ፈልግ

በኢራን የደረሰው የጎርፍ አደጋ በኢራን የደረሰው የጎርፍ አደጋ  

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሐዘን መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኢራን በደረሰው የጎርፍ አደጋ ሕይወታቸውን ባጡት እና በቆሰሉት ሰዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል። የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የቅዱስነታቸውን የሐዘን መግለጫ መልዕክት ከተቀበሉ በኋላ ፊርማቸውን በማኖር መላካቸውን አስታውቀዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሞት አደጋ የተለዩትን ሰዎች በሙሉ በጸሎታቸው ማስታወሳቸውን፣ በከባድ ሐዘን ላይ ለሚገኙት ጽናትን የተመኙላቸው መሆኑን ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን ገልጸው በነፍስ አድን ተግባር ላይ የተሰማሩትን እና መላውን የኢራን ሕዝብ ሁሉን ለሚችል እግዚአብሔር አደራ መስጠታቸውን አስታውቀዋል።

27 March 2019, 15:12