ፈልግ

የጀርመን ፍራንችስካዊያን የወንጌል ተልዕኮ እንቅስቃሴ አባላትን ተቀብለው ባነጋገሩበ ጊዜ፣ የጀርመን ፍራንችስካዊያን የወንጌል ተልዕኮ እንቅስቃሴ አባላትን ተቀብለው ባነጋገሩበ ጊዜ፣ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “ቤተክርስቲያን እውነተኛ ለውጥን ማምጣት የምትችለው የእግዚአብሔርን ቃል በማዳመጥ ብቻ ነው”።

ከእግዚአብሔር ዘንድ ቅዱስ ፍራንችስኮስን የደረሰው ጥሪ ቤተክርስቲያኑን እንዲያድስ የሚል እንደነበር ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ቅዱስ ፍራንችስኮስ በዘመኑ የቤተክርስቲያን አቅም ውስን መሆኑን ቢገነዘብም ቅድሚያን የሰጠው እውነተኛ የወንጌል ሕይወትን እንደመረጠ ገልጸዋል ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የአሲዚው ቅዱስ ፍራንችስኮስ በዘመኑ ከሁሉም በላይ ወንጌልን በተግባር መኖር የቻለ መሆኑን ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ለውጥን ማምጣት የምትችለው እግዚአብሔርን ብቻ በማዳመጥ እንደሆነ አስገንዝበዋል። ቅዱስነታቸው ይህን ያስታወቁት ቅዳሜ ጠዋት መጋቢት 28 ቀን 2011 በቫቲካን ውስጥ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለተቀበሏቸው ፍራንቸስካዊያን ገዳማዊያት እና ገዳማዊያን እንዲሁም ምዕመናን ባሰሙት ንግግር ነው። የፍራንችስካዊ ተልዕኮ እንቅስቃሴ የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት ለማክበር ከጀርመን ወደ ሮም የመጡት በቁጥር 25 የሚሆኑ የእንቅስቃሴው አባላት ለቅዱስነታቸው ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል።  

ተልዕኮአችሁ ድሆችን እና ስደተኞችን ማገዝ ይሁን፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ በጀርመን ቦን ከተማ አቅራቢያ ፍራንችስካዊያኑ በማበርከት ላይ ለሚገኙት አገልግሎት አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው በንግግራቸው እንደገለጹት ገዳሚያዊያን እና ገዳማዊያት ከምዕመናን ጋር በመተጋገዝ፣ ሌሎች ምእመናኖችም እንዲተባበሩ በማድረግ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ የደሄዩት እና የተሰደዱት የወደ ፊት መልካም ተስፋ እንዲኖራቸው ለማድረግ የምታደርጉት ጥረት መልካም ነው ብለዋል።

የቅዱስ ፍራንችስኮስ ምሳሌ ሕያው ነው፣

ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ “ከእነዚህ ወንድሞች መካከል ለአንዱ ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደርጋችሁ ነው” ያለውን ያስታወሱ ቅዱስነታቸው፣ ፍራንችስካዊ ልኡካን ማሕበር የሚከተለው መንገድ ቅዱስ ፍራንችስኮስ የመረጠው የድህነት ሕይወት እና ከደሆች ጋር በመሆን ሕይወቱን በሙሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ አደራ በመስጠት ደስታ እና የእርሱን በረከት ያገኘበት መንገድ መሆኑን አስረድተዋል። የማዕከላቸው ዓላማ ይህ በመሆኑ በመላው ዓለም ውስጥ የቸርነት፣ የአንድነት እና የወንድማማችነት መንፈስ እንዲስፋፋ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።

ቤተክርስቲያን አቅሟ ውስን ቢሆንም የእግዚአብሔርን ጥሪ ማዳመጥ ያስፈልጋል፣

ከእግዚአብሔር ዘንድ ቅዱስ ፍራንችስኮስን የደረሰው ጥሪ ቤተክርስቲያኑን እንዲያድስ የሚል እንደነበር ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ቅዱስ ፍራንችስኮስ በዘመኑ የቤተክርስቲያን አቅም ውስን መሆኑን ቢገነዘብም ቅድሚያን የሰጠው እውነተኛ የወንጌል ሕይወት መኖር እንደነበር አስታውሰዋል። ዛሬም ቢሆን ቤተክርስቲያን የአቅም ውስንነት እንደሚታይባት ገልጸው በመስቀል ላይ የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑ እንድንደግፍ እና እንድናሳድግ ለእያንዳንዳችን ጥሪውን ያቀርብልናል ብለዋል። በቤተክርስቲያን ለውጥ ሊመጣ የሚችለው እርሱን በማዳመጥ፣ ሁሉን ለእርሱ አሳልፎ በመስጠት እና በመልካም ሥራዎቻችን ከእርሱ ጋር ስንተባበር ነው ብለዋል።

ዛሬ በሚያጋጥሙን ችግሮች ሳንሸነፍ ከወትሮ በበለጠ ራሳችንን ለአገልግሎት በማነሳሳት መጪው ጊዜ መልካም እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።  ዛሬ በሚያጋጥሙን ችግሮች ሳንሸነፍ ከወትሮ በበለጠ ራሳችንን ለአገልግሎት በማነሳሳት መጪው ጊዜ መልካም እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። የፍራንችስካዊያኑ የወንጌል ተልዕኮ ማዕከልም በተግባር እየገለጸ ባለው የሕይወት ምስክርነት ብዙ አስተዋጽኦን ሊያበረክት ይችላል ብለዋል። ቅዱስነታቸው በመጨረሻም አባላቱ አገልግሎታቸውን የጋራ ጥቅምን እና የተፈጥሮ ደህንነትን ባገናዘበ መልኩ እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
08 April 2019, 17:05