ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የእምነት ተቋማት መካከል የሚደረግ ውይይት ለሰላም መረጋገጥ ወሳኝ ነው!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወይም እንደ አስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ እርሳቸው የሚያደርጉትን ሳምንታዊ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አሰተምህሮ ለመከታተል ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። 

በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ማለትም በጥር 29/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች ዘወትር ረቡዕ እለት በሚያደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አሰተምህሮ ፈንታ በቅርቡ “ሰብዓዊ ወንድማማችነት” በሚል መሪ ቃል ከጥር 26-28/2011 ዓ.ም በተባበሩት የአረብ ኤምሬትስ አገር በሆነችው በአቡ ዳቢ ተካሄዶ በነበረው ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሐይማኖት መሪዎች ስብሰባ ላይ ለመካፈል ወደ እዚያው አቅንተው 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በተሳካ መልኩ ፈጽመው ወደ ቫቲካን በሰላም መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው ዘወትር ረቡዕ እለት በሚያደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ፈንታ ዛሬ ያደረጉት ንግግር ይህንን በቅርቡ ያጠናቀቁትን 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በተመለከተ መናገራቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በወቅቱም ቅዱስነታቸው “በክርስትናና እስልምና የእምነት ተቋማት መካከል የሚደረጉ ውይይቶች ለዓለማችን ሰላም መረጋገጥ ወሳኝ ነው!” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዛሬው እለት ማለትም በጥር 29/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ በቅርቡ የተጠናቀቀውን 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አስመልክተው ያደርጉትን ንግግር ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!

ባለፉት ቀናት ውስጥ በተባበሩት የአረብ ኤምሬትስ አገር በሆነችው በአቡ ዳቢ ያደረኩትን ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቅቄ ተመልሻለሁ። ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝት አጭር የነበረ፣ ነገር ግን በጣም አስፈላጊ የሆነ ጉዞ የነበረ ሲሆን እ.አ.አ 2017 ዓ.ም በግብፅ በታላቁ በአል-አዝሃር ታላቁ መስጊድ የነበረንን ቆይታ ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ በክርስትና እና በእስልምና የእመንት ተቋማት መካከል በዓለም ውስጥ ሰላምን ለማረጋገጥ የተሰጠንን ተልዕኮ “በሰብዓዊ ወንድማማችነት” መንፈስ ውይይት በማድረግ ስምምነት ላይ በመድረሳችን በታሪክ ውስጥ ቁርጠኛ የሆነ አዲስ ምዕራፍ ከፍተናል።

ለመጀምሪያ ጊዜ አንድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ አረብ ባሕረ ስላጤ ያደረጉት ጉብኝት ነበር። ለመንፈስዊ ጥበቃ ምስጋና ይግባውና የአዚዚው ቅዱስ ፍራንቸስኮስ እና ሱልጣን ኣል ማሊክ ኣል ካሊም ከተገናኙ የዛሬ 800 ዓመት ገደማ በኋላ ፍራንቸስኮስ በመባል የሚጠራ አንድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ያደረጉት ጉብኝት ነው። በዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝ ወቅት ስለ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ በጣም ብዙ ጊዜ አስቤ ነበር፡ በነበረኝ የጉብኝት ሂደት ውስጥ ቅዱስ ወንጌልን በልቤ ውስጥ አድርጌ እንዲይዝ በማድረግ የኢየሱስን ፍቅር በልቤ ውስጥ ጠብቄ እንድጓዝ ረድቶኛል፣ በልቤ ውስጥ የክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል ነበረ፣ ለሁሉም የእግዚኣብሔር ልጆች በተለይም ደግሞ ለድሆች ፣ የኢፍታዊ ተግባራት፣ የጦርነት፣ የስቃይ ወዘተ ሰለባ ለሆኑ ሰዎች ጸልዬላቸው ነበር፣ ይህንንም ያደረኩት በክርስትናና በእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል የሚደርገው ውይይት ለዛሬው ዓለም ሰላም ወሳኝ በመሆኑ የተነሳ ነው።

የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ንጉሥ እና ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንት እና ሁሉም ባለስልጣኖች በታላቅ አድናቆት ተቀብለው ስላስተናገዱኝ  ምስጋናዬን ከልቤ አቀርባልሁ። ያች አገር በቅርቡ የዛሬ ዐሥር ዓመታት አከባቢ በጣም ማደግ የጀመርች አገር ስትሆን በምሥራቅና በምዕራብ መካከል በመሆን በርካታ ሕዝባዊ እና በርካታ ሐይማኖታዊ ሁኔታዎችን የምታስተናግድ “ደሴት” ሆናለች፣ ስለዚህ የመሰባሰብ ባህልን ለማስፋፋት ተስማሚ የሆነች አገር ነች። ይህ ጉብኝት እንዲሳካ ለካቶሊክ ማህበረሰብ የሚሆን ዝግጅት በማዘጋጀት ከፍተኛ አስተዋጾ ላደርጉት፣ በእዚያች አገር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የክርስትናን እምነት እንዲወዱ ጥረት ያደርጉ የደቡባዊው የአረብ አገሮች የቅድስት መንበር ሐዋሪያዊ ጉዳዮች ጸሐፊ ለሆኑት ለክቡር አቡነ ፖል ሂንደር ምስጋናዬን አቀረባለሁ።

በአቡዳቢ በነበረኝ ቆይታ ከግብፅ የአልዓዛር ኢማም ከሆኑት ከሼክ አልጣይብ ጋር ሰብዓዊ ወንድማማችነትን በተመለከተ፣ ሁሉም የሰው ልጆች ወንድማማቾች እና እህተማማቾች መሆናቸውን ስያረጋግጡ ብቻ ነው የእግዚኣብሔር ልጆች መሆን የሚችሉት የሚል ጭብጥ ያዘለ የመግባቢያ ሰነድ ፈርመናል። በዚህም የመግባቢያ ሰንድ ማነኛውንም ዓይነት ሁከት፣ በተለይም ደግሞ በሐይማኖት የተነሳ የሚደርጉ ግጭቶችን በመቃወም በአንጻሩ ደግም እውነተኛ የሆኑ እሴቶቻችንን በማጉላት ለሰላም ግንባታ ጥረት ማደርግ እንደ ሚገባን ተወያይተናል። ይህ የመግባቢያ ሰነድ በተለያዩ አገራት ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቬርሲቲዎች ውስጥ በትምህርት መልክ እንዲሰጥ ተግባብተናል። እናንተም ብትሆኑ ይህንን ሰነድ እንድታነቡት፣ በሚጋባ እንድታውቁት እና በሕይወታችሁ ውስጥ እንድትጠቀሙበት አደራ እላለሁ።

በተባበሩት የአረብ ኤምሬትስ ውስጥ ከአንድ ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ክርስትያኖች የሚገኙ ሲሆን እነዚህም ከተለያዩ የኤሺያ አገራት የተውጣጡ በአገሪቷ በመሥራት ላይ የሚገኙ ሰዎች ናቸው። በዚያም ለእነርሱ መስዋዕተ ቅዳሴ አድርጌላቸው ነበር። በጣም ደስ የሚል አጋጣሚ ነበር።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝት እግዚኣብሔር ያሳካው “ያልተጠበቀ” ሐዋርያዊ ጉዞ ነበር። በዚህም ምክንያት ለእርሱን እና ለእርሱ መንፈሳዊ ጥበቃ ምስጋና ማቅረብ የሚገባ ሲሆን ምክንያቱም የተዘራው ዘር በእርሱ ቅዱስ ፈቃድ ምክንያት ፍሬያማ የሆን ዘንድ መጸለይ ይገባል።

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ
06 February 2019, 14:32