ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ወደ ሞሮኮ ከማቅናታቸው በፊት ለአገሪቷ ሕዝብ መልእክት አስተላለፉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 21-22/2011 ዓ.ም ድረስ 28ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ሞሮኮ ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ራባት እንደ ሚያቀኑ ይታወቃል። ቅዱስነታቸው ይህንን በሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት “የእግዚኣብሔር አገልጋዮች አገልጋይ” በሚል መሪ ቃል የሚያደርጉትን 28ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት ከመጀመራቸው በፊት በመጋቢት 19/2011 ዓ.ም ለአገሪቷ ሕዝብ በቪዲዮ መልእክት ማስተላለፋቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱሰንታቸው በመልእክታቸው እንደ ገለጹት ወደ ሞሮኮ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞ “በወንድማማችነት እና በሰላም መንፈስ” የሚያደርጉት መንፈሳዊ ጉዞ እንደ ሆነ ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሞሮኮ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመጋቢት 21/2011 ዓ.ም እንደ ሚጀምሩ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእዚያው በሚኖራቸው ቆይታ የሞሮኮ ሱልጣን ከሆኑት ሙሃመድ 6ኛ እና የተለያዩ የሞሮኮ ሕዝብ ተወካዮች፣ ባለስልጣናት፣ የሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የተለያዩ አገራት ልዑካን ተወካዮች በተገኙበት የሞሮኮ ሱልጣን በሆኑት ሙሃመድ 6ኛ ንግግር ካደረጉ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የዚህ የ28ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት የመጀመሪያውን ንግግር እንደ ሚያደርጉ የሚጠብቅ ሲሆን ከዚያም በመቀጠል በሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት ውስጥ በሚገኘው እና ካሪታስ በመባል በሚታወቀው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የእርዳታ መስጫ ተቋም ውስጥ የተለያዩ አገራት ስደተኞች በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴ እንደ ሚያሳርጉ ይጠበቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት ወደ ሞሮኮ የሚጓዙት በወንድማማችነት እና በሰላም መንፈስ መንፈሳዊ ንግደት ለማድረግ እንደ ሆነ ጭመረው የገልጹ ሲሆን ይህም አሁን ዓለማችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስፈልገው ስጦታ ነው ብለዋል።

28 March 2019, 16:30