ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ቅዱስ ቁርባን ሁላችንም ወንድማማቾች መሆናችንን እንድንረዳ ያደርገናል” አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከሚያዝያ 27-29/2011 ዓ.ም ድረስ 29ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በቡላጋሪያ እና በሰሜን መቀዶኒያ በቅደም ተከተል እያደርጉ መሆናቸውን ቀድም ሲል መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው በቡላጋሪያ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመቀጠል በሚያዝያ 27/2011 ዓ.ም በዚያው በቡልጋሪያ ራኮቪስኪ በመባል በምትታወቀው እና ከፍተኛ የሆነ የካቶሊክ ምዕመናን ቁጥር በሚገኝባት ከተማ ውስጥ በሚገኘው ኬንያዝ አሌክሳንደር ቀዳማዊ በመባል በሚታወቀው አደባባይ ላይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ቅዱስነታቸው መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው እንደ ነበረ ከስፍራው ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በእለቱ በተደረገው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የመጀመርያ ቅዱስ ቁራባን የተቀበሉ ታዳጊ ሕጻናት መሳተፋቸውም ተገልጹዋል፣ በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባስረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ግለጹት “ቅዱስ ቁርባን ሁላችንም ወንድማማቾች እና እህተማማቾች መሆናችንን መገንዘብ ያስቸልን ዘንድ ይረዳናል”  ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በወቅቱ ቅዱስነታቸው ያደርጉት ስብከት አጭር እና ግልጽ፣ እንዲሁም በቀጥታ በእለቱ የመጀመርያ ቅዱስ ቁርባን የተቀበሉትን 242 ሕጻናት ከግምት ያስገባ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ የመጀመርያ ቅዱስ ቁርባን የተቀበሉት ሕጻናት ከተለያዩ አከባቢዎች የተውጣጡ ሕጽናት መሆናቸው የገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ሕጻናቱን “የጽገሬዳ ምድር” ፍሬዎች በማለት የጠሩዋቸው ሲሆን ቅዱስነታቸው ይህንን ያሉት ቡልጋሪያ ከመካከለኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ለሽቱ መስሪያ የሚያገለግል የጽገሬዳ አበባ ዘይት አምርች አገር መሆኑዋን ለማመልከት እንደ ሆነም ከስፍራው ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

“ኢየሱስ ሕያው ነው እዚህ ከእኛ ጋር አሁን ይገኛል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህም የተነሳ ነው ዛሬ ሕያው የሆነውን ጌታ በቅዱስ ቁርባን አማካይነት እንገናኘዋለን፣ በአካላዊ ዓይናችን እርሱን በቅዱስ ቁራባን መመልከት ባንችልም ነገር ግን በእምነት ዓይን እርሱን መመልከት ግን እንችላለን” ብለዋል።

በወቅቱ የመጀመርያ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የተዘጋጁ ሕጻናት የለበሱዋችውን ነጫጭ ልብሶች እና በወገባቸው ላይ የታጠቁትን ነጭ ገመድ በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው “ትርጉም ያለው እና ቆንጆ ምልክት " መሆኑን ገልጸው “ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ለመሆን የሚፈልገውን ክርስቶስን እያካበርነው እንደ ምንገኝ ያሳያል ብለዋል” ብለዋል።

በእለቱ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰውን ኢየሱስ ጥቂት ዓሣ እና ጥቂት እንጀራ ከባረከ በኋላ 5ሺ የሚሆኑ ሕዝቦችን እንደ መገበ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይህ ተዐምር ሊከሰት ወይም ሊፈጸም የቻለው አንድ ሕጻን ልጅ ለኢየሱስ ባቅረበው ትንሽ ዓሣ እና እንጀራ አማካይነት መሆኑን ገልጸው ተዐምራት በሕይወታችን ውስጥ ለፈጸሙ የሚችሉት እንደ እናንተ ያለ ንጹዕ ልብ ሲኖረን ብቻ እንደ ሆነ ገልጸው ካለው ማካፈል የሚችል ልብ፣ ሕልም ያለው ልብ፣ አመስጋኝ የሆነ ልብ፣ ሌሎች ሰዎችን ማመን እና ማክበር የሚችል ልብ ሲኖረን ተዐምራት በሕይወታችን ውስጥ ሊፈጸሙ ይችላሉ ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ይህ በዓል "ለእናንተና ለቤተክርስቲያኒቷ በሙሉ" የኅብረት ቀን ነው፣ ምክንያቱም "ቅዱስ ቁርባን ሁሉም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ህብረት እንዲፈጥሩ የሚያስችል ኃይል እንዳለው የገለጹት ቅዱስነታቸው የእኛ መታወቂያ ካርድ የሚሆነው እግዚአብሔር አባታችን፣ ኢየሱስ ወንድማችን፣ ቤተክርስትያን ደግሞ ቤተሰባችን” መሆኑ እንደ ሆነ ገልጸው በዚህም የተነሳ ሁላችንም “ወንድማማቾች እና እህተማማቾች ነን ሕጋችን ደግሞ መሰረቱን ያደርገው በፍቅር ላይ ነው” ብለዋል።

05 May 2019, 18:08