ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሳንታ ማሪያ ማጆሬ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሳንታ ማሪያ ማጆሬ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በፓናማ ሲያደርጉት የነበረውን ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው ተመለሱ

ከጥር 14-19/2011 ዓ.ም “እነሆኝ  የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተገኙበት በፓናማ ሲካሄድ የቆየው 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በጥር 19/2011 ዓ.ም በሰላም መጠናቀቁ ይታወቃል። በዚህ 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ተገኝተው ሐዋርያዊ ጉብኝት በማደርግ ላይ የነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 20/2011 ዓ.ም እኩለ ቀን አከባቢ ላይ ወደ ሮም መመለሳቸው ታውቁዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እንደ ተለመደው ቅዱስነታቸው ማንኛውንም ሐዋሪያዊ ጉብኝት ከመጀመራቸው በፊት እና ማነኛውንም ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሮም በሚመለሱበት ወቅት በሮም ከተማ እንብርት ላይ በሚገኘው በማሪያም ስም ከተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በአውሮፓ አህጉር በትልቅነቱ እና በጥንታዊነቱ በሚታወቀው ሳንታ ማሪያ ማጆሬ በመባል በሚታወቀው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተገኝተው፣ በዚያው በሳናታ ማርያ ማጆሬ ባዚሊካ ውስጥ በሚገኘው ባላቲን ቋንቋ “Salus Populi Romani” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም የሮም ከተማ ሕዝቦች አዳኝ ወይም ጠባቂ በመባል የሚታወቀው እና በአብዛኞቹ  የሮም ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሕጻኑን ኢየሱስን በእጆቹዋ ላይ አቅፋ መያዙዋን የሚያሳየው ምስል ስር በመገኘት የምስጋና ጸሎት ማቀረባቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በተለይም ደግሞ ይህ 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በታቀደው መሰረት በሰላም በመጠናቀቁ የተነሳ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ለማርያም  ምስጋና ማቅረባቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

29 January 2019, 13:55