ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የመካከለኛው አሜሪካ ቤተ ክርስትያን ደም ውስጥ ቅዱስ ኦስካር ሮሜሮ ይገኛል

ከጥር 14-19/2011 ዓ.ም እነሆኝ   የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በፓናማ በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች እየተከበረ እንደ ሆነ መግለጻችን ይታወሳል። ይህንን 34ኛውን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት በማድረግ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፓናማ ሐዋርያዊ ጉብኝት እያደርጉ መሆናቸውም ይታወቃል።

የዚህ ዘገባ አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን   

በዚህም መሰረት ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወጣው የጉዞ መረዐግብር መሰረት በትላንትናው እለት ማለትም ሐሙስ ጥር 16/2011 ዓ.ም ቅዱስነታቸው በፓናማ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተገኝተው የፓናማ ርዕሰ ብሔር ዩዋን ካርሎስ፣ የተለያዩ የአገሪቷ ባለስልጣናት፣ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች እና ከሲቪል ማኅበራት የተውጣቱ ተወካዮች በተገኙበት በፓናም ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተግኝተው የአገሪቷ ርዕሰ ብሔር ካደርጉት ንግግር በመቀጠል ቅዱስነታቸው ንግግር ማድረጋቸውን ለቫቲካን ዜና ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

ከዚያ በመቀጠል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከተለያዩ ከመካከለኛው አሜሪካ ከተውጣጡ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዓን ጳጳሳት ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ቤተ ክርስቲያኒቷን በሚመለክቱ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉትንን ንግግር የጀመሩት ከራስቸው ቀደም ብለው ንግግር ካደርጉት “የሳልቫዶር ሊቃነ ጳጳሳት ሆሴ ሉዊስ በሁሉም ጳጳሳት ስም ሆነው ላቀረቡት የእንኳን ደህና መጣህ መልእክት አስመሰግናለሁ” በማለት እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ከአንተ ጋር ለመሆን በመቻሌ እና የእናንተን ተስፋዎችን፣ እቅዶች እና ህልሞች በመካፈል ጌታ የእርሱን ቅዱስ ሕዝብ እንድትንከባከቡ በአደራ ያስረከባችሁ እረኞች ከሆናችሁ ከእናንተ ጋር በመገናኜቴ ከፍተኛ ደስታ ተስምቶኛል” በማልት ንግግራቸውን ጀምረው ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራነችስኮስ በወቅቱ ለብጹዕን ጳጳሳቱ ያደረጉት ንግግር ለቤተ ክርስቲያን ማሰብ ያስፈልጋል በሚል ዐብይ አርእስት ስር “እውቅና እና ምስጋና መስጠት፣ በሰዎች የሚወደድ ጳጳሳት መሆን አላባችሁ፣ ልባችሁ እና ነፍሳችሁ በቤተ ክርስቲያን አስተሳሰብ መሞላት ይኖርበታ፣ የክርስቶስ እርጋታ እንዲኖራችሁ ያስፈልጋል” በሚሉ ጭብጦች ዙሪያ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለስ ሲሆን በክፍል ሁለት ዐብይ አርእስት ሥር ደግሞ በአሁኑ ወቅት በተለይም ደግሞ “በወጣቱ ትውልድ ዘንድ በዓለም ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንሰራፋ የመጣውን የዓለማዊነት መንፈስ እንዴት መዋጋት እንደ ሚቻል” በተመለከተ ስፋ ያለ ንግግር ማድረጋቸውን ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም በጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2019 ዓ.ም “ሁላችሁም የአንድ አካል ክፍሎች ናችሁ” (ኤፌ. 4፡25) በሚል መሪ ቃል እና “ከማህበራዊ የመገናኛ መረብ ማኅበርሰብ ወደ ሰብዓዊ ማኅበረሰብ”  በሚል ጭብጥ ዙሪያ ለሚከበረው 53ኛው ዓለማቀፍ የብዙዐን መገናኛ ቀን መሪ ቃል ጭብጥ ዙሪያ ትኩረት ያደርገ ንግግር ማድረጋቸውም ተገልጹዋል።

