ፈልግ

 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰሜን መቀዶኒያ ከወጣቶች ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰሜን መቀዶኒያ ከወጣቶች ጋር በተገናኙበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለወጣቶች “ሕልማችሁን እውን ለማድረግ በትጋት ሥሩ” አሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቡልጋሪያ እና ሰሜን መቀዶኒያ ከሚያዝያ 27-29/2011 ዓ.ም ድረስ በቅደም ተከተል ያደርጉትን 29ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመቀጠል በሰሜን መቀዶኒያ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር በዋና ከተማዋ መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ተስፋችሁን እና ሕልማችሁን እውን ለማድረግ ትጉ ማለታቸው ተገልጹዋል።

ቅዱስነታቸው ከወጣቶቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ ያደርጉት ንግግር ሕልም እና ሕልምን የማለም ጠቀሜታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ንግግር እንደ ነበረ ከስፍራው የደረሰን ዜና የሚያስረዳ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የሚገኙ እጅግ በጣም ብዙ የሚባሉ ሰዎች ሕልም የማለም ችሎታዎቻቸውን እያጡ መምጣታቸውን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ሕልም በእውነት ሊደረስበት የሚችል ሌላ ዓለም እንዳለ እርግጠኞች እንድንሆን እና እዚያ ሥፍራ ላይ ለመደረስ ደግሞ የበኩላችንን ጥረት እንድናደርግ እንደ ሚገፋፋን” የገለጹት ቅዱስነታቸው “ሕልሞቻችን እውን ሊሆኑ የሚችሉት ደግሞ በተስፋ፣ በትዕግስት እና በቁርጠኝነት መሥራት ስንችል ብቻ” ነው ብለዋል። "እድላችንን ለመጠቀም ወይም ደግሞ ስህተት ለመሥራት" በፍጹም መፍራት የለብንም” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ስህተት ብትሰሩም እንኳን ከወደቃችሁበት ተነስታችሁ በአዲስ መልክ ጉዞዎቻችሁን ለመቀጠል ትችላላችሁ፣ በዚህም የተነሳ ሕልም አላሚ እና ተስፋ ስጪ መሆናችሁን በፍጹም እንዳታቋርጡ” ብለዋል።

የእማሆይ ትሬዛን አብነት መከተል

ወጣቶች የእማሆይ ትሬዛን አብነት በመከተል “በእጆቻቸው መሥራትን፣ ሕይወታቸውን ከቁም ነገር መቁጠር እና ሕይወታቸውን ውብ የሆን ነግሮችን ለማከናወን እንዲጠቀሙበት” መጠራታቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው እማሆይ ትሬዛ በሕይወት ዘመናቸው በጣም ታላላቅ የሚባሉ ነገሮችን ማለም ይወዱ እንደ ነበረ አስታውሰው በዚህም ምክንያት የተነሳ ነው እርሳቸው በሕይወት ዘመናቸው በጣም ትልቅ የሚባል ተግባራ በማከናወን ያለፉት ብለዋል። እማሆይ ትሬዛ “በእግዚኣብሔር እጅ ውስጥ የሚገኝ እርሳስ ለመሆን ፈለገው እንደ ነበረ” ገልጸው “በዚህ የተነሳ እግዚኣብሔር የእርሳቸዉን አስገራሚ ታሪክ ገጾች መጻፍ እንደ ጀመረ” ቅዱሰናትቸው ጨምረው ገልጸዋል። “ መነኛችንም ብንሆን ሕልሞቻችንን በራሳችን ኃይል ብች እውን ለማደረግ አንችልም” ያሉት ቅዱስነታቸው “ሕልሞቻችን እውን ይሆኑ ዘንድ የሚረዳን ማኅበረሰብ ያስፈልገናል” ብለዋል። ከሌሎች ሰዎች ጋር የጋራ የሆነ ሕልም ማለም ተገቢ እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው “የሌሎች ሰዎችን ሕልም አትቃረኑ፣ ጋብቻን ለመመስረት አልሙ፣ በእናንተ ውስጥ የሌሉ ነገሮችን ለማግኘት አልሙ፣ የጋራ የሆነ ሕልሞችን አልሙ” ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት እየተዘነጋ ወይም እየተተወ ያለ፣ ነገር ግን በማኅበርሰቡ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ከሚባሉት ነገሮች መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሰውን ፊት ለፊት ተገናኝቶች የመወያየት እና የመነጋገር ክህሎት ማዳበር እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው አሁን ያለንበት የቴክኖሎጂ ወይም ዲጂታል የሆነ ዓለም ፊት ለፊት ተገናኝቶ የመነጋገር እና የመወያየት በሕል በከፍተኝ ሁኔታ እንዲቀንስ እያደረገ እንደ ሆነ ገልጸው ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም መገናኘት እንችላለን ነገር ግን በዚህ ረገድ የእኛ ቀጥተኛ የሆነ ተሳታፊነት ሊኖር እንደ ማይችል ገልጸው ፊት ለፊት ተገናኝቶ መልካም ይሁን መልካም ያልሆኑ ተሞክሮዎቻችንን ተገናኝተን በማውራት እና በመወያየት መልካም የሆነ የሕይወት ገጽታ ለመገንባት መጣር ይኖርብናል ብለዋል።

አረጋዊያንን ማዳመጥ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰሜን መቀዶኒያ በነበራቸው የአንድ ቀን ቆይታ ማብቂያ ላይ ከወጣቶች ጋር በነበራቸው ቆይታ ማብቂያ ላይ እንደ ገለጹት ወጣቶች በሁኑ ወቅት በጣም አስፈላጊ የሆነ እሴት ማዳበር ከፈለጉ አረጋዊያንን ማዳመጥ እንደ ሚኖርባቸው ገልጸው በዚህ ረገድ ወጣቶች ከአያቶቻቸው ጋር ጊዜ ማሳለፈ እንደ ሚገባቸው ገልጸው “ታሪኮቻቸውን አድምጡ" ብለዋል።

ሕልማችሁ እየደበዘዘ ሲሄድ እና ልባችሁ መስመጥ ሲጀምር" ማኅበረሰቡ እንዲረዳችሁ ጠይቁ፣ እርስ በእርሳችሁ እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ ተጓዙ፣ እናንተ ሕያዋን እንድትሆኑ የሚፈልግ አንድ ኃይል እንዳለ መቼም ቢሆን እንዳትዘነጉ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

07 May 2019, 16:12