ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሞሮኮ የሚያደርጉት 28ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከመጋቢት 21-22/2011 ዓ.ም 28ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በሞሮኮ ለማድረግ ወደ እዚያው እንደ ሚያቀኑ ይታወቃል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በስድስት አመት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው ከጣሊያን ውጭ አሁን በሞሮኮ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ጨምሮ 28 ሐዋርያዊ ጉብኝቶችን ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በእነዚህም ሐዋርያዊ ጉብኝቶች በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ከሚገኙት ከኬኒያ፣ ከሁጋንዳ እና ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ አንስቶ በኩባ፣ በአሜሪካ፣ በላቲን አመሪካ በምስራቅ አውሮፓ እና በኤሽያ አህጉር በመጓዝ የሰላም እና የአንድነት መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

900 የካቶሊክ ምዕመናን ብቻ የሚገኙባትን እና አብዛኛው ሕዝብ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍል የሚኖሩባትን አዛረበጃንን ጨምሮ አብዛኛው የማኅበረሰብ ክፍል የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ሕዝቦች የሚኖሩባቸውን ባንግላዲሽ እና ማያን ማር (የቀድሞ ስሟ በርማ) ድረስ በመሄድ የሰላም እና የአንድነት መልእክታቸውን ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አሁን በሞሮኮ የሚያደርጉት 28ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሞሮኮ ያደረጉት ሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት ሲሆን ከዚህ ቀደም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለኛ እንደ የጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በነሐሴ 19/2985 ዓ.ም በዚያው በሞሮኮ በሚገኘው የካዛ ብላንካ እስቴዲዬም ለተገኙ በርካታ የክርስታና እና የእስልምና እምነት ተከታይ ወጣቶች ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል።

ለዚህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሞሮኮ ለሚያደርጉት 28ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት የተዘጋጀው የጉዞ አርማ በአንድ በቀይ ቀለም በተሰራ የጨረቃ ቅርጽ ውስጥ አንድ በቢጫ እና በአረንጓዴ ቀለሞች የተሰራ መስቀል በውስጡ የሚገኝ አርማ ሲሆን በአጠቃላይ ይህ አርማ የጨረቃ እና የመስቀል ምልክት አጣምሮ የያዘ አርማ ሲሆን ጨረቃው የእስልምና እምነት ተከታዮችን መስቀሉ ደግሞ የክርስትና እምነት ተወካዮችን የሚወክል ሲሆን አጠቃላይ ትርጉሙ ደግሞ በእስልምና እና በክርስትና እምነት ተከታዮች መካከል የሚደርገውን የጋራ ውይይት የሚያመልክት አርማ ነው። በአርማው ላይ የሚታየው አረንጓዴ እና ቀይ ቀለም ሞሮኮን የሚወክል ሲሆን ቢጫ እና ነጭ ቀልማት ደግሞ የቅድስት መንበርን ወይም ቫቲካንን የሚወክል ቀለም ነው።

29 March 2019, 16:09