ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ወደ ራባት ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ እንደ ደረሱ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ወደ ራባት ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ እንደ ደረሱ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሞሮኮ የሚያደርጉትን 28ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ጀመሩ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሞሮኮ የሚያደርጉትን 28ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ጀመሩ

እንደ ተለመደው ቅዱስነታቸው ማንኛውንም ሐዋሪያዊ ጉብኝት ከመጀመራቸው በፊት እና ማነኛውንም ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሮም ከተማ በሚመለሱበት ወቅት በሮም ከተማ እንብርት ላይ በሚገኘው በማሪያም ስም ከተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በአውሮፓ አህጉር በትልቅነቱ እና በጥንታዊነቱ በሚታወቀው ሳንታ ማሪያ ማጆሬ በመባል በሚታወቀው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተገኝተው፣ በዚያው በሳናታ ማርያ ማጆሬ ባዚሊካ ውስጥ በሚገኘው ባላቲን ቋንቋ “Salus Populi Romani” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም የሮም ከተማ ሕዝቦች አዳኝ ወይም ጠባቂ በመባል የሚታወቀው እና በአብዛኞቹ  የሮም ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሕጻኑን ኢየሱስን በእጆቹዋ ላይ አቅፋ መያዙዋን የሚያሳየው ምስል ስር በመገኘት ይህ በሞሮኮ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ 28ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት የተሳካ ይሆን ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትረዳቸው ዘንድ የመማጸኛ ጸሎት  ማቀረባቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ባሳንታ ማሪያ ማጆሬ ባዚሊካ ተገኝተው ጸሎት ካደርሱ ቡኃላ በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 6፡45 ላይ በሮም ከተማ ከሚገኘው እና በ15ኛው ክፍለ ዘመን በኖረው የጌታን የመጨረሻ እራት እና ሞናሊዛን በመሳሰሉ ድንቅ በሆኑ ስዕሎቹ በሚታወቀው በሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ ስም ከተሰየመው ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማርፊያ በመነሳት ጉዞዋቸውን ጀምረው 1901 ኪሎ መትሮችን በአየር ላይ ተጉዘው የጣሊያንን፣ የፈረንሳይን፣ የእስፔንን እና የሞሮኮን የአየር በረራ ክልል አቋርጠው የ03፡15 ደቂቃ ጉዞ ካደረጉ ቡኃላ በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ በ10 ሰዓት ላይ የሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት በሰላም መድረሳቸው ተገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ራባት ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ እንደ ደረሱ የአገሪቷ ንጉሥ በሆኑት ሞሃመድ 6ኛ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ባሕላዊ ልብስ የለበሱ ሁለት ሕጻናት ለቅዱስነታቸው የአበባ ጉንጉን በስጦታ መልክ አቅርበዋል። ከአቀባበሉ በመቀጠል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሞሮኮ ሱልጣን በሆኑት ሙሃመድ 6ኛ እና የራባት አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሆኑት ክሪስቶባል ሎፔዝ ሮሜሮ ታጅበው ወደ ሞሮኮ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተወስደዋል።

በመቀጠል በእዛው በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ውስጥ የተለያዩ የሞሮኮ ሕዝብ ተወካዮች፣ ባለስልጣናት፣ የሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የተለያዩ አገራት ልዑካን ተወካዮች በተገኙበት የሞሮኮ ሱልጣን በሆኑት ሙሃመድ 6ኛ ንግግር ካደረጉ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የዚህ የ28ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት የመጀመሪያውን ንግግር በእዚያው እድርገዋል።

29 March 2019, 16:33