ፈልግ

VATICAN-POPE-ANGELUS VATICAN-POPE-ANGELUS 

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ መልእክት አስተላልፈዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ትናንት እሑድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበስቡ ምዕመናን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ካደርጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በመቀጠል በስፍራው ለተገኙት በሙሉ ንግግር አድርገውላቸዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ ቅዳሜ የካቲት 30 ቀን 2011 ዓ. ም. በስፔን አገር ሰማዕትነታቸው የታወጀላቸውን አንጀሎ ኩርታስን እና 8 የዘርዓ ክህነት ተማሪዎችን አስታውሰው በእምነታቸው ምክንያት የተገደሉት እነዚህ የዘርዓ ክህነት ተማሪዎች እግዚአብሔርን ከልባቸው እንደወደዱት ገልጸው ኢየሱስ ክርስቶስን መከራ እና ስቃይ መካፈል የፈለጉ ናቸው ብለዋል። ይህ ለሌሎች የዘርዓ ክህነት ተማሪዎች፣ ካህናት እና ጳጳሳት የግዚአብሔርን ሕዝብ በቸርነት እና በታማኝነት ለማገልገል የገቡትን ቃል እንዲጠብቁ በማድረግ መልካም ምስክርነት እንዲሆናቸው ያስፈልጋል ብለዋል።

በመቀጠልም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ከእርሳቸው ጋር በመሆን በዕኩለ ቀኑ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ላይ ለተገኙት በሙሉ ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። በርካታ ቤተሰቦችን፣ የቁምስናዎች መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ማሕበራት አባላትን፣ ከኢጣሊያ እና ከሌሎች አገሮች ለመጡ ነጋዲያንና ለተለያዩ ማሕበራት አባላት በሙሉ ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። ከስፔን ካስትሮ ኡርዲያለስ ለመጡት ተማሪዎች፣ ከፖላንድ ቫርሳቪያ እና ከኢጣሊያ ስታቢይ እና ፖርቻ ለመጡት ምእመናን በሙሉ ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። ከስዊዘርላንድ ለመጡት መዘምራን፣ ከሰሜን ኢጣሊያ ከሚላኖ ለመጡት ታዳጊ ሕጻናት፣ የትምህርተ ክርስቶስ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ከቬሮና እና ከጀኖቫ ለመጡት ታዳጊ ሕጻናት ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። 

በቅርቡ የተጀመረው የጾም፣ የጸሎት እና የቸርነት ጊዜ ፍሬያማ እንዲሆንላቸው በማለት ለምእመናኑ በሙሉ መልካምን ተመኝተው በአደባባዩ የነበሩ ምዕመናን በሙሉ፣ ከእርሳቸው ጋር የሱባኤን ጊዜን ለመጀመር የተዘጋጁ፣ በቅድስት መንበር የካርዲናሎች ጉባኤ አባላትን በጸሎታቸው እንዲያስታውሷቸው አደራ ካሉ በኋላ በደባባዩ ለነበሩት በሙሉ መልካም እሁድን እና መልካም ምሳን በመመኘት ንግግራቸውን አጠቃልለዋል። 

11 March 2019, 17:36