ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሕግ ባለሙያዎች የሰው ልጅ ሰብዓዊ መብት እንዲጠበቅ ማድረግ ይኖርባቸዋል

የካቲት 06/2011 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከጣሊያን የሕግ ባለሙያዎች ማሕበር ተወካዮች ጋር በቫቲካን መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ይህ የጣሊያን የሕግ ባለሙያዎች ማሕበር ከተቋቋመ 110 ዓመት እንደ ሆነው ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል። በግንኙነቱ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት ፍትህን ርኅራኄ በተሞላው መልኩ ማስከበር እንደ ሚገባቸው ገልጸው “እናንተ የሕግ ባለሙያዎች ከሰው ልጅ ሕይወት መጀመሪያ አንስቶ እስከ የሰው ልጅ ሕይወት ማብቂያ ድረስ ያሉትን ዋና ዋና በጣም አስፈላጊ ወሳኝ የሆኑ የሰው ልጆች የሕይወት አውድ ከግምት ባስገባ መልኩ ፍትህ እንዲረጋገጥ ማድረግ ይኖርባችኋል” ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“ፍትህ ምንድን ነው? የትኞቹን ግቦች መምታት ይኖርበታል? ዛሬ የሕግ ባለሙያዎችን እየተፈታተኑ የሚገኙ ሁኔታዎች ምንድናቸው?” በማለት ለጣሊያን የሕግ ባለሙያ ማኅበር አባላት ተወካዮች ጥያቄን በማቅረብ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በአንድ ወቅት እውነት ማለት ከተጭበረበሩ ሐሳቦች ነጻ የሆነ ነገር ተደርጎ ይቆጠር እንደ ነበረ ገልጸው ነገር ግን እውነት ከእውነቱ በላይ ከእውነታ የላቀውን ነገር ማፅናት ማለት ሊሆን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

የሕግ ባለሙያዎች ተግባር

የጣሊያን የሕግ ባለሙያ ማኅበር ዋነኛው ዓላማ እና ተግባር ሊሆን የሚገባው ዲሞክራሲያዊ የሆኑ ሕግጋትን ተግባራዊ መሆናቸውን መከታተል እና ሕገ-መንግሥታዊ እሴቶችን መደገፍ እና ለጋራ ጥቅም አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ማስቻል እንደ ሆነ አክለው የገለጹት ቅዱስነታቸው “ትክክለኛውን እውነታ" በትክክለኛ ጥናት ላይ በመመርኮዝ እና" ቀጣይነት ያለው የማሻሻያ ጥረቶችን በማድረግ ትክክለኛ እና ትክክለኛነት እንዲረጋገጥ መጣር እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ፍትህ በጎነት ነው

ለማኅበራዊ ሕይወት አዲስ የሆነ ጣዕም ለመስጠት "በሁሉም የኑሮ መስኮች ላይ አስፈላጊ የሆነውን እና በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን ፍትህ ማስፈን እና ማረጋገጥ እንደ ሚገብ የገለጹት ቅዱስነታቸው የፍልስፍና ባህል እንደሚለው ፍትህ ማለት "የመለኮት ባህርይን መላበስ ማለት" እንደ ሆነ ገልጸው ይህም "ትክክለኛ አቅጣጫን ያመለክታል" ካሉ በኋላ ይህም ለማኅበርሰቡ ድጋፍ እና ማዕከላዊ የሆነ ነጥብ ነው ብለዋል።

ፍትህ እና ሰላም

መሰረታዊ የሆነ የፍትህ ድጋፍ የሌለበት ማኅበረሰብ “ልክ አንድ ጊዜ ከተዘጋ በኋላ ተመልሶ እንደ ማይከፈት በር ሁሉም ዓይነት ማኅበራዊ ሕይወት የተዘጋ ይሆናል፣ ወይም ደግሞ በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለው ጭቅጭቅ እና መሰነጣጠቅ ይጨምራል፣ ያልተገባ ዓይነት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ በመቀጠል ማኅበረሰቡን እንደ ሚረብሽ የገለጹት ቅዱስነታቸው “በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ አዎንታዊ ገጽታ ያላቸው ኃይሎች እና አካላት በሙሉ ፍትህ ይረጋገጥ ዘንድ የራሳቸውን አስተዋጾ ማድረግ እንደ ሚገባቸው ገልጸው ምክንያቱም ይህ ሰላምን ለማረጋገጥ ዓይነተኛ የሆነ ዜዴ ነው ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

