ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ኢየሱስ የሰው ዘርን ሁሉ ይባርካል” ማለታቸው ተገለጸ።

“እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም” (ዘህልቍ 6፡22-26)

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የዓለማችን የማኅበረሰብ ክፍሎች ዘንድ 2018 ዓ.ም ተጠናቆ የ2019 ዓ.ም አዲስ አመት በታኅሳስ 23/2011 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል። በተመሳሳይ መልኩም በዚሁ በጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር የ2019 ዓ.ም የአዲስ አመት መጀመሪያ ላይ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ከአዲስ አመት በዓል ባሻገር ስለ እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ከተደነገጉ አራት የእምነት እውነቶች መካከል በቀዳሚነት የሚገኘው እና እ.አ.አ በ250 ዓ.ም አከባቢ ላይ የተደነገገው “እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ናት” በመባል የሚከበረው አመታዊ በዓል በታኅሳስ 23/2011 ዓ.ም በታላቅ መንፈሳዊነት ተክብሮ ማለፉ ይታወሳል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ይህንን በዓል ለመታደም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኝዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ በተነበቡት የመጽሐፍ ቅድስ ምንባባት ላይ መሰረቱን ባደረገ አስተንትኖ እንደ ገለጹት “ኢየሱስ ለእያንዳንዳችን እና ለመላው የሰው ዘር ቡራኬውን ይሰጣል” ብለዋል።
ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉትን አስተንትኖ የጀመሩት ማርያም ሕጻኑን ኢየሱስን በእቅፋ ይዛ የምያሳየውን ምስል በመግለጽ ሲሆን ወደ ዓለም የመጣው ኢየሱስ በእናቱ እቅፍ ውስጥ ሆኖ በማርያም አማካይነት ቡራኬውን ይሰጠናል ብለዋል። በዚህም ምክንያት ማርያም የእያንዳዳችንን የሕይወት ጉዞ በዚህ ዛሬ በተጀመረው አዲስ አመት በማርያም እንደ ሚባረክ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም ቡራኬ የሚለካው ደግሞ እያንዳዳችን መልካም ነገርን ይዞልን ወደ ምድር የመጣው ሕጻኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ያመጣልንን መልካም ነገሮችን በምንቀበልበት ልክ ተስፍሮ የሚሰጠን እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠል በእለቱ በተነበበው የመጀመርያ ምንባብ ውስጥ የተጠቀሰውና በጥንት ዘመን እስራኤላዊያን የሚጠቀሙበትን “እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም” (ዘህልቍ 6፡22-26) የሚለውን የቡራኬ ቃል በመጥቀስ እንደ ገለጹት በዚህ በአሁኑ ወቅት የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የዓለማችን ማኅበርሰቦች ዘንድ ዛሬ በተጀመረው አዲስ አመት የምንገናኛቸውን ሰዎች ሁሉ ተመሳሳይ ቃል በመጠቀም እግዚኣብሔር ይባርካቸው ዘንድ ልንጸልይላቸው የገባል ብለዋል።
የእግዚኣብሔር ፊት
እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ የሚለው ቃል በወቅቱ የነበሩት ካህናት እግዚኣብሔር ምሕረቱን እና ሰላሙን ለሕዝቡ እንዲሰጥ እና እንዲያወርድ የሚማጸኑበት ጸሎት እንደ ሆነ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው የእግዚአብሔር ፊት የእርሱን ክብር የሚገልጽ በመሆኑ የተነሳ ይህንን ታላቅ የሆነ የእግዚኣብሔር ክብር አይቶ በሕይወት ለመኖር የሚችል ማንም ሰው እንደ ሌለ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ነገር ግን አሉ ቅዱስነታቸው ሐሳባቸውን በሚገባ ለማስረዳት በማሰብ “ነገር ግን የእግዚኣብሔር ክብር በፍቅር የተሞላ” እንደ ሆነ ገልጸው እያንዳንዱ ሰው በሕይወት ሂደት ውስጥ በንጹዕ ልብ የሚጓዝ ከሆን ልያገኘው የሚችለው ጸጋ እንደ ሆነ ገልጸው የእግዚኣብሔር በፍቅር የሚገለጽ ክብር ሕይወታችንን እንደ ምያበራ፣ የፍቅር ጸጋ እንደ ሚሰጥ፣ በሁሉም ፍጡራን በተለይም ደግሞ በእርሱ ሀምሳል በተፈጠሩ ሰዎች ፊት ላይ የሚያበራ በፍቅር የሚገለጽ ክብር እንድ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።
ዓለማቀፍ የሰላም ቀን
በወቅቱ በታኅሳስ 23/2011 ዓ.ም ማለት ነው ከተከበረው የጎርጎሮሳዊያኑ 2019 ዓ.ም አዲስ አመት እና በተመሳሳይ መልኩ ማርያም የአምላክ እናት መሆኑዋ የሚገልጸው አመታዊ በዓል ጋር ተያይዞ 54ኛው ዓለማቀፍ የሰላም ቀን እይተከበረ መሆኑን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይህ 54ኛ ዓለማቀፍ የሰላም ቀን “መልካም ፖሌቲካ ለሰላም” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ እንደ ሚገኝ አስታውሰው ማንኛውም ፖለቲካ ሰብአዊ መብቶችን የሚያከብር እና የሚያስከብር፣ የዜጎችን ስብዕና የሚገነባ፣ ወጣቶችን የሚያበረታታ ከሆነ ፖለቲካ የበጎ አድራጎት እና ለሰላም ግንባታ አገልግሎት የሚውል ድንቅ መሳርያ ይሆናል ማለት ነው” ማለታቸውም ተገልጹዋል።


 

01 January 2019, 17:49