በቤተ ክርስቲያን አስተሳሰብ መሞላት ይኖርባችኋል

“በቤተ ክርስቲያን አስተሳሰብ መሞላት ያስፈልጋል” የሚለው አስተሳሰብ የሳልቫዶር ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት እና ለማኅበራዊ ፍትህ መስፈን በመታገላቸው የተነሳ መስዋዕተ ቅዳሴ በማሳረግ ላይ በነበሩበት ወቅት በጥይት ተመተው የተገደሎት ሰማዕቱ ቅዱስ ኦስካር ሮሜሮ የጵጵስና ማዕረግ በተቀበሉበት ወቅት እርሳቸው መርጠውት የነበረ የጵጵስናቸው ዘመን አርማ እንደ ነበረ በማስታወስ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን ቀጥለዋል። “ብዙ ወንዶችና ሴቶች፣ ቀሳውስት እና ደናግላን፣ ገዳማዊያን እና ገዳማዊያት፣ መንፈሳዊ ጉዞ ለመከተል የመረጡ ሰዎች እና ምዕመናን ቤተ ክርስቲያን ፍትህ ይሰፍን ዘንድ የምታደርገው ጥረት በመደገፍ፣ ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀምን በማውገዝ ነቢያዊ የሆነ ድምጽ በማሰማት እና ተልዕኮዋን ለማስቀጠል በማሰብ ደማቸውን እስከ ማፍሰስ እና ሕይወታቸውን እስከ መገበር ደርሰው ነበር”  ያሉት ቅዱስነታቸውየቤተ ክርስቲያን እረኞች የሆኑት ብጽዕን ጳጳሳት ወቅታዊ የሆኑ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ በመመልከት ተመጣጣኝ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ እንደ ሚኖርባቸው” አስታውሰው ቤተ ክርስቲያን እብሪተኛ እና በኩራት የተወጠረች ሳትሆን የቅዱስ ሮሜሮን አብነት በመከተል ቤተ ክርስቲያን ትሁት እና ድሃ መሆን እንደ ሚኖርባት ቅዱስነታቸው አሳስበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚሁ በፓናማ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በፓናማ በማድረግ ላይ በሚገኙት ሐዋሪያዊ ጉብኝት ወቅት ከመካከለኛው አሜሪካ ከተውጣጡ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ግራ በተገናኙበት ወቅት ያደርጉት ንግግር በቀጥታ ብጹዕን ጳጳሳቱን የሚመለከት ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን መላውን የእግዚኣብሔር ሕዝብ ያማከለ ንግግር እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

የመካከለኛው አሜሪካ ቤተ ክርስትያን ደም ውስጥ ቅ. ኦስካር ሮሜሮ ይገኛል

“የመካከለኛው አሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ደም ውስጥ ቅ. ኦስካር ሮሜሮ ይገኛሉ” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ደግማ ለመላው ቤተ ክርስቲያን እና ለብጹዕን ጳጳሳት እርሱ "የማያቋርጥ የመነሻ ምንጭ" ነው ያሉት ቅዱስነታቸው በዚህም ምክንያት "ራሱን ለመጉዳት፣ ራሱን አሳልፎ ለመስጠት፣ የምሕረት ሥራዎች ሕያው ይሆኑ ዘንድ ራሱን በመንፈሳዊነት ያደከመ፣ ያለ እረፍት የሠራ፣ ተግባሩን ‘እንደ ምጽዋዕት’ ሳይሆን እንደ ‘ጥሪ’ አድርጎ የተቀበለውን የቅዱስ ኦስካር ሮሜሮን አብነት መከተል” ይኖርብናል ብለዋል።

