ፈልግ

የራባት አገረ ስብከት ካቴድራል ሞሮኮ የራባት አገረ ስብከት ካቴድራል ሞሮኮ  

የራባት አገረ ስብከት ታሪካዊ ዳራ በአጭሩ

የሞሮኮ ዋና ከተማ የሆነችው ራባት አገረ ስብከት የተቋቋመው እ.አ.አ በ1923 ዓ.ም እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህ አገረ ስብከት 400,000 ሺ እስኩዌር ኪሎሜሮችን የሚሸፍን ሲሆን በውስጧ 20 ሺ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ይገኛሉ። በራባት አገረ ስብከት ውስጥ 28 ቁምስናዎች፣ 33 የአገረ ስብከት ካህናት፣ 22 የተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት እና ገዳማት ካህናት፣ 101 የተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት እና ገዳማት ደናግላን፣ 36 የትምህርት መስጫ ተቋማት፣ 1 የእርዳታ መስጫ ተቋም የሚገኙ ሲሆን በያዝነው የአውሮፓዊያኑ 2019 ዓ.ም ብቻ 89 ሰዎች ምስጢረ ጥምቀት መቀበላቸውን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

29 March 2019, 16:38