ፈልግ

Pope Francis' Angelus Pope Francis' Angelus 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከመላከ እግዚ/ር ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልእክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየካቲ 10/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው አስተንትኖ ካደርጉ በኋላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማርያምን አበሰራት” የሚለውን የብስራተ ገብሬል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ እንደ ተለመደው ለዓለም ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት ከሚቀጥለው ሐሙስ የካቲት 14-17/2011 ዓ.ም ድረስ በታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚድረሰውን የተለያየ ጥቃት በማስወገድ ለታዳጊ ወጣቶች ጥበቃ ማደረግ ይገባል በሚል ጭብጥ ዙሪያ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተውጣጡ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንቶች በቫቲካን በመገኘት ስብሰባ እንደ ሚያደርጉ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ይህ ስብሰባ የታለመለትን ግብ እንዲመታ እና የተሰጠንን ሐዋርያዊ ተግባር በኃላፊነት መወጣት እንችል ዘንድ በጸሎታችሁ ከእኛ ጋር እንድትሆኑ አደራ እላለሁ ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በዚያው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተገኙትን እና ከተለያዩ አገራት የተውጣጡትን መንፈሳዊ ነጋዲያን አመስግነው እና ሰላምታ አቅርበው እንደ ተለመደው እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳተረሱ ካሉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው መሰናበታቸውን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

18 February 2019, 16:09