ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከመልአከ እግዚ/ር ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልእክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየካቲት 24/2011 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበስቡ ምዕመናን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ካደርጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በመቀጠል  ዘወትር በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት እና በዕለተ ሰንበት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከሚደግሙት፣ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛ የሆነውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለውን የመልኣኩ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት በወቅቱ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተገኙትን ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያ እና የአገር ጎብኝዎች ሰላምታ ማቅረባቸው ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “በደስታ የተሞላ ሕይወት ለመኖር መሞከር ይኖርባችኋል” ያሉት ቅዱስነታቸው “የጌታን ቸርነትና ይቅር ባይነት በትህትና መንፈስ ልትመሰክሩ ይገባል” ካሉ በኋላ መልካም ቀን ይሆንላቸው ዘንድ ተመኝተው ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው፣ ሰላምታን አቅርበው እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

03 March 2019, 14:52