ፈልግ

አዲሱ ቃለ ምዕዳናቸው እንዲታተም በፊርማ ሲያረጋግጡ አዲሱ ቃለ ምዕዳናቸው እንዲታተም በፊርማ ሲያረጋግጡ  

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በሎሬቶ “ሕያው ክርስቶስ” የተሰኘ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸውን ይፋ አደረጉ።

ከመስከረም 23 ቀን እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ. ም. ድረስ በቫቲካን ከተማ የተካሄደው 15ኛ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ለወጣቶች የጻፉትን መልዕክት ከተመለከቱ በኋላ በፊርማቸው በማጽደቃቸው “ሕያው ክርስቶስ” የተሰኘ አዲስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸው ታትሞ ከመጋቢት 24 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ ለዓለም ወጣቶች በሙሉ ይፋ እንደሚሆን ከቫቲካን የዜና አገልግሎት የወጣ ዜና ገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዛሬ መጋቢት 16 ቀን 2011 ዓ. ም. ወደ ሎሬቶ ከተማ ሲደርሱ በርካታ ምዕመናን ደማቅ አቀባበል ማድረጋቸው ከሥፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል። የሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ዋና ዓላማ በላቲን የሥርዓተ አምልኮ የቀን አቆጣጠር በምትከተል ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሰራት በሚታወስበት እለት በሎሬቶ በሚገኘው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴን ለማሳረግ፣ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ወጣቶችን አስመልክቶ በመስከረም ወር 2011 ዓ. ም. በቫቲካን ከተማ ካደረገው 15ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በኋላ ያወጣውን የድህረ ጉባኤ መልዕክት በፊርማቸው ሊያጸድቁት፣ ወደ ሎሬቶ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የንግደት ስፍራ ከመጡት ሕሙማን እና ምዕመናን ጋር ለመገናኘት እንዲሁም የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አብሮአቸው ለመድገም መሆኑን የሐዋርያዊ ጉዞአቸው መርሃ ግብር ይገልጻል።

በሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ወቅት ከኢጣሊያ ክፍላተ ሀገራት ከመጡ ወደ 800 ከሚጠጉ ወጣቶች ጋር መገናኘታቸው ታውቋል። ወጣቶቹ በየዓመቱ ወደ ሎሬቶ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ የሚደረገውን መንፈሳዊ ጉዞን የተካፈሉ መሆናቸው ታውቋል።      

ቅዱስነታቸው ለወጣቶች ሰላምታቸውን ካቀረቡላቸው በኋላ በሥፍራው የተገኙትን ሕሙማን ጎብኝተው ሰላምታን ተለዋውጠዋል። ቅዱስነታቸው በዕለቱ ካከናወኗቸው ተግባራት መካከል የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ዘንድሮ በቫቲካን ከተማ ወጣቶችን አስመልክቶ ካደረገው 15ኛው ጠቅላላ ጉባኤ በኋላ ያወጡትን የድህረ ስብሰባ መልዕክትን በፊርማቸው ማጽደቃቸው ታውቋል።

ከመስከረም 23 ቀን እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ. ም. ድረስ በቫቲካን ከተማ የተካሄደው 15ኛ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ለወጣቶች የጻፉትን መልዕክት በፊርማቸው አጽድቀው “ሕያው ክርስቶስ” የተሰኘ አዲስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸው ከመጋቢት 24 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ ለዓለም ወጣቶች በሙሉ ይፋ እንደሚሆን ከቫቲካን የዜና አገልግሎት የወጣ ዜና ገልጿል።

25 March 2019, 18:24