ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሴሜን መቀዶኒያ በደረሱበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሴሜን መቀዶኒያ በደረሱበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ትልቅ የሆነ ሕልም ይኑራችሁ፣ የጋራ የሆነ ሕልም ይኑራችሁ” አሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቡልጋሪያ እና ሰሜን መቀዶኒያ ከሚያዝያ 27-29/2011 ዓ.ም ድረስ በቅደም ተከተል ያደርጉትን 29ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመቀጠል በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 29/2011 ዓ.ም ሰሜን መቀዶኒያን መጎብኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በቡልጋሪያ የነበራቸውን ቆይታ ካጠናቀቁ በኋላ የዚህ የ 29ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ሁለተኛ መዳረሻ ወደ ሆነችው ሴሜን መቀዶኒያ አቅንተው እንደ ነበረ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው የሰሜን መቀዶኒያ ዋና ከተማ ወደ ሆነችው እስኮፒዬ በደረሱበት የሐገሪቷ ርዕሰ ብሔር አቀባባል ያደረጉላቸው ሲሆን ባሕላዊ ልብስ የለበሱ ሕጻናት የአበባ ጉብጉን ለቅዱስነታቸው ማቅረባቸውም ተገልጹዋል።

በመቀጠልም ቅዱስነታቸው በሰሜን መቀዶኒያ ዋና ከተማ በሆንቸው እስኮፕዬ ውስጥ በሚገኘው የአገሪቷ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ውስጥ ለተገኙ የአገሪቷ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ በስፍራው ለነበሩ ለሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች እና የተለያዩ አገራት ልዑካን ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት ትልቅ የሆነ ሕልም በጋራ ማለም እንደ ሚገባቸው የገለጹ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ያደረጉት ንግግር እርሳቸው በርዕሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ዘመን ቅድሚያ የሚሰጡዋቸውን ጉዳዮች የሚያመላክት ንግግር ማድረጋቸው ተገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት ሰሜን መቀዶኒያ በጣም ብዙ የተለያዩ ባሕሎች እና የተለያየ እምነት ተከታዮች በሰላም የሚኖሩባት አገር መሆኑዋን ገልጸው በተለይም ደግሞ “ሰላማዊና ዘላቂነት ያለው አንድነት መኖሩ እንደ ሚያስደስታቸው ገልጸው በአገሪቷ ሕዝቦች እጅግ ውድ የሆነ ውርስ በመባል የሚታወቀው የሕቦች እና የሐይማኖት ብዝሃነት በመቻችል የሚኖሩባት አገር መሆኗ እጅግ በጣም መልካም የሆነ የአገሪቷ ገጽታ እንደ ሆነ ገልጸዋል።

የዚህ የብዝሃነታችሁ ትልቅ ምስክር የሚሆነው ደግሞ በመላው ዓለም የሚታወቁት ቅድስት እማሆይ ትሬዛ መሆናቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው እኝህ ቅድስት በዓለም ሕዝቦች ቀለል ባለ ሁኔታ “እማሆይ ትሬዛ” በማለት እንደ ሚጠሩዋቸው ገልጸው ቅድስት እማሆይ ትሬዛ ተወልደው ባደጉባት በእስኮፒዬ ውስጥ ከሚገኙ ማኅበርሰቦች በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን እንዴት መውደድ እንደ ሚገባቸው ትምህርት መቅሰማቸውን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

እማሆይ ትሬዛ "ድሆችን፣ የተናቁትን፣ ለጥቃት ተገላጭ የሆኑትን እና ስደተኞችን" በቃላት ብቻ ሳይሆን በተጨባጭና ውጤታማ የሆኑ ድርጊቶችን በመፈጸም ሳይቀር እንዴት መውደድ እንደ ሚገባን ምሳሌ አሳይተውን ማለፋቸውን ገልጸዋል።

በሰሜን መቀዶኒያ የሚገኙ የካቶሊክ እመንት ተከታዮች ከአገሪቷ አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር ውስጥ አንድ በመቶ ያህሉን ብቻ እንደ ሚወክሉ ከስፍራው የደረሰን ዜና የገለጸ ሲሆን በአገሪቷ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የፍቅር፣ የተስፋ እና በልዩነት ውስጥ የሚገኘውን አንድነት በመግለጽ የሰላም መልእክተኞች ይሆኑ ዘንድ ጥሪ ማቀረባቸው የተገለጸ ሲሆን ይህንምም ከሁሉም በላይ ደግሞ በተግባር እና ተጨባጭ በሆነ መልኩ በሕይወታቸው መግለጽ እንደ ሚኖርባቸው ጨምረው ገልጸዋል።

07 May 2019, 16:07