ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለጥር ወር 2011 ዓ.ም ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየወሩ ለወሩ የሚሆን የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ መልእክት ይፋ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህም መሰረት በጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር መሰረት በቅርቡ ለተጀመረው ለጥር ወር ቅዱስነታቸው ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ “ወጣቶች እና የማርያም አብነት” የተሰኘው የጸሎት ሐሳብ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው በዛሬው እለት ማለትም በታኅሳስ 30/2011 ዓ.ም በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ይፋ ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
የዚህ ዘገባ አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ወጣቶች ለደስታቸው ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን እና ተነሳሽነት እንዲኖራቸው የሚረዷቸውን የመነሻ ሐሳብ ምንጭ የሆነውን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን አብነት መከተል እንደ ሚችሉ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ቅዱስነታቸው መግለጻቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅርቡ ከጥር 15-19/2011 ዓ.ም “እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል በፓናማ የሚከበረው 34ኛውን ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን ከግምት ባስገባው መልኩ ቅዱስነታቸው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ጨምረው እንደ ገለጹት፣ በዚህ በፓናማ በሚከበረው 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ከማርያም ጋር በጋራ በመሆን የክርስቶስን ምስጢር ማሰላሰል እንደ ሚገባ ገልጸው በዚያ ከጥር 15-19/2011 ዓ.ም “እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል በፓናማ በሚከበረው 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ሰላም በዓለማችን ላይ ይሰፍን ዘንድ እያንዳንዱ ሰው በአፍ መፍቻ ቋንቋው የመቁጠሪያ ጸሎት እንደ ሚደገም መግለጻቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
“በዚህ አጋጣሚ በዓለማችን ውስጥ ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ ለሰላም ግንባታ ጠንክረን መሥራት የገባናል” በማለት ቅዱስነታቸው ለዚህ ለጥር ወር 2011 ዓ.ም የሚሆን የጸሎት ሐሳብ ያፋ ባደረጉበት ወቅት ጨምረው መግለጻቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
 

09 January 2019, 08:43