻ የተቀበላችሁትን በነጻ ስጡ” ብሎናል። በዚህም መስረት የምታከናውኑት መስዋዕተ ቅዳሴ የእዚህ ነጻ የሆነ ስጦታ የመጨረሻው መገለጫ ምልክት ነው። እባካችሁን በራሳችሁ ጥቃቅን በሆኑ የግል ፍላጎቶቻችሁ የተነሳ ይህንን ምስጢር አታጉድፉት” ብለዋል።

መሐሪ ከመሆን አትታክቱ

በምስጢረ ንስሐ አማካይነት በእግዚኣብሔር፣ በክርቶስ እና በቤተ ክርስትያን ሥም የሐጢአት ስርሄት መስጠት ይኖርባችኋል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል. . .

“እዚህ ጋር እባክችሁን ምሕረት አድራጊዎች ከመሆን እንዳትታክቱ እጠይቃችኋለሁ። አባታችን መሐሪ እንደ ሆነ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ እና ለሁላችን ምሕረት አድርጎልን እንደ ነበረ እናንተም ምሕረት አድርጊዎች ሁኑ። በሚስጢረ ቀንዲል አማካይነት በምትቀቡት ቅባት ለበሽተኛው ፈውስ አምጡ። ከታመሙ ሰዎች ጋር ጊዜያችሁን ማሳለፍ እንዳትዘነጉ።

ለእግዚኣብሔር ቅርብ ሁኑ

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማብቂያ ላይ እንደ ገለጹት "በደስታ መንፈስ እና በቅን ልቦና በሚደረግ ልገሳ የክርስቶስ ክህነታዊ ተግባር በሕይወታችሁ በመለማመድ ራሳችሁን ሳይሆን እግዚኣብሔርን ብቻ ደስ ለማሰኘት” ማከናወን እንደ ሚገባቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው “የክህነት ሕይወት ደስታን ሊሰጥ የሚችለው በዚህ መልኩ ይህንን ጥሪ የሰጠንን እግዚኣብሔርን ብቻ ለማስደሰት በሚከናወኑ ተግባራት አማካይነት እንደ ሆነ ቅዱስነትቸው አጽኖት ሰጥተ ገልጸዋል። አንድ ካህን “በጸሎት አማካይነት ለእግዚአብሔር፣ ለጳጳሱ፣ ለሌሎች ካህናት እና እንዲሁም ለእግዚኣብሔር ሕዝቦች ሳይቀር ቅርብ መሆን እንደ ሚገባው ገልጸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .”ሁል ጊዜም ቢሆን ሊገለገል ሳይሆን ሊያገለግል እና የጠፋውን ሊፈልግ የመጣውን የመልካም እረኛውን ምሳሌ በዓይኖቻችሁ ፊት ለፊት ላይ በማኖር ሕይወታችሁን መኖር እንዳትዘነጉ” ካሉ በኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
12 May 2019, 16:18