ፈልግ

በሮም በሚገኘው በታላቁ ቅድስት ማርያም ባዚሊካ የምስጋና ጸሎት ሲያቀርቡ፣  በሮም በሚገኘው በታላቁ ቅድስት ማርያም ባዚሊካ የምስጋና ጸሎት ሲያቀርቡ፣  

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በአቡ ዳቢ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ወደ ቫቲካን ተመለሱ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከጥር 26 እስከ ጥር 28 ቀን 2011 ዓ. ም. ድረስ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያደረጉትን 27ኛ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ፈጽመው ወደ ሮም መመላሳቸው ታውቋል። ዛሬ ጠዋት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአቡ ዳቢ ከተማ ውስጥ በሚገኘው በዛይድ ስተዲዬም ካሳረጉት የመስዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል ከአቡ ዳቢ ከተማ በሃያ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኝ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ መሄዳቸው ታውቋል።

በአውሮፕላን ጣቢያ ተገኝተው ደማቅ ኣሸኛኘት ያደረጉት ልዑል ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ ናያን ከሌሎች የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን እንደሆነ ታውቋል። በሽኝቱ ስነ ስርዓት ላይ ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን፣ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ፣ ብጹዕ ካርዲናል ሌዎናርዶ ሳንድሪ፣ የምስራቅ አገሮች ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተጠሪ፣ ካርዲናል ፈርናንዶ ፊሎኒ ለሕዝቦች የወንጌል ስርጭት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ፣ ብጹዕ አቡነ ሚጌል አንገል ኣዩሶ፣ በጳጳሳዊ ምክር ቤት የእምነቶች የጋራ ውይይት አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ መገኘርታቸው ታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአየር ጣቢያው ለተገኙት በሙሉ ምስጋናቸውን እና ሰላምታቸውን ማቅረባቸው ታውቋል። ቅዱስነታቸው ከ7 ሰዓት በረራ በኋላ በሮም አቅራቢያ በሚገኘው በቻምፒኖ አውሮጵላን ማረፊያ መድረሳቸው ታውቋል። በመቀጠልም ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ሲፈጽሙ እንደሚያደርጉ ሁሉ የምስጋና ጸሎታቸውን ለማቅረብ፣ በሮም ከተማ ውስጥ ወደ ሚገኘው የቅድስት ድንግል ማርያም ባዚሊካ ወይም ሳንታ ማሪያ ማጆሬ ባዚሊካ ሄደው ጸሎታቸውን ማቅረባቸው ታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጸሎታቸውን ካደረሱ በኋላ በቫቲካን ወደ ሚገኘው መንበራቸው በሰላም መግባታቸውን ከቫቲካን የዜና አገልግሎት የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።      

05 February 2019, 09:21