ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የአረብ ባሕረ ስላጤን አገራት የጎበኙ የመጀመሪያው ር.ሊ.ጳ ናቸው

“ሰብዓዊ ወንድማማችነት” በሚል መሪ ቃል በተባበሩት የአረብ ኤምሬትስ አገር በሆነችው በአቡ ዳቢ በሚካሄደው ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሐይማኖት መሪዎች ስብሰባ ላይ ለመገኘት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 26/2011 ዓ.ም ወደ እዚያው በማቅናት 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን መጀመራቸው ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ በተባበሩ የአረብ ኤምሬትስ አገር በሆነችው በአቡ ዳቢ እያደረጉት የሚገኘው 27ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት “የሰላም መሳርያ አድርገኝ” የሚል መሪ ቃል ያነገበ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደ ሆነ ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እ.አ.አ በ13ኛው ክፍለ ዘመን የዛሬ 8 ምዕተ አመታት በፊት ቅዱስ ፍራንቸስኮስ እና በወቅቱ የገብፅ ሱልጣን የነበሩት ማሊክ አል ካሚል ጋር በጣሊያን በተገናኙበት ወቅት የተጠቀሙበት መሪ ቃል በድጋሚ ለማስታወስ እና አሁንም ቢሆን ከ8 ምዕተ አመታት በኋላም ቢሆን እንኳን ዓለማችን በከፍተኛ ግጭቶች ውስጥ ስለምትገኝ በዚህ በግጭቶች እና በጦርነቶች እየተናጠች በምትገኘው ዓለማችን ሰላም ይሰፍን ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እና መንግሥታት የራሳቸውን አዎንታዊ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ ለማሳሰብ የተመረጠ መሪ ቃል እንደ ሆነ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 26/2011 ዓ.ም በሮም ከተማ ከሚገኘው እና በሊዮናርዶ ዳቪንቺ ስም በተሰየመው ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ተነስተው 4,298 ኪሎ ሜትሮችን በአየር ላይ አቆራርጠው የጣሊያንን፣ የማልታን፣ የግብፅን እና የሳውዲ አረቢያን የአየር በረራ ክልሎች በማቋረጥ እንደ ተለመደው የአየር የበረራ ክልሎቻቸውን በቋረጡባቸው አገራት ውስጥ ለሚገኙ ርዕሳነ ብሔራት እና ሕዝቦች ሰላም እና ብልጽግናን ተመኝተው የስድስት ሰዓት በረራ ካደርጉ በኋላ የተባበሩት አረብ ሄምሬትስ አገር ወደ ሆነችው አቡ ዳቢ መድረሳቸውን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አቡ ዳቢ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊይ በደረሱበት ወቅት የአገሪቷ ንጉሥ የሆኑት ክቡር ሼኪ ሙሃመድ ቢን ዛይድ አል ዛይን ሞቅ ያለ አቀባበል እንዳደርጉላቸው ለመረዳት ተችሉዋል።

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የአረብ ባሕረ ስላጤን አገራት የጎበኙ የመጀመሪያው ር.ሊ.ጳ ናቸው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የእስልምና እመንት ምንጭ የሆነውን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አከባቢ እየጎበኙ የሚገኙ የመጀመሪያው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንደ ሆኑ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በዚያው አከባቢ “ሰብዓዊ ወንድማማችነት” በሚል መሪ ቃል በአቡ ዳቢ ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሐይማኖት መሪዎች ስብሰባ ላይ ከተካፈሉ በኋላ ከአገሪቷ 9,222,000 ሕዝብ መካከል 9.1 % የሆኑት በአዐዝ ሲቀመጥ 1 ሚልዮን የሚሆን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ጋር እንደ ሚገናኙ እና መስዋዕተ ቅዳሴ እንደ ሚያሳርጉ ለቅዱስነታቸው ከወጣው የጉዞ መርዐ ግብር ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው በአቡ ዳቢ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊይ በደረሱበት ወቅት ንጉሥ ሼክ ሙሃመድ ቢን ዛይድ ኣል ዛያን ሞቅ ያለ አቀባበል አድርገውላቸው የነበረ ሲሆን በመቀጠልም ሁለት ሕጻናት ለቅዱስነታቸው የአበባ ጉንጉን ማበርከታቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል።

ቅዱስነታቸው ከዚያም በመቀጠል እርሳቸው በተደጋጋሚ “ጓደኛዬ እና ወንድሜ” በማለት አዘውትረው ከሚጠሩዋቸው የግብፅ የአልዓዛር ታላቁ መስጊድ እና ዩኒቬርሲቲ አስተዳዳሪ ከሆኑት ከታላቁ ኢማም አህመድ አል ጣይብ ጋር መገናኘታቸውን ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል፣ ይህ ግንኙነት ደግሞ በእስልምናው ዓለም ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው እና በአጠቃላይ በክርስትና እና በእስልምና የእመን ተቋማት መካከል ያለው ግንኙነት አዎንታዊ በሆነ መልኩ እየተጠናካረ መሄዱን የሚያሳይ መልካም ገጽታ ነው።

ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአቡ ዳቢ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ የተደርገላቸው ደማቅ አቀባበል በባሕላዊ ሙዝቃዎች የታጀበ እንደ ነበረ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተባበሩት የአረብ ኤምሬትስ የቅድስት መንበር ቋሚ መኖሪያ ቤት ባለመኖሩ ቅዱስነታቸው እና ከእርሳቸው ጋር የነበሩ ልዑካን ሙሽሪፊ ሕንጻ በመባል በሚታወቀው ሕንጻ ውስጥ ወደ ተዘጋጀላቸው ማረፊያ መወሰዳቸው ተገልጹዋል።

03 February 2019, 16:49