ፈልግ

በዱባይ የሚገኝ የቅድስት ድንግል ማርያም የንግደት ስፍራ በዱባይ የሚገኝ የቅድስት ድንግል ማርያም የንግደት ስፍራ  

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ስለ ምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አጭሩ ታሪክ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የእስልምናን እምነት በስፋት እንደሚከተሉ ሌሎች የአረብ አገሮች፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶችም የክርስትና እምነት መታየት የጀመረው በቅርብ ዘመናት ውስጥ እንደሆነ ይታወቃል፣ አገሩ ከሌሎች አገሮች ጋር ባደረገው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች አማካይነት ወደዚያ አገር በሄዱት የክርስትና እምነት ተከታይ ዲፕሎማቶች፣ እንደዚሁም በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ተሰማርተው በሚገኙ የውጭ አገር ግለሰቦች አማካይነት እንደሆነ ይታወቃል። በዚህ መሠረት በአሁኑ ጊዜ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውስጥ ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ክርስቲያኖች እንደሚገኙ እና እነዚህም የአገሩ ተውላጆች ሳይሆኑ ሙሉ በሙሉ የውጭ አገር ተወላጆች መሆናቸው ታውቋል።       

ከእነዚህ የክርስቲያን ወገኖች መካከል 901 ሺህ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች መሆናቸው ሲታወቅ ይህ ማለት ደግሞ ከጠቅላላ የአገሩ ነዋሪዎች መካከል 9.8 ከመቶ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች መሆናቸው ታውቋል። በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በአንድ የሐዋርያዊ አስተዳደር ስር የተዋቀረች ስትሆን 1 ጳጳስ፣ 8 ቁምስናዎች፣ 15 ሐዋርያዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ 11 የሀገረ ስብከት ካህናት፣ 57 የማሕበር ካህናት፣ በድምሩ 68 ካህናት፣ 1 ቋሚ ዲያቆን፣ 1 የገዳማዊያን ማሕበር አባል፣ 43 ደናግል፣ 1,535 የትምህርተ ክርስቶስ መምህራን፣ 3 የከፍተኛ ዘርዓ ክህነት ተማሪዎች፣ 27 የትምህርት ተቋማት፣ በእነዚህ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ 20,883 ተማሪዎች እና በተለያዩ ማሕበራዊ ችግሮች ውስጥ ለወደቁት የእርዳታ አገልግሎቶችን የሚሰጡ 6 ማዕከላት እንደሚገኙባት ታውቋል።

03 February 2019, 09:24