ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካቴድራል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካቴድራል  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “አባታችን ሆይ!” የሚለው ቃል የሁላችን የሆነ አንድ የጋራ አባት እንዳለን ያሳ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከግንቦት 23-25/2011 ዓ.ም ድረስ 30ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በሮማኒያ እያደረጉ መሆኑን ቀደም ሲል መግለጸቻን ይታወሳል። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከግንቦት 23-25/2011 ዓ.ም ድረስ 30ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በሮማኒያ ማድረጋቸውን በቀጠሉበት ወቅት በቅድሚያ በአገሪቷ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ውስጥ በእዚያው ለተገኙ የአገሪቷ ባለስልጣናት፣ የሲቪክ ማኅበረሰብ አባላት እና የተለያዩ አገራትን ልዑካን በተገኙበት የአገሪቷ ርዕሰ ብሔር ካደረጉት የእንኳን መጣችሁ መልእክት በመቀጠል ቅዱስነታቸው ንግግር ማድረጋቸውን ቀደም ሲል መገለጻችን የሚታወስ ሲሆን ከእዚያም በመቀጠል በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ 10፡15 ላይ በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ መኖሪያ ሕንጻ በማቅናት በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ በሆኑት በብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል ደማቅ አቀባበል ተድርጎላቸው እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእዚያው ለተገኙ በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል እና በአገሪቷ የምትገኘው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ቋሚ አባላት ንግግር ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት “እኛን የሚያገናኝ የእምነት መስተሳስር ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የነበረ ነው” ማለታቸው መግለጻችን ይታወሳል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ቅዱስነታቸው ከእዚያን በመቀጠል አዲስ በተገነባው በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካቴድራል ማቅናታቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚያው በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል እና በአገሪቷ የምትገኘው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ቋሚ አባላት ጋር “አባታችን ሆይ!” የሚለውን ጸሎት መድገማቸው ተገልጹዋል።
በወቅቱ ቅዱስነታቸው “በእዚህ ቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ በጋራ ስለተሰበሰብን እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል” በማለት መናገራቸው የተገለጸ ሲሆን “ኢየሱስ ወንድማማቾቹን ጴጥሮስ እና እንድርያስን ጠርቶ የዓሳ ሳይሆን የሰው አጥማጆች እንዲሆኑ እንደ መረጣቸው” ገልጸው “አንድ ወንድም ብቻ ለአገልግሎት መጥራት ሙሉ እንደማያደርግ ኢየሱስ በመረዳቱ የተነሳ ሁለቱንም ወንድማማቾች መጥራቱን ገልጸው በእዚህም መሰረት ዛሬ እኛ ጎን ለጎን ሆነን አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት መጸለያችን መልካም ገጽታ አለው ብለዋል። ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ “ወላጅ እንደ ሌላቸው ልጆች ብቻችሁን አልተዋችሁም” በማለት ቃል ገብቶላቸው እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው አብረን በመጸለያችን ብቻችንን እንዳልሆንን ያሳያል ብለዋል።
ቅዱሰንታቸው ንግግራቸውን በቀጠሉበት ወቅት “አባታችን ሆይ” በሚለው ጸሎት ውስጥ የሚገኙትን የመማጸኛ ቃላትን አንድ በአንድ በአጭሩ ማብራራታቸው የተገለጸ ሲሆን “አባታችን” የሚለው ቃል የሁላችን የሆነ አንድ የጋራ አባት እንዳለን ያሳያል፣ የእኔ አባት እና የእንተም አባት የሚለውን ትርጉም እንደ ሚያሰማ ገልጸዋል።