እናንተ የህግ ባለሙያዎች፣ ፍትህን ማስፈን በተመለከተ እጅግ ልዩ በሆነ መንገድ ይህ ጉዳይ በአደራ ለእናንተ ተሰጥቶቱዋችኋል፣ ምክንያቱም ይህ አደራ የተሰጣችሁ እናንተ ይህንን ጉዳይ እንድታስፈጽሙት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ፍትህን የተመለከቱ ጉዳዮችን ያለምንም ድካም ለሁሉም ሰዎች የማስተዋወቅ ኃላፊነት ጭምር ተሰጥቱዋችኋል፣ ይህ አንድ ጊዜ ለእናንተ ተስጥቶ ያበቃ ትዕዛዝ ሳይሆን ነገር ግን በእየቀኑ በሕይወታችሁ ተግባራዊ ልታደርጉት የሚገባ ኃላፊነት ነው”።

የህግ መስመሮች

የሕግ ባለሙያዎች በሚያከናውኑዋቸው ተግባሮች የተነሳ "አንድ ሺህ ችግሮች ይገጥማቸዋል"፣ “መሰረታዊ የሆኑ ጉዳዮችን ለማስፈጸም የሚወጣው ውጪ ውድ ከመሆኑ የተነሳ በቂ የሆነ የሕግ ባለሙያ ለመቅጠር አስቸጋሪ በመሆኑ የተነሳ ጭምር” በእለታዊ ተግባሮቻቸው ውስጥ እንቅፋት ይገጥማቸዋል። ሕጋዊ የሆኑ ሂደቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተወሳሰቡ ከመምጣታቸው የተነሳ፣ ሕጋዊ የሆኑ ጉዳዮች በቁጥር እጅግ በጣም እያሻቀቡ በመምጣታቸው ጭምር፣ እንዲሁም ቀደም ሲል በነበሩ እና እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ያሉ ሕጎች እርስ በእራሳቸው ከመጣረዛቸው የተነሳ፣ የአንድ አገር ሕግ ከሌላ አለም አቅፍ ሕግ ጋር በአንድ አንድ ሁኔታዎች ላይ የሚቃረኑ በመሆናቸው የተነሳ ሕጋዊ የሆኑ መስመሮች ላይ የሚፈጥረው ጫና ከፍተኛ እንደ ሆነ” ቅዱስነታቸው እንደ ሚረዱ ጨምረው ገልጸዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. .

ሕጋዊ የሆኑ መስመሮች በሕይወት ጅማሬ እና በሕይወት መጨረሻ ላይ ያሉ ጉዳዮችን በተመለከተ፣ ለምሳሌም የቤተሰብ መብት እና ለስደተኞች ሊደረግ ስለሚገባ እንክብካቤ የሚመለከቱ አስፈላጊ የሆኑ ጥያቄዎች ውስብስብ እውነታዎች በመሆናቸው የተነሳ የህግ ማዕቀፍ ውስጥ መግባት ይኖርባቸዋል። እነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች ፍርድ ቤቱ ወይም የሕግ ባለሙያው ከተለመደው ተግባሩ ውጭ የሚሄድ ሃላፊነት እንዲኖረው ይጠይቃል፣ እናም እሱ በእነዚህ ክስተቶች ውስጥ እንዲገባ በማድረግ እና እነዚህን ሁኔታዎች በላቀ መልኩ ማከናውን እንዳለበት ግድ ስለሚለው ጉዳዮን ይበልጥ ለሕግ ባለሙያው ከባድ እንዲሆን ያደርገዋል።

የሕግ ባለሙያዎች አብነት ያለው ተግባር ማከናወን ይኖርባቸዋል

የሕግ ባለሙያዎች "እንዲሁ የሥራ አስፈጻሚዎች ብቻ ሳይሆኑ ነገር ግን ከዚህ እጅግ የሚልቁ ናቸው፣ በሁሉም የዜግነት ደረጃዎች በተለይም በጣም ወጣት ለሆነው የማኅበርሰብ ክፍል አብነት ሊሆኑ ይገባቸዋል፣ ሕግ ሁሉንም ሰዎች እና ዜጎችን ያቀፈ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፣ ትንሽ ከሚባለው የማኅበረሰብ ክፍል ጀምሮ እስከ ትልቁ ድረስ ለሁሉም ተደራሽ በመሆን ሕግ ሁሉን አቀፍ መሆኑን በማረጋገጥ መልካም አብነት ማሳየት ይኖርባቸዋል” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

16 February 2019, 10:12