ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ወደ ፓናማ ጉዞ በጀመሩበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ወደ ፓናማ ጉዞ በጀመሩበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በፓናማ በሚካሄደው 34ኛው የወጣቶች ቀን ላይ ለመሳተፍ ወደ እዚያው አቀኑ።

ከጥር 14-19/2011 ዓ.ም “እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን በፓናማ እንደ ሚከበር ይታወቃል።

ከጥር 14-19/2011 ዓ.ም “እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን በፓናማ እንደ ሚከበር ይታወቃል። በዚህ በፓናማ በሚካሄደው 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከጥር 15-19/2011 ዓ.ም በዚያ እንደሚገኙ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህ መሰረት ለቅዱስነታቸው ከወጣው የጉዞ መረሃ ግብር ለመረዳት እንደተቻለው ቅዱስነታቸው ረቡዕ ጥር 15/2011 ዓ.ም በሮም ከተማ ከሚገኘው እና በሌዮናርዶ ዳቪንቺ ስም ከተሰየመው ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ተነስተው 9500 ኪሎ ሜትሮችን በአየር ላይ አቋርጠው 12 ሰዓት ከ55 ደቂቃ የሚወስድ በረራ አድርገው የጣሊያን፣ የፈረንሳይ፣ የስፔን፣ የፖርቱጋል፣ የሳንታ ማሪያ ደሴት፣ የአሜሪካ ውቅያኖሶችን፣ ፖርታሪኮ፣ የዶሜኒካን ሪፖብሊክ፣ አንቲሌ ኦልናደሲ ደሴት ኮሎምቢያን የአየር ክልል አቁርጠው በፓናማ በሚገኘው ቶኩሜን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚደርሱ በቅድስት መንበር የህትመት እና የዜና ክፍል ካወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከጥር 15-19/2011 ዓ.ም እነሆኝ   የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል በፓናማ የሚካሄደው 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን የወጣው የጉዞ መርሃ ግብር፥   

ሐሙስ ጥር 16/2011 ዓ.ም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፓናማ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት በመገኘት ከሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር እና ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ይገናኛሉ። ከዚያ በመቀጠል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከተለያዩ ከመካከለኛው አሜሪካ ከተውጣጡ ብጹዓን ጳጳሳት ጋር ይገናኛሉ።

ዐርብ ጥር 17/2011 ዓ.ም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፓናማ የሚገኘውን የወጣቶች መዕከል ይጎበኛሉ፣ በዚያ የሚካሄደው የሚስጢረ ንስሐ ስነ-ስረዓት ላይ ይሳተፋሉ። በተመሳሳይ ቀን ከሰዓት በኋላ ላይ ወጣቶች በፓናማ ከተማ በሚያደርጉት የወጣቶች የመስቀል መንገድ ጸሎት ላይ ቅዱስነታቸው እንደሚሳተፉ ከወጣው የጉዞ መረሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።

ቅዳሜ ጥር 18/2011 ዓ.ም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፓናማ ከተማ በሚገኘው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባዚሊካ ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴን ያሳርጋሉ። ከመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት በመቀጠል ቅዱስነታቸው ከወጣቶች ጋር የምሳ ግብዣ ይቋደሳሉ። አመሻሹ ላይ ቅዱስነታቸው