ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ  የግሪክ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ልኡካንን ተቀብለው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የግሪክ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ልኡካንን ተቀብለው  

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ “የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት የልዩነቶች ተገዥ መሆን የለባቸውም”።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሕብረት መጓዝ ማለት እያንዳንዱ በራሱ መንገድ ይጓዛል ማለት ሳይሆን እንደ በወንድማማችነት፣ እግዚአብሔር አንዱን ከሌላው ሳያበላልጥ ለሁሉ ባዘጋጀው ብቸኛ መንገድ በሕብረት መጓዝ ነው ብለዋል። ይህንን ተገንዝበው ተግባር ላይ ካዋሉት ካቶሊኮች እና ኦርቶዶክሶች ከሚያራርቁ ነገሮች ይልቅ አንድ የሚያደርጋቸው የጋራ እሴቶች የሚበልጡ መሆናቸውን ይረዱታል ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትናንት የካቲት 18 ቀን 2011 ዓ. ም. የግሪክ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ልኡካንን ተቀብለው ማነጋጋራቸው ታውቋል። በቫቲካን ከተማ በሚገኘው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የእንግዳ መቀበያ ውስጥ ተቀብለው ላነጋገሯቸው የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ልኡካን ባሰሙት ንግግር በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መካከል ያለው ትብብር እና ውይይት ባስገኙት መልካም ውጤቶች እጅግ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

በሕብረት መጓዝ ማለት እያንዳንዱ በራሱ መንገድ ይጓዛል ማለት ሳይሆን እንደ በወንድማማችነት እግዚአብሔር አንዱን ከሌላው ሳይለይ ለሁሉ ባዘጋጀው ብቸኛ መንገድ በሕብረት መጓዝ ነው ብለዋል። ይህንን ተገንዝበው ተግባር ላይ ካዋሉት ካቶሊኮች እና ኦርቶዶክሶች ከሚያራርቁ ነገሮች ይልቅ አንድ የሚያደርጋቸው የጋራ እሴቶች የሚበልጡ መሆናቸውን ይረዱታል ብለዋል።

በሁለቱ ቤተክርስቲያኖች መካከል ከ15 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን ጠንካራ ትብብር ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባሕል ነክ የሆኑ ፕሮጀክቶችን እና የስልጠና ዕድሎችን በማመቻቸት ያካሄዱት እንቅስቃሴዎች መልካም ውጤት በማስገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ይህ ተጨባጭ ምሳሌ በሕብረት በመሥራት ወንድማማችነታችንን በድጋሚ እንድናውቅ አድርጎናል ብለዋል።

ወጣቶች እኛን የልዩነቶች ተገዥ እንዳንሆን ያስተምሩናል፣ በሕብረት ለመጓዝ ያለንን ፍላጎት በማሳደግ የአንድነት እንቅፋቶችን ማስወገድ እንችላለን ብለዋል። ስለዚህ በሕብረት ለመጓዝ የጀመርነውን መንገድ መቀጠል አለብን፣ እውነተኛ ወንድማማችነታችንን ለማወቅ በጋራ መሥራት ያስፈልጋል ብለው ወንድማማቾች እንደ መሆናችን እግዚአብሔር ለሁላችን ባዘጋጀልን ብቸኛው መንገድ፣ አንዳችን የሌላውን ሸክም በመሸከም ወደ አንድ እግዚአብሔር ዘንድ ለመድረስ በሕብረት መጓዝ ያስፈልጋል አደራ ብለዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙትን እና የተለያየ ባሕልን የሚከተሉ የክርስቲያን ቤተሰቦችን እየፈታተነ የሚገኘውን ፈጣን ለውጦች ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከእነዚህ የክርስቲያን ቤተሰብ ጋር በመሆን የክርስቲያናዊ ጋብቻ ውበትን በማስረዳት፣ በቤተሰብ መካከል ያለው ፍቅር እንዲያድግ እና በየቀኑ እንዲታደስ ማገዝ ይኖርብናል ብለው የቤተሰብ ሕይወትን እንደ ቅዱስ ወንጌል ቃል መሠረት በሰላም እና በደስታ እንዲኖሩ ለማገዝ ተጠርተናል ብለዋል።  

26 February 2019, 16:29