ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 27 ሕጻናትን በቫቲካን ባጠመቁበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 27 ሕጻናትን በቫቲካን ባጠመቁበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ወላጆች ለልጆቻቸው እምነትን ማስተማር እና ማውረስ ይኖርባቸዋል” አሉ።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በምትከተለው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በትላንትናው እለት ማለትም በጥር 05/2011 ዓ.ም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ የተጠመቀበት የጥምቀት በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። ይህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት በተደርገ የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ተከብሮ ማለፉን ለመርዳት የተቻለ ሲሆን በወቅቱ በተደርገው የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ 27 ሕጻናትን ማጥመቃቸውን ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኋ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

በምስጢረ ጥምቀት ስነ-ስረዓት መግቢያ ላይ “ለልጆቻችሁ ምን ትጠይቃላችሁ?” ተብሎ ለቀረበላችሁ ጥያቄ ሁላችሁም በጋራ “እምነት” ብላችሁ መልሳችኋል። እናንተ ቤተክርስቲያን ለልጆቻችሁ እምነት እንድትሰጥ ጠይቃችኋል፣ እናም ዛሬ የእመነት ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን እያንዳንዳችሁ በልቦናችው እና በነፍሳችሁ ውስጥ ይህንን የእምነት ስጦታ ትቀበላላችሁ። ነገር ግን ይህ እመነት ማደግ ይኖርበታል። ምን አልባት አንድ ሰው አዎን አዎን ይህ ጉዳይ ጥናት ያስፈልገዋል ብሎ ሊመልስ ይችል ይሆናል። እውነት ነው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በምንማርበት ወቅት ስለእምነት ምንነት በሚገባ እንማራለን። ነገር ግን ይህንን የተምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ልጆቻችሁ ከመውሰዳቸው በፊት ስለእምነት ከእናንተ ሊማሩ ይገባል፣ ይህም የወላጆች ኃላፊነ ነው። ዛሬ እናንተ ወላጆች የምትወስዱት ኃላፊነት ይህ ነው፣ እምነትን ለልጆቻችሁ ማስተላለፍ እንዳለባችሁ በሚገባ መረዳት ይኖርባችኋል። ይህንን የምታደርጉት ደግሞ በቤታችሁ ውስጥ ነው። ምክንያቱም እምነት ሁልጊዜም ቢሆን ግልጽ በሆነ መልኩ “በእናት ቋንቋ”፣ በቤተሰብ ቋንቋ፣ በቤታችን ቋንቋ፣ የቤታችንን አጠቃላይ ሁኔታ ከግምት ባስገባ መልኩ ሊተላለፍ ይገባዋል።
ይህ የእናንተ ተግባር ነው - እምነትን ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ በሕይወት በመግለጽ፣ በተጨማሪም በቃላት፣ በመስቀል ምልክት ማማተብ እንዴት እንደ ሆነ ለልጆቻችሁ በማስተማር ማስተለፍ ይኖርባችኋል። ይህ በጣም አስፈልጊ የሆነ ጉዳይ ነው። እስቲ ለአንድ አፍታ ተመልከቱ፡ የመስቀል ምልክት በማድረግ ማማተብ የማይችሉ ሕጻናት እንዳሉ አሁን መመልከት ትችላላችሁ። “እስቲ የመስቀል ምልክት በማድረግ አማትብ” ብለን አንድ ሕጻን እዚሁ ብንጠይቅ፣ ምን አልባት ምን ማለት እንደ ሆነ መረዳት የሚያዳግት ምልክት ሊያሳዩን ይችላሉ። በዚህም ምክንያት በቅድሚያ ወላጆች ለሕጻናት ማድረግ የሚጠበቅባቸው ነገር “የመስቀል ምልክት በማድረግ” ማማተብ ይችሉ ዘንድ ልጆቻቸውን ማስተማር መሆን ይኖርበታል።
ነገር ግን ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆነ ነገር እምነትን በሕይወታችሁ መግለጽ ነው፣ ሕጻናት በባለትዳሮች መካከል ያለውን ፍቅር ማየት ይፈልጋሉ፣ ሕጻናት በቤት ውስጥ ሰላም እንዳለ ማየት ይፈልጋሉ፣ ሕጻናት ኢየሱስ በዚያ ቤት ውስጥ እንዳለ ማየት የፈልጋሉ። በዚህ አጋጣሚ አንድ ነገር እንድመክራችሁ ፍቀዱልኝ፣ ይህንን በመናገሬ ይቅርታ አድታደርጉልኝ በቅድሚያ ጠይቃለሁኝ- እባካችሁን በፍጹም በሕጻናት ፊት ሆናችሁ አትጋጩ/አትከራከሩ። በትዳር ውስጥ መከራከር ወይም መጋጨት ያለ ነገር ቢሆንም፣ ነገር ግን ይህንን በፍጹም በሕጻናት ፊት ሆናችሁ አታድርጉት፣ ለብቻችሁ ስትሆኑ ወይም ሕጻናት በሌሉበት ቦታ ሆናችሁ አድርጉት። አንድ ልጅ ወላጆቹ ሲጨቃጨቁ ሲመለከት የሚደርስበትን ሥቃይ ከፍተኛ ነው። እምነታችን በተግባር ለማስተላፈ የሚረዳን ምክር ልለግሳችሁ። መጨቃጨቅ በጥም መጥፎ የሆነ ነገር ነው አይደል? ይሁንና መጨቃጨቅ መጥፎ ነገር ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን ያለ እና የሚኖር ጉዳይ ነው። ነገር ግን ስንጨቃጨቅ ሕጻናት እንዳይጨንቁ፣ እንዳይደነግጡ ንትርካችሁን ሕጻናት እንዳያዩት ማድረግ ግን ይኖርባችኋል።
ይህንን ካልን በኋላ አሁን ደግሞ የምስጢረ ጥምቀት አስጣጥ ስነ-ስረዓታችንን እንጀምራለን፣ አንድ ነገር በጭቅላታችሁ ውስጥ ማኖር ይኖርባችኋል፣ እምነትን ማስተላለፍ የእናንተ የወላጆች ተግባር ነው። ይህንንም ማድረግ የምትጀምሩት በቤታችሁ ውስጥ ነው፣ ምክንያቱም ስለእምነት የምንማረው በቤታችን ውስጥ ነው፣ ስለእመንት በትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የምንማረው ከዚያን ቀጥሎ ነው፣ ከሁሉም በላይ ስለእመነት የምንማረው በቤታችን ውስጥ ነው። ስለዚህ እምነታችሁን ማስተላለፍ የእራሳችሁ ተግባር መሆኑን በጥልቀት በመገንዘብ በዚህ ሐሳብ ወደ ምስጢረ ጥምቀት አሰጣጥ ስነ-ስረዓት እንሄዳለን።

 

14 January 2019, 14:23