ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከብስራተ ገብርኤል ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 15/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ በመቀጠል ዘወትር በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት እና በዕለተ ሰንበት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከሚደግሙት፣ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛ የሆነውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለውን የመልኣኩ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ከባለፈው ከየካቲት 27 ጀምሮ በሀገሪቱ በሰፊው የሚሰተዋለውን ከባድ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ለመፍታት ወሳኝ ንግግሮች በኒካራጓ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው በአገሪቷ የሚታየው ቀውስ በሰላም ይፈታ ዘንድ እኛም በጸሎት ልንደግፋቸው የገባል ብለዋል።

በቅርቡ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በተከሰተው የሱናሚ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ፣ ለተጎዱ ለተፈናቀሉ ሰዎች ጸሎት ማድረግ እንደ ሚገባ ጥሪ ያቀረቡት ቅዱሰንታቸው በተለይም ደግሞ በናይጄሪያ እና በማሊ በዚህ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች ጸሎት ማድረግ ይገባል ብለዋል። ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በእለቱ የተገኙትን ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ግብኚዎች ሰላምታን አቅርበው እና አመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬያቸወን ሰጥተው እንደ ተለመደው እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ ካሉ በኋላ ቅዱስበታቸው መሰናበታቸውን ከስፍራው ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

24 March 2019, 11:23