ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡትን በጸሎቴ አስታውሳቸዋለሁ”። ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡትን በጸሎቴ አስታውሳቸዋለሁ”። 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በኢትዮጵያ በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጹ።

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ በደረሰው አደጋ ሕይወታቸውን ያጡትን በሙሉ በጸሎታቸው አስታውሰው የተሰማቸውንም ሐዘን በመልዕክታቸው ገለጸዋል። የአደጋው ሰለባ የሆኑ ሰዎች ነፍሳትን በሙሉ እግዚአብሔር በምሕረቱ እንዲቀበል በማለት በጸሎታቸው አስታውሰዋል። በጥልቅ ሐዘን እና በለቅሶ ላይ ለሚገኙት ቤተሰቦቻቸው በሙሉ መጽናናትን ተመኝተውላቸዋል።  

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን የሐዘን መግለጫ መልዕክት ተቀብለው መላካቸው ታውቋል።

11 March 2019, 17:56