ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በስቅለተ ዐርብ ምሽት ያደርጉት የማጠቃለያ ጸሎት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በስቅለተ ዐርብ ምሽት ያደርጉት የማጠቃለያ ጸሎት 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በስቅለተ ዐርብ ምሽት ያደርጉት የማጠቃለያ ጸሎት

ጌታ ኢየሱስ ሆይ በዓለም ውስጥ የሚገኙትን መስቀሎች ሁሉ በአንተ መስቀል ውስጥ አስገብተን እንድንመለከት እርዳን፣

እለታዊ እንጀራ እና ፍቅር የተራቡ ሰዎችን መስቀል

ብቸኛ የሆኑ ሰዎችን እና በገዛ ልጆቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ችላ የተባሉ ሰዎችን መስቀል

ፍትህን እና ሰላምን የተጠሙ ሰዎችን መስቀል

የእምነት መጽናኛ የሌላቸው ሰዎችን መስቀል;

በእድሜ የተነሳ እና በብቸኝነት ምክንያት የኑሮ ጫና የበረከተባቸውን አረጋዊያንን መስቀል

በፖለቲካ ስሌቶች የተነሳ በተፈጠረው ፍርሀት ምክንያት እና ልባቸው በደነደነ ፖለቲከኞች ምክንያት ድንበር የተዘጋባቸው ስደተኞችን መስቀል

በንጽሕናቸው እና በየዋዕነታቸው ምክንያት ጥቃት የደረሰባቸውን ትንንሽ የሆኑ ሰዎች መስቀል

እርግጠኛ ባልሆኑበት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ገብተው እና በተጨማሪም በአሁኑ ዓለማችን ውስጥ ባለው የጨለማ ባህር ውስጥ ገብተው የሚንከራተቱ የሰው ልጆችን መስቀል

በክህደት፣ በመጥፎ መንፈስ አማላይነት ወይም በግድዬለሽ መንፈስ እና በራስ ወዳድነት መንፈስ እንዲለያዩ የተደርጉትን ቤተሰቦች መስቀል

ያለመታከት የአንተን ብርሃን በዓለም ውስጥ እንዲበራ ለማድረግ በሚሰሩበት ወቅት ተቀባይነት ያጡትን፣ የተሳለቁባቸውን እና ያዋረዱዋቸውን መንፈሳዊ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎችን መስቀል

የአንተን መንገድ በመገንባት ላይ በነበሩበት ሂደት ውስጥ መጀመሪያ የተቀበሉትን ፍቅር በመዘንጋታቸው የተነሳ ከፍተኛ ጫና ውስጥ የገቡትን ሰዎች መስቀል

የእንተን ቃል በመከተል እና በቃልህ መሠረት ለመኖር በሚሞክሩበት ወቅት በቤተሰቦቻቸው፣ በዘመዶቻቸው እና በእኩዮቻቸው ሳይቀር የተገለሉትን ልጆችህን መስቀል

በድክመቶቻችን፣ በግብዝነታችን፣ በክህደታችን፣ በኋጥያቶቻችን እና ብዙ በተግባር ላይ ባላዋልናቸው ቃልኪዳኖቻችን የተነሳ የተሸከምነውን መስቀሎቻችንን

ለቅዱስ ወንጌል ታማኝ የሆነችሁን፣ የአንተን ፍቅር በተጠመቁ ሰዎች መካከል ለማስረጽ እየደከመች የምትገኘውን ታማኝ የሆነችሁን የአንተን ቤተ ክርስቲያን መስቀል

የአንተ ሙሽራ የሆነችውና ቀጣይነት ባለው መልኩ ከውስጥ ሆነ ከውጪ እየተወጋች ያለችሁን የአንተን ቤተ ክርስቲያን መስቀል

በራስ ወዳድነት እና በስግብግብነት መንፈስ እንዲሁም በስልጣን እና በከፍተኛ ቅናት የተነሳ በመታወራቸው ዓይኖቻቸው እያየ እየወደመች የምትገኘውን የጋራ መኖሪያ የሆነችሁን የምድራችን መስቀል ወደ አንተ እናቀርባለን።

ጌታ ኢየሱስ ሆይ የትንሣኤ ተስፋ እና በእያንዳንዱም ክፋትና ሞት ላይ የተቀናጀኸውን የመጨረሻውን ድል አሳየን። አሜን!

20 April 2019, 17:24