ፈልግ

በአባ ኤርኔስቶ በአባ ኤርኔስቶ  

የዛሬ 35 አመት ገደማ በአባ ኤርኔስቶ የክህነት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እቀባ ተነሳ።

የዛሬ 35 አመት ገደማ የኒካራጓ አገር ተወላጅ በሆኑት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህን በአባ ኤርኔስቶ ካርዲናል የክህነት አገልግሎታቸውን በይፋ እንዳያከናውኑ ለባለፉት በርካታ አመታት ተጥሎባቸው የነበረው ክልከላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ማንሳታቸው ተገለጸ።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በአባ ኤርኔስቶ ካርዲናል ላይ የዛሬ 35 አመታት ገደማ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቀኖናን በሚጣረዝ መልኩ በወቅቱ በኒካራጓ በነበረው ኮሚኒስታዊ መንግሥት ውስጥ እርሳቸው እና ሌሎች የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህነት የነበሩ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ተቀጥረው በመሥራታቸው ምክንያት ሕገ ቀኖናዊ በሆነ መልኩ ክህነታዊ አገልግሎታቸውን በይፋ ማከናወን እንዳይችሉ እቀባ ወይም ክልከላ ተደርጎባቸው እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን ይህ ሕገ ቀኖናዊ የሆነ ክልከላ የተበየነባቸው ደግሞ እ.አ.አ 1984 ዓ.ም በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ  እንደ ነበረ ይታወሳል።

አባ ኤርኔስቶ ካርዲናል በወቅቱ የኒካራጓ ኮሚኒስታዊ ሥርዓት መሪ በነበሩ በዳኒኤል ሆርቴጋ አማካይነት የአገሪቷ የባሕል ሚንስትር ሆነው መመረጣቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህም ምክንያት ለባለፉት 35 አመታት ያህል በክህነት አገልግሎታቸው ላይ ተጥሎ የነበረው ክህነታዊ አገልግሎት ከመስጠት የሚያግዳቸው ክልከላ በአሁኑ ወቅት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መነሳቱ የተገለጸ ሲሆን እ.አ.አ 1984 ዓ.ም በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ “በቤተ ክርስቲያን ወዋቅር ውስጥ እንጂ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ለመሥራት የክህነት አገልግሎትህ አይፈቅድልህም፣ ስለዚህ ተመልሰህ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያለህን ግንኙነት አድስ” ብለው መልእክት ካስተላለፉ በኋላ በወቅቱ ይህ ጥያቄያቸው ተግቢ የሆነ ምላሽ ባለመግኘቱ የተነሳ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቀኖና በቁጥር 285 ላይ የተጠቀሰውን እና ማነኛውም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህን መንግሥታዊ በሆኑ ተቋማት ውስጥ ተቀጥሮ ከመሥራት የሚያግደውን የሕገ ቀኖና ክፍል በመጥቀስ ክህነታዊ አገልግሎታቸውን በይፋ እንዳይሰጡ ክልከላ አድርገውባቸው እንደ ነበረ ይታወሳል።

21 February 2019, 09:02