ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በየካቲት 03/2011 ዓ.ም ያስተላለፉት መልእክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየካቲ 03/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው አስተንትኖ ካደርጉ በኋላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማርያምን አበሰራት” የሚለውን የብስራተ ገብሬል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ እንደ ተለመደው ለዓለም ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት ከሁለት ቀናት በፊት የቅድስት ባኪታ አመታዊ በዓል በተከበረበት ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመቃወም የሚዘከረው ዓለም አቀፍ ቀን ታስቦ መዋሉን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ሁላችምን የዝህን ዓይነቱ ሕገወጠ የሰውች ዝውውር እንዲያበቃ የበኩላችንን ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊ የሆነ፣ አሁን ባለንበት ዘመናዊ ዓለም ውስጥ እየተከሰተ የሚገኝ ዘመናዊ የባርነት ቀንበር እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው በተለያየ መልኩ እና ሁኔታ እነዚህን አስቃቂ የሆኑ ተግባራትን በመዋጋት ላይ የምትገኙትን ሰዎች ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል። በተለይም የዚህ ጉዳይ ቀጥተኛ ተጠቂ ለሆናችሁ ለወጣቶች ይህንን ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው ይህ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የሚያስከትለውን መዘዝ መርማራችሁ ማወቅ ይኖርባችኋል፣ ብለዋል።
 

11 February 2019, 15:12