በሰማይ የምትኖር” የሚለው ቃል ደግሞ ሰማያት በሁሉም ማለትም በክፉዎች እና በደጎች፣ በፍትሃዊ እና ኢፍታዊ በሆኑ ሰዎች ላይ የምትወጣው ጸሐይ መገኛ” እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው እኛ በምድር ላይ ልናመጣው ያልቻልነውን ሰላምና ኅበረት ማስፈን እንችል ዘንድ የሚያሳስበን ነው፣ ይህንንም ለማድረግ እንችል ዘንድ በሰማይ ቤት የሚገኙትን በእምነት አባት እና እንት የሆኑትን የቅዱሳንን አማላጅነት መማጸን ይገባል ብለዋል።
ስምህ ይቀደስ” የሚለው መማጸኛ ደግሞ በሰማይ ቤተ ከሚገኙ ከቅዱሳን ጋር በጋራ በመሆን የእኛ ስም ሳይሆን የእርሱ፣ በጎ ሥራዎችን እንድናከናውን የሚረዳን እና የምያንቀሳቅሰን የእግዚኣብሔር ስም የተቀደሰ ይሁን የሚለውን ትርጉም እንደ ሚያሰማ ገልጸዋል።
መንግሥትህ ትምጣ” የሚለው መማጸኛ ደግሞ የአንተ መንግሥት ትመጣ ዘንድ በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን፣ የእግዚኣብሔር መንግሥት ይመጣ ዘንድ በናፍቆት እንጠባበቃለን፣ ምክንያቱ አሁን በዓለም ውስጥ የሚታዩ ሁኔታዎች የእግዚኣብሔር መንግሥት መምጣትን የማይደግፉ በመሆናቸው የተነሳ የሰማያዊ አባታችን መንግሥት ይመጣ ዘንድ በመማጸን በዓለም ውስጥ የሚታዩ” ያልተገቡ ድርጊቶችን በመላካም ይቀይርልን ዘንድ የምንማጸንበት የጸሎት ክፍል ነው ብለዋል።
ፍቃድህ ይሁን” የሚለው መማጸኛ ደግሞ “የእግዚኣብሔር ፈቃድ ሁሉም ይድኑ ዘንድ ነው” የሚለውን ትርጉም የሚያሰማ እንደ ሆነ ገልጸው አድማሳችንን በማስፋት ውስንነታችንን በእርሱ በአባታችን ምሕረት ውስጥ በማስገባት ሁሉም የሰው ልጆች ይድኑ ዘንድ በመመኘት የምንጸልየው የመማጸኛ ጸሎት መሆኑን ያስረዳል ብለዋል።
“የእለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን” የሚለው የመማጸኛ ጸሎት ደግሞ እግዚኣብሔር የሕይወት እንጀራ መሆኑን እና ይህም የተወደድን የእግዚኣብሔር ልጆች መሆናችንን እንድናስተውል ያደርገናል፣ ወላጅ አልባ ሕጻናት እንዳልሆንም እንድንረዳ ያደረገናል” የሚለውን ትርጉም እንደ ሚያሰም ገልጸው እርሱ ለሁላችን የሚያገለግል የሕይወት እንጄራ በመሆኑ የተነሳ እኛም እርስ በእርሳችን አንዱ አንዱን እንድያገልግል ይረዳን ዘንድ የምንጸልየው መማጸኛ ነው ብለዋል።
በተመሳሳይ መልኩም ዛሬ በዚህ አባታችን ሆይ በሚለው ጸሎት ውስጥ “የእለት እንጀራችንን ስጠን” ብለን የምንማጸነው ጸሎት በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ውስጥ በቂ የሆነ የምግብ ክምች ቢኖርም ቅሉ የሚቀመስ ምግብ አጥተው የሚሰቃዩ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን እግዚኣብሔር ያስባቸው ዘንድ የምንማጸንበት የጸሎት ክፍል እንደ ሆነ ገልጸው በተለይም ደግሞ ከምግብ ባሻገር ፍቅር የተራቡ ብዙ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ስለሚገኙ እግዚኣብሔር በበረኩት ያጠግባቸው ዘንድ በማሰብ የምንጸልየው የመማጸኛ ጸሎት ነው ብለዋል።
በደላችንን ይቅር በልልን” የሚለው የመማጸኛ ጸሎት ደግሞ እግዚኣብሔር ኋጢአታችንን ይቅር ይለን ዘንድ በማሰብ የምንጸልየው ጸሎት እንደ ሆነ ገልጸው እኛም በበኩላችን የበደሉንን ሰዎች በደል ይቅር ማለት እንደ ሚጠበቅብን የሚያሳስብ የጸሎት ክፍል እንደ ሆነ ገልጸዋል። በተጨማሪም ይህ የጸሎት ክፍል ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ይቅር ማለት እንችል ዘንድ ብርታቱን እግዚኣብሔር ይሰጠን ዘንድ የምንማጸንበት የጸሎት ክፍል እንደ ሆነ ገልጸው እግዚኣብሔር ይቅር እንደ ሚለን እኛም እርስ በእርሳችን ይቅር መባባል እንችል ዘንድ እንዲረዳን፣ እንዲያነሳስን የምንጸልየው ጸሎት ነው ብለዋል።
ወደ ፈተና አታግባን” የሚለው የመማጸኛ ጸሎት ደግሞ እግዚኣብሔር ከፈተና ውስጥ ያወጣን ዘንድ በተለይም ክፉ የሆነ መንፈስ ከልባችን ውስጥ ያስወግድልን ዘንድ በማሰብ የምንጸልየው የመማጸኛ ጸሎት እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ወደ ፈተና ውስጥ ለመግባት በከፍተኛ ሁኔታ በምንፈተንበት ወቅት እግዚኣብሔር ከእዚህ ፈተና ያወጣን ዘንድ፣ ከኋጢአት ቀንበር ሥር ያላቅቀን ዘንድ እና ሁሉም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን መሆናቸውን በመገንዘብ በጋራ እና በመተጋገዝ ወደ እርሱ ወደ እግዚአብሔር መጓዝ እንችል ዘንድ እንዲረዳን የምንጸልየው የመማጸኛ ጸሎት መሆኑን ገልጸው እግዝአብሔርን ሁል ጊዜ አባት ብለን መጥራት እንችል ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጠን እንማጸነው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው አስተንትኖዋቸውን አጠናቀዋል።

 

31 May 2019, 11:57