ፈልግ

የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በዓል የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በዓል 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “እግዚአብሔር ራሱን ለመግለጥ ወደ ዓለም ከፍታ ላይ አልወጣም”።

“የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው ያለው?” ብለው ኢየሱስ የተወለደበትን ሥፍራ ለማወቅ የፈለጉት ሰብዓ ሰገሎች ኢየሱስን ያገኙት እነርሱ በጠበቁበት በኢየሩስሌም በሚገኘው ቤተ መንግሥት ውስጥ ሳይሆን በቤተልሔም በሚገኝ በአንድ አነስተኛ መኖሪያ ውስጥ ነው

ኢየሱስን ለማግኘት ያለን ብቸኛው አማራች ፍቅር የሆነውን የእርሱን መንገድ መያዝ እንደሆነ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትናንት እሁድ ታሕሳስ 28 ቀን 2011 ዓ. ም. የጎርጎሮሳዊያኑን የዘመን አቆጣጠር በምትከተል ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተከበረው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ክብረ በዓል ለማከበር በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ባሰሙት ስብከታቸው ገልጸዋል። የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት የሚከበርው እግዚአብሔር ራሱን የገለጠው የዓለምን ሕዝብ ለሚወክሉት ለሰብዓ ሰገል እንደሆነም አስረድተዋል። እርሱ ወደ ዓለም የመጣው ለአህዛብ በሙሉ ብርሃን በመሆን ነው ብለዋል።

እግዚአብሔር ራሱን ያስተዋወቀው በሃያላን ሰዎች በኩል አይደለም፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በስብከታቸው አማካይነት፣ እግዚአብሔር ራሱን ለዓለም እንዴት እንደገለጸ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰውን በማብራራት እንዳስረዱት፣ “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው ያለው?” ብለው ኢየሱስ የተወለደበትን ሥፍራ  የፈለጉት ሰብዓ ሰገሎች ያገኙትም እነርሱ በጠበቁበት በኢየሩስሌም በሚገኘው ቤተ መንግሥት ውስጥ ሳይሆን በቤተልሔም በሚገኝ በአንድ አነስተኛ መኖሪያ ውስጥ እንደሆነ አስረድተዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ማናቸውም የአገሩ ሃያላን፣ ንጉሥ በከብቶች በረት ውስጥ ይወለዳል ብለው አላሰቡም። በዚህ ሁኔታ ተውልዶ ካደገ በኋላም ኢየሱስ ክርስቶስ በአጥማቂው ዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ በወደደ ጊዜ ራሱን ከታላላቅ ሰዎች እይታ በማግለል ነበር። የመረጠውም ቤተመንግሥትን ሳይሆን ዝቅተኛ ስፍራን፣ ሃብታም ወይም ታዋቂ ሰዎችን በማሕበረሰቡ መካከል ዝቅተኛ ስፍራ የነበራቸውን ሰዎች መርጧል።

ነብዩ ኢሳይያስ፥ “ተነስና ብርሃንን ልበስ”፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ስብከታቸውን በመቀጠል እንዳስገነዘቡት የእግዚአብሔር ብርሃን በላያቸው የሚበራላቸው፣ ብርሃኑን ለመቀበል ፈቃደኛ በሆኑት ሰዎች ላይ ነው ብለዋል። መጀመሪያ ላይ በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፣ የእግዚአብሔርን ብርሃን ለመልበስ ራሳችንን እንድናዘጋጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ይጋብዘናል ብለዋል። በመሆኑም ይህን ብርሃን ለመልበስ የሚያግዱንን እንቅፋቶች ለመሻገር ራሳችንን እንድናዘጋጅ አሳስበዋል። አያይዘውም ኢየሱስ ክርስቶስ የዘወትር ከለላችን እስከሚሆነን ድረስ ብርሃን የሆነውን እግዚአብሔር መልበስ ያስፈልጋል ብለው፣ የብርሃንን ያህል የቀለለ እግዚአብሔርን ከመልበሳችን በፊት በላያችን ላይ ያለውን ካባድና ወፍራም የሆኑ የሐጢአትና የእንቅፋት ልብሶቻችንን አውልቀን መጣል ያስፈልጋል ብለዋል።      

06 January 2019, 16:06