ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ ከቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛን ጋር፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ ከቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛን ጋር፣ 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛን ጎበኙ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማተር ኤክለሲያ ገዳም የሚገኙትን የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛን የጎበኙት የጎርጎሮሳዊውን የቀን አቆጣጠር በምትከተል ካቶሊካዊ ቤተክርስቲያን ሊከበር የተቃረበውን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል ምክንያት በማደረግ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን ለማቅረብ እና ለልደታቸው 92ኛ ዓመት እንኳን አደረሱ ለማለት እንደሆነ ታውቋል።

በጎርጎሮሳዊው የቀን አቆጣጠር መሠረት ትናንት ሰኞ በተጀመረው የሕማማት ሳምንት መግቢያ ላይ የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ጊዜያዊ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አሌሳንድሮ ጂሶቲ፣ ርዕሠ ሊቃነ ራንችስኮስ በቫቲካን ውስጥ ወደሚገን ማቴር ኤክሌሲያ ገዳም ሄደው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛን የሚጎበኙ መሆናቸውን በመግለጫቸው ማስታወቃቸው ይታወሳል። የመግለጫ ክፍሉ ዳይሬክተር አቶ አሌሳንድሮ ጂሶቲ እንደተናገሩት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጉብኝት ለቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ያላቸውን አክብሮት እና ፍቅር የሚገልጹበት እንደሆነ ገልጸው ለ92ኛ የልደት በዓላቸው የተሰማቸውን ልባዊ ደስታ የሚገልጹበት አጋጣሚ ይሆናል ብለዋል።       

16 April 2019, 17:08