ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቡላጋሪያ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ጀመሩ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቡልጋሪያ እና ሰሜን መቀዶኒያ ከሚያዝያ 27-29/2011 ዓ.ም ድረስ በቅደም ተከተል የሚያደርጉትን 29ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመጀመር በሚያዝያ 27/2011 ዓ.ም የዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የመጀመርያ መዳረሻ ወደ ሆነችው ወደ ቡላጋሪያ አቅንተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው በሮም ከተማ አቅራቢያ ከሚገኘው የሊዮናርዶ ዳቪንቺ ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ በሮም የሰዓት ቆጣጠር ከጥዋቱ 1 ሰዓት ላይ ተነስተው 895 ኪሎሜትሮችን በአየር ላይ አቋርጠው የሁለት ሰዓት በረራ ካደርጉ በኋላ የቡላጋሪያ ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ወደ ሶፊያ ደርሰዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የቡላጋሪያ ሪፖብሊክ ጠቅላይ ሚንስትር በሆኑት ቦዪኮ ቦሪዞፍ እና በአገሪቷ የቫቲካን ልዑክ አቀባባል ያደረጉላቸው ሲሆን 4 ሕጻናት ለቅዱስነታቸው የአበባ ጉንጉን በስጦታ መልክ አበርክተዋል።

ቅዱስነታቸው በጠቅላይ ሚንስትሩ ታጅበው ወደ አንድ መቆያ ክፍል በመግባት በእዚያ ሁለቱ ማለትም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የአገሪቷ ጠቅላይ ሚንስትር የግል ውይይት ማድረጋቸው ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

05 May 2019, 17:46