ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፦ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶችን አመሰገኑ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፦ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶችን አመሰገኑ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፦ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶችን አመሰገኑ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቀደም ሲል ያስነበብናችሁን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ለወጣቶች ባደርጉት የመሰናበቻ ንግግር እንደ ገለጹት “በዚህ ዝግጅት ማብቂያ ላይ በእነዚህ ቀናት እርስ በርስ ለመገናኘት እና ሐሳብ ለመለዋወጥ በመብቃቴ እና በዚህ የዓለም ወጣቶች ቀን ላይ ዳግም ለመሳተፍ በመቻሌ እጅግ በጣም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ” በማለት የምስጋና ንግግር ለወጣቶቹ ማቀረባቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

“በተለይም ደግሞ ለየት ባለ ሁኔታ የፓናማ ርዕሰ ብሔር የሆኑትን ሁዋን ካሎስን ጨምሮ በዚህ የወጣቶች  ቀን ላይ በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ ያደርጉ የተለያዩ አገራት መሪዎችን፣ የፖለቲካ እና የሲቪክ ማኅበረሰቡን፣ በወጣቶች ቀን ላይ ተሳታፊ የሆኑ የተለያየ ድርሻ የነበራቸውን ተቋማት እና ግለሰቦችን ይህ የወጣቶች ቀን በተሳካ መልኩ እንዲካሄድ ላባረከቱት አስተዋጾ ቅዱስነታቸው ምስጋና ማቅረባቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በቅርቡ በፍልጲንስ በሚገኘው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል ላይ በአሸባሪዎች በተቃጣው ጥቃጣው የቦንብ ጥቃት ማዘናቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው በአደጋው 20 ያህል ሰዎች ውድ የሆነ ንፍሳቸውን መነጠቃቸውን የገለጹ ሲሆን አደጋውን አውግዘው በዚህ አደጋ ነፍሳቸውን ያጡ ሰዎችን በጸሎታቸው እንደ ሚያስታውሱ የገለጹት ቅዱስነታቸው በምንም መስፈርት ቢሆን የሰው ልጆችን ነፍስ አደጋ ላይ የሚጥል ጥቃት አስፈላጊ እንዳልሆነ ጠቅሰው የተቃጣውን ጥቃት በድጋሚ ማወገዛቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፦ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶችን አመሰገኑ
28 January 2019, 13:51