ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጉባኤውን አባላት ተቀብለው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጉባኤውን አባላት ተቀብለው 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የሰውን ልጅ ማንነት እና ጥበብ መተካት አይችሉም”።

በሰዎች እና በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል ያለውን ግንኙነት በምንመለከትበት ጊዜ በእርግጥ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሰውን ልጅ ሕይወት በአስገራሚ መልኩ እየቀየሩት እንደሆነ ይስተዋላል ብለው ትክክለኛ አገልግሎትን ወይም እድገትን ለማምጣት ከተፈለገ እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለእያንዳንዱ የሰው ልጅ ጥቅም ብሎም ለጠቅላላ ሰብዓዊ እድገት መዋል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በቅድስት መንበር ጳጳሳዊ የስነ ሕይወት ጥናት አካደሚ፣  ሰዎች፣ ቴክኖሎጂ እና ጤና በሚል ርዕሥ በየካቲት 18 ቀን 2011 ዓ. ም. በቫቲካን ከተማ በሚገኘው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ዓመታዊ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤያቸውን ማካሄዳቸው ታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጉባኤውን አባላት ተቀብለው ባሰሙት ንግግር እንደገለጹት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ለሰው ልጅ የሚያበረክቱት እገዛ መጠን ብዙ ቢሆንም የሰውን ልጅ መተካት አይችሉም ብለዋል።    

ቴክኖሎጂን በሁለት ጎኑ መመልከት እንችላለን ብለው በአንድ ጎኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በእለታዊ ኑሮ መካከል የሚያበረክቱት እገዛ መኖሩ የሚታወቅ ሲሆን፣ በሁለተኛ ጎኑ በሰዎች ላይ የራሳቸውን ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ፣ ጫናንም እንደሚፈጥሩ መዘንጋት የለበትም ብለዋል። መገንዘብ ያለብን የቴክኖሎጂ ውጤቶች በሰው እጅ የተሰሩ፣ በሰዎች የሥራ ውጤቶች እና ችሎታ ላይ ተጨማሪ እገዛን የሚያደርጉ መሆናቸውን ማወቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ሙሉ በሙሉ መመካት አያስፈልግም፣

ባለንበት ዘመን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለሰው ልጅ የሚያበረክቱትን አገልግሎት እና የሚያስወግዱትን ችግሮች ብዙ ቢሆንም፣ አንድን ሥራ በተቀላፈ መልኩ በጥራት ማከናወን መልካም እንደሆነ የተናገኣሩት ቅዱስነታቸው እንዴት ተሠራ ከማለት ይልቅ ማን ሠራው፣ ለማን ተሠራ የሚሉትን ጥያቄዎች መመልከት ያስፈልጋል ብለዋል። በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የመመካት አደገኛነትን የገለጹት ቅዱስነታቸው፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለሰው ልጅ ዕለታዊ አገልግሎት በማለት የሰውን ልጅ የበላይነት አሳልፎ መስጠት ሰብዓዊ ክብርን አሳልፎ ወደ መስጠት ሊያደርስ ይችላል ብለዋል።

የጋራ ዓላማን ማበጀት ይገባል፣

ውዳሴ ላንተ ይሁን የሚለውን ሐዋርያዊ መልዕክታቸውን ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስለ ዘመናዊ የተክኖሎጂ አጠቃቀም አንዳንድ መመሪያዎችን በምናወጣበት ጊዜ እና ጥናት በሚደረግበት ጊዜ ጥንቃቄ ሊደረግበት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። በሰዎች እና በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል ያለውን ግንኙነት በምንመለከትበት ጊዜ በእርግጥ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሰውን ልጅ ሕይወት በአስገራሚ መልኩ እየቀየሩት እንደሆነ ይስተዋላል ብለው ትክክለኛ አገልግሎትን ወይም እድገትን ለማምጣት ከተፈለገ እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለእያንዳንዱ የሰው ልጅ ጥቅም ብሎም ለጠቅላላ ሰብዓዊ እድገት መዋል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሊያስከትሉ የሚችሉት ችግሮች፣

የቴክኖሎጂ ውጤቶች አጠቃቀምን አስመልክተው ባቀረቡት ሃሳባቸው እነዚህ ሰው ሠራሽ አዕምሮ የሚባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ባሁኑ ጊዜ የሰውን ልጅ አእምሮ ለመቆጣጠር የሚያደርጉት አዝማሚያ የተሳሳተ እንደሆነ ገልጸው የሰው ልጅ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተገዥ ከሚሆን ይልቅ በቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ የበላይነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል። ይህን ለማድረግ ከሁሉ አስቀድሞ እውቀት፣ የህሊና ስሜት፣ ስነ ምግባር፣ በራስ መተማመን ያለበት ስነ ምግባራዊ እርምጃዎች ምን ማለት እንደሆኑ መገንዘቡ መሠረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል። 

ሃሳብን ወደ ሌላ አቅጣጫ ማዞር አስፈላጊ አይደለም፣

የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለእያንዳንዱ ሰው ማሕበራዊ ዕድገት ማዋል ከተፈለገ በሰው እና በቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ለይቶ ማወቅ እንደሚያስፈልግ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አሳስበዋል። በማከልም ሁለተኛውን የቫቲካን ጉባኤ ሰነድን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሰውን ልጅ ከማገልገል ይልቅ አስተሳሰብን፣ ሞራላዊ ስነ ምግባርን፣ ሰብዓዊ ባሕርያትንም ጭምር ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲያዘነብሉ በማድረግ በስነ መለኮታዊ አስተሳሰብ፣ በክርስቲያናዊ እምነት እና በስነ ሞራላዊ ስራዎች ላይ ተጽዕኖን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አስረድተው፣ ቴክኖሎጂ በፍጥነት እያደገ ባለበት ዘመናችን በቅድስት መንበር ጳጳሳዊ የስነ ሕይወት ጥናት አካደሚ ተግባር ለሰው ልጅ ሕይወት ቅድሚያን በመስጠት፣ በዘርፉ የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ ላይ ከሚገኙ ምሁራን እና ተመራማሪዎች ጋር መተባበር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
27 February 2019, 15:16