ከቤተ ክርስቲያን ስሜት ጋር አንድ መሆን

ከቤተ ክርስቲያን ጋር የነበረው ግንኙነት "አስፈሪ በሚባሉ ጊዜያት እንኳን ሳይቀር የሕይወት አቅጣጫውን ሳይቀይር ሕይወቱን በታማኝነት አሳልፎ የሰጠ፣ አስገራሚ በሆነ መልኩ በየዕለቱ ይሰጠው በነበረው አገልግሎት አማካይነት ራሱን ለሰመስዋዕትነት አቅርቦ የነበረውን፣ የሰማዕቱን የቅዱስ ሮሜሮ አስካርን አብነት በዛሬው ዘመን የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ልትከተለው የሚጋባት የሕይወት አቅጣጫ እንደ ሆነ” ቅዱስነታቸው ገልጸው “የቅዱስ ሮሜሮን አብነት መከተል ማለት ራሳችንን ለቅድስና መክፈት ማለት እና በደማችን ውስጥ የሚገኘውን የነቢይነት ተልዕኮ በድጋሚ እንዲያስነስራራ ማድረግ ማለት ነው” ብለዋል።

የሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ሰንድ ክርስቶስን ለመከተል እርግጠኛ የሆነ መንገድ ነው

“አንድ ሰማዕት የሆነ ሰው መለኮታዊ ጸጋን እና ታላላቅ ነገሮችን ለእግዚአብሔር ክብር ለማምጣት የሠራ፣ ወይም ደግሞ ሕይወቱን የማይወድ ሰው አመለካከት፣ ወይም የሕይወትን ዋጋ ለይቶ የማያውቅ ሰው ማለት ሳይሆን ነገር ግን ሰማዕት የሆነ ሰው ምስጋናውን በሕይወቱ ‘ለመግለጥ እና ለመተርጎም’ የሚያስችል ችሎታ ያለው ሰው ማለት እንደ ሆነ” በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሳልቫዶር ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ሰማዕቱ ቅዱስ ሮሜሮ “እመነት እንዲኖረው ያደርገችውን እና የረዳቺውን ቤተ ክርስቲያኑን እጅግ በጣም ይወድ ነበር፣ የእርሷ አንድ አካል እና አባል እንደ ሆነ ሆኖ ይሰማው ነበር፣ ይህንንም ያደርገው የሁለተኛውን የቫቲካን ጉባሄ አስተምህሮዎች እና ታድሶዎች በመቀበል ነበር” ብለዋል።

ትሁት እና ደሀ የሆነች ቤተ ቤተ ክርስቲያን

“ክርስቶስ እኛን የሰው ልጆችን ለመምሰል በማሰብ ራሱን አገልጋይ እና ድሃ አድርጎ ወደ እዚህ ምድር በመምጣቱ የተነሳ ቤተ ክርስቲያን ይህንን የክርስቶስ አብነት በመከተል ራሱናን ትሁት እና ድሃ ማድረግ እንደ ሚጠበቅባት” የተናገሩት ቅዱስነታቸው “በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክርስቶስ በመካከላችን ስለሚኖር በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያን ትሁት እና ድሃ መሆን እንጂ በትዕቢት እና በኩራት የተሞላችን ቤተ ክርስቲያን መመስረት እንደ ማይገባ” ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ሕይወታቸው ከቆሰሉ ሰዎች ጋር መሆን

“በታሪክ ውስጥ እንደ እንደ ተመለከትነው እግዚኣብሔር የእያንዳንዱን ሰው ሕይወት እንደ ሚያድን ተመልክተናል” የሚለውን የሰማዕቱ የቅዱስ ኦስካር ስብከተ በአብነት በመጥቀስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያን “በተለያዩ ምክንያቶች ሕይወታቸው ከቆሰሉ ሰዎች ጋር በመሆን በሕይወት ጉዞዋቸው ውስጥ ያጋጠማቸውን መንፈሳዊ እና አካላዊ የሆኑ ቁስሎችን ለመፈወስ ጥረት ማድረግ እንደ ሚገባት” ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከመካከለኛው አሜርካ ለተውጣጡ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ባደርጉት ንግግር ጨምረው ገልጸዋል።

ወጣቶች በነዋይ እየተማረኩ በእየ ጎዳናው ላይ ፈሰው ይጋኛሉ

25 January 2019, 15:37