ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከአቡዳቢ መልስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከአቡዳቢ መልስ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ “የአንድ ክርስቲያን መሣሪያ እምነት እና ፍቅር ነው”!

“ሰብዓዊ ወንድማማችነት” በሚል መሪ ቃል በተባበሩት የአረብ ኤምሬትስ አገር በሆነችው በአቡ ዳቢ ተካሂዶ በነበረው ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሐይማኖት መሪዎች ስብሰባ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ተሳታፊ እንደ ነበሩ የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው የእስልምና እምነት ምንጭ የሆነውን የባሕረ ስላጤ አከባቢ የጎበኙ የመጀመሪያ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመሆናቸው የተነሳ ይህ የቅዱስነታቸው 27ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት ተሪካዊ እንዲሆን አድርጎታል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአቡ ዳቢ በነበራቸው ቆይታ ከተለያዩ የእምነት ተቋማት መሪዎች እና ተወካዮቻቸው ጋር ቆይታ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በተለይም ደግሞ እርሳቸው “ወንድሜ እና ጓደኛዬ” በማለት ከሚጠሩዋቸው የግብፅ ታላቁ የአልዓዛር መስጊድ እና ዩኒቬርሲቲ ኢማም ከሆኑት አህመድ አል ጣይብ ጋር መገናኘታቸው እና በዓለም ዙሪያ ሰላም ይሰፍን ዘንድ የሁለቱ ሐይማኖት ተቋማት ተወካዮች ማለትም የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ምዕመናን በወንድማማችነት መንፈስ በመተጋገዝ እና በመደጋገፍ ይኖሩ ዘንድ የሚያስችላቸው የመግባቢያ የሰላም ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።

የክርስቲያን መሳሪያ እመንት እና ፍቅር ነው!

ቅዱስነታቸው በዚያው በአቡዳቢ ባደርጉት ታሪካዊው 27ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት በአቡዳቢ ከሚገኙ አጠቃላይ 10 ሚልዮን ከሚሆኑ ሕዝቦች ውስጥ 1 ሚልዮን የሚሆኑ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን መካከል 180,000 ሺ የሚሆኑ ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴ ማስረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “የአንድ ክርስቲያን መሳሪያ እመንት እና ፍቅር ነው” ማለታቸውም ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው በአቡዳቢ ያደርጉትን 27ኛውን ታሪካዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠቃለው በትላንትናው እለት ማለትም በጥር 28/2011 ዓ.ም ወደ ቫቲካን በመመለስ ላይ በነበሩበት ወቅት ከእርሳቸው ጋር በአውሮፕላን ይጓዙ ለነበሩ ጋዜጠኞች ይህንን 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተው እንደ ነበረም ለቫቲካን ዜና ከደረሰው ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

የሰላም ስምምነቱ ታሪካዊ ነው

በወቅቱ ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “የግብፅ ታላቁ የአልዓዛር መስጊድ እና ዩኒቬርሲቲ ኢማም ከሆኑት ሼክ አህመድ አል ጣይብ ጋር የተፈራረሙት የሰላም የመግባቢያ ሰንድ ታሪካዊ” መሆኑን ገልጸው “በዚህም ሰብዐዊ ወንድማማችነትን ለማጠናከር የሚያስችል እና ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ሰነድ የተወለደ አዲስ ስምምነት ማድረጋቸው በጣም እንዳስደሰታቸው” ቅዱስነታቸው የገለጹ ሲሆን “ይህ የተፈረመው የሰላም የመግባቢያ ሰነድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ስር መስረታቸውን በሁለተኛው ቫቲካን ጉባሄ ላይ ማድረጋቸውን የሚያሳይ አንድ እርምጃ” እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

ይህ የመግባቢያ ሰነድ የተወለደው ከእምነት ነው

ይህ ቅዱስነታቸው እና የግብፅ ታላቁ የአልዓዛር መስጊድ እና ዩኒቬርሲቲ ኢማም የሆኑት ሼክ አህመድ አል ጣይብ የተፈራረሙት የሰላም መግባቢያ ሰነድ የተዘጋጀው “ከፍተኛ የሆነ አስተንትኖ እና ጸሎት ከተደረገ” በኋላ እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው “ይህ የሰላም መግባቢያ ሰነድ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን በከፍተኛ ሁኔታ በመንጸባረቅ ላይ ያሉ አስከፊ የሆኑትን “ጦርነቶች፣ ውድመቶችን እና የእርስ በእርስ ጥላቻን” ለማስወገድ በማሰብ በጥንቃቄ የተዘጋጀ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። “እኛ አማኝ የሆንን ሰዎች እጅ ለእጅ መጨባበጥ፣ መተቃቀፍ፣ መሳሳም እና አብረን መጸለይ ካልቻልን፣ እምነታችን ተሸናፊ ይሆናል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህም መሰረት ይህ እርሳቸው እና የግብፁ ታላቁ የአልዓዛር መስጊድ እና ዩኒቬርሲቲ ኢማም የሆኑት ሼክ አህመድ አል ጣይብ የተፈራረሙት የሰላም የመግባቢያ ሰነድ “የተወለደው የሁሉም አባት ከሆነውና የሰላም አባት ከሆነው በእግዚአብሔር ላይ ካለን እምነት ነው፣ እርሱም በታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው የአሸባሪዎች ጥቃት ከሆነው ከቃየን የሽብር ዘመቻ ጀምሮ ያሉትን ውድመቶች እና የአሸባሪዎች ጥቃት ያወግዛል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ይህ “ሰብዓዊ ወንድማማችነት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው እና የተፈረመው የሰላም የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በካቶሊክ እምነት እይታ ሲታይ እና ሲገመገም ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ሰነድ አጠቃላይ ይዘት ውጪ በመሆን አንዲት ሴንቲ መትር ያክል እንኳን ወጣ ያለ እንዳልሆነ፣ ነገር ግን በተቃራኒው የሁለተኛውን የቫቲካን ጉባሄ ሰነድ መንፈስ ጠብቆ የተዘጋጀ የመግባቢያ የሰላም ሰነድ እንደ ነበረ” ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። የመግባቢያ ሰነዱ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የተለያዩ ሐሳቦችን ያስነሳ እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው እነርሱም ቢሆኑ በሂደት ላይ እንደ ሆኑ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ጥበብ እና ታማኝነት

የእስልምና እምነት ተከታይ ከሆኑ መሪዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ “ጥበብ እና ታማኝነት” የሚሉትን ሁለት ቃላት ተጠቅመው እንደ ነበረ በመግለጫቸው ወቅት ያስታወሱት ቅዱስነታቸው “የጥበብ እና የታማኝነት መንገድ ሰላምን ለመገንባት ያስችላል” ካሉ በኋላ በአቡ ዳቢ የነበራቸው ቆይታ “እውነተኛ ጥበበኞች በሆኑ ሰዎች መካከል ሆኜ ስለ ተሰማኝ እጅግ በጣም ረክቻለሁ” በማለት ጨምረው ገልጸዋል።

ቬንዙዌላን በተመለከተ

06 February 2019, 14:38