ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በማረሚያ ቤት የሚሰሩ ማረሚያ ቤቶችን የበዣ ስፍራ ሊያደርጉ ይገባል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸኮስ በጥር 30/2011 ዓ.ም በሮም ከተማ ከሚገኘው “ሬጂና ኮሌይ” በመባል ከሚታወቀው ማረሚያ ቤት ለተውጣጡ የማረሚያ ቤት ሥራተኞች ጋር በነበራቸው ቆያት እንደ ገለጹት በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ማረሚያ ቤቶችን ወደ የመበዣ ሥፍራ መቀየር ይችላሉ ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ባለፈው ዓመት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን በሮም ከተማ የሚገኘውን “ሬጂና ኮሌይ” በመባል የሚታወቀውን ማረሚያ ቤት ጎብኝተው እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ በማረሚያው ቤት ውስጥ ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው በእዚያው ማረሚያ ቤት የሚገኙ ሰዎችን ማበረታታታቸው ይታወሳል።

በዚህ ማረሚያ ቤት የሚሰሩ ከ600 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በትላንትናው እለት በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ከቅዱስነታቸው ጋር ተገናኝተው የነበረ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደርጉት ንግግር ማረሚያ ቤቶች “የቅጣት እና የመከራ ቦታዎች” እየሆኑ ቢገኙም ነገር ግን በእዚያ ለሚግኙ ሰዎች “ሰብዓዊ እንክብካቤ ማድረግ” ይገባል ብለዋል።

ከቁስል የማገገሚያ ስፍራ

በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ “ሰራተኞች፣ ጠባቂ ፖሊሶች፣ በማረሚያ ቤት መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች፣ በማረሚያ ቤት ውስጥ ትምህርት የሚሰጡ ሰዎች ወዘተ በማረሚያ ቤት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ልባቸው የቆሰለባቸው ታራሚዎችን ከዚህ የመንፈስ ቁስል እንዲላቀቁ መሥራት ከባድ ቢሆንም የበኩላቸውን ጥረት በማድረግ በማረሚያ ቤት የሚገኙ የሕግ ታራሚዎች የመንፈስ ነጻነት እንዲኖራቸው ለመርዳት የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ እንደ ሚጠበቅባቸው” ገልጸው ማረሚያ ቤቶች የግጭት ስፍራዎች፣ ሕገወጥ የሆኑ ተግባሮች የሚፈጸሙባቸው ሥፍራዎች እና የሰው ልጅ ድክመቶች ብቻ የሚወሩባቸው ቦታዎች ሊሆኑ ግን አይገባም ብለዋል።

በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ ታራሚዎች ድሆች መሆናቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው እነርሱን የሚጎበኛቸው ዘመድ አዝማድ፣ ጥብቅና የሚቆምላቸው ሰው፣ መብታቸውን እንዲያስከብሩ የሚረዱዋቸው ሰዎች እንደ ሌሉ ገልጸው በዚህ የተነሳ ተገለው እና ተረስተው ይገኛሉ፣ ማኅበረሰቡም ቢሆን ስለእነርሱ ሲያስብ ምቾት አይሰማውም፣ እንዲያውም የማኅበርሰቡ ሸክም እንደ ሆኑ አድረገው ይቆጥሩዋቸዋል ብለዋል።

የሥራ ጭንቀት

በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችን በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በማረሚያ ቤት ውስጥ ሆኖ ሥራ መስራት በጣም ቀላል የሚባል ነገር እንዳልሆነ፣ ሥራው በጣም አስጨናቂ እና ውጥረት የሚፈጥር እንደ ሆነ እንደ ሚረዱ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን ጭንቀት ለመቀነስ ይቻል ዘንድ ሙያዊ እና ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ ጭንቀትን መቀነስ በሚችል መልኩ ተግባራችሁን ማከናውን ያስፈልጋል ብለዋል።

ማረሚያ ቤቶችን የደህንነት ስፍራ ማድረግ ይቻላል

በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ከሚሰሩ ሰዎች ጋር በትብብር በመስርታ  ማረሚያ ቤቶችን የደህንነት ስፍራ ማድረግ ይቻላል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህ በብዙዎቹ ዘንድ የቅጣት ቦታ ተደርጎ የሚቆጠረው ማረሚያ ቤት የደህንነት ሥፍራ፣ የትንሳኤ ስፍራ እና የሕይወት ለውጥ ማምጫ ስፍራ ማድረግ እንደ ሚችላ ገልጸው እነዚህን ሁሉ ተግባራት ማከናውን የሚቻለው ግን ታራሚዎች እና በማረሚይ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ሳይቀር በጋራ በእምነት ጎዳና ላይ ሲራመዱ ብቻ ነው ብለዋል።

09 February 2019, 08:56