ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራቸስኮስ በቡልጋሪያ እና በሰሜን መቀዶኒያ የነበራቸውን ቆይታ አጠቃለው በሚመለሱበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራቸስኮስ በቡልጋሪያ እና በሰሜን መቀዶኒያ የነበራቸውን ቆይታ አጠቃለው በሚመለሱበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ጌታ ብርታትን ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ” አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ማነኛውንም ዓይነት ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሮም ሲመለሱ እንደ ተለመደው እና ዘወትር ማነኛውንም ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው በሚመለሱበት ወቅት በአውሮፕላን ውስጥ ሆነው ጋዜጠኞች ስላከናወኑት ሐዋርያዊ ጉብኝት እና ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች እንደ ሚያቀርቡላቸው እና ቅዱስነታቸው ምላሽ እንደ ሚሰጡ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው ቡልጋሪያ እና ሰሜን መቀዶኒያ ከሚያዝያ 27-29/2011 ዓ.ም ድረስ በቅደም ተከተል ያደርጉትን 29ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው በሚመለሱበት ወቅት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች መልስ መስጠታቸው የተገለጸ ሲሆን በቡልጋሪያ እና በሰሜን መቀዶኒያ የነበረኝ ሐዋርያዊ ጉብኝት በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ “ጌታ ብርታትን ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ” ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በወቅቱ ቅዱስነታቸው ከጋዜጠኖች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በቡልጋሪያ ከምትገኘው ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር ስላለው ግንኙነት እና እንዲሁም የእርሳቸው ጥንካሬ እና ጉልበት ምስጢር ምን እንደ ሆነ በሚገልጹ ጭብጦች ላይ እንደ ነበረ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

በቡልጋሪያና በሰሜን መቄዶኒያ ስለነበራቸው ቆይታ

በቡልጋሪያና በሰሜን መቄዶኒያ ስለነበራቸው ቆይታ የተሰማቸውን ስሜት እንዲገልጹ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ቅዱስነታቸው በሰጡት ምላሽ እንደ ገለጹት እነዚህ “ሁለቱ አገራት ሙሉ በሙሉ የተለያዩ አገሮች መሆናቸውን” ገጸዋል።

ቡልጋሪያ ለዘመናት ያህል የዘለቀ ባሕል ያላት አገር መሆኑዋን፣ ሰሜን መቀዶኒያም ለዘመናት የዘለቀ ባሕል ያላት አገር ብትሆንም ቅሉ ነገር ግን ገና ወጣት የሆነች አገር እና በወጣት ትውልድ የተሞላች አገር መሆኑዋን ገለጸዋል።

ሰሜን መቄዶንያ በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በቅርብ ጊዜ እንደ አዲስ አገር ሆና በአዲስ መልክ የተቋቋመች አገር መሆኑዋን፣ የክርስትና እምነት ለመስበክ ወደ ኤሺያ አህጉር በመሄድ ላይ በነበረበት ወቅት ወደ መቀዶኒያ እንዲሄድ በተጠራው በሐዋርያው ጳውሎስ አማካይነት የክርስትና እምነት ወደ ምዕራቡ ዓለም እንዲገባ ያደረገች በምልክትነት የምትጠቀስ አገር መሆኑዋን የገለጹት ቅዱስነታቸው "የመቄዶንያ ሕዝቦች የክርስትና እምነት ወደ ምዕራቡ ዓለም የገባው የእነርሱን አገር እንደ በር ተጠቅሞ እንደ ነበረ አሁኑም ቢሆን ከመግለጽ አልታከቱም” ብለዋል።

ቡልጋሪያ በርካታ ጦርነቶች እና ዓመፅ የተሰነዘረባት እና ያስተናገደች አገር እንደ ነበረች ያስታወሱት ቅዱስነታቸው እ.አ.አ በ 1877 ዓ.ም ከኦቶማን ቅኝ ግዛት ሥር ነጻ ለመውጣት ባደረገችው ጦርነት ምክንያት በአገሪቷ የሞቱትን ከ200, 000 ሺ በላይ የራሻ ወታደሮችን በዋቢነት ገልጸዋል። “ነጻነታቸውን ለመጎናጸፍ ብዙ ትግል ያደረጉ፣ በሂደቱ ብዙ ደም የፈሰሰባቸው፣ ብሔራዊ ማንነታቸውን ለማስጠበቀ የተጉ” አገራት ቢሆኑም ቅሉ በሁለቱም አገራት ውስጥ የኦርቶዶክስ እና የካቶሊክ አብያተ ክርስትያን ምዕመናን እና እንዲሁም የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ሕዝቦች በጋራ የሚኖሩባቸው አገራት እንደ ሆኑ ጨምረው ገልጸዋል።

በሁለቱም አገራት ውስጥ በሚገኙ በተለያዩ እምነቶች መካከል ያለው በመከባበር ላይ የተመሰረተ መልካም ግንኙነት እንዳለና እነዚህም የተለያዩ የእመን ተቋማት ልዩነታቸውን በማክበር እንደ ሚኖሩ፣ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ እና ዜጎች እርስ በእስርስ እንዲቀባበሉ ለማሳችል የሚያደርጉትን ጥረት እንደ ሚያደንቁ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ የኃይላቸው ምንጭ ምንድነው?

አንድ ጋዜጠኛ እንደ እዚህ ለመጓዝ እና ለመሥራት የሚያስፈልገውን ኃይል እና ጥንካሬ ከየት እንደ ሚያገኙ በማውሳት ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ይህንን ኃይል እና ጥንካሬ ለማግኘት “ወደ ጥንቆላ እንደ ማልሄድ በቅድሚያ ላረጋግጥልህ እወዳለሁ” በማለት የተናገሩ ሲሆን ጥንካሬው እና ኃይል “የጌታ ስጦታ" እንደ ሆነ ገልጸው እርሳቸው በሚሄዱባቸው ስፍራዎች ሁሉ ኃይል እና ጉልበት የሚሆናቸው እግዚኣብሔር እንደ ሆነ ገልጸዋል።

“ማነኛውንም ሐዋርያዊ ጉብኝት በሚያደርጉበት ወቅት እንደ ማይደክማቸው፣ ነገር ግን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ከተመለሱ በኋላ የድካም ስሜት እንደ ሚሰማቸው” በግልጽ የተናገሩት ቅዱስነታቸው “ብርታቱን እና ጥንካሬውን የሚሰጠኝ እግዚኣብሔር ነው” ብለዋል። “ለእርሱ እና እርሱ ለሰጠኝ አገልግሎት ታማኝ እሆን ዘንድ እንዲረዳኝ እግዚኣብሔር እጠይቀዋለሁ፣ የማደርጋቸው ሐዋርያዊ ጉብኝቶች እንደ አንድ የአገር ጎብኚ ሆኜ ሳይሆን ነገር ግን የሰላም መልእክተኛ ሆኜ አከናውን ዘንድ እንዲረዳኝ እጠይቀዋለሁ፣ ያለእርሱ እርዳታ ምንም ነገር ማከናወን አልችልም” ብለዋል።

ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ

በቡልጋሪያ ከሚገኘው ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ከኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ጋር ያለው ግንኙነት ጠቅለል ባለ መልኩ በጎ እና በመልካም ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንዳለ ጨምረው ገልጸዋል።

07 May 2019, 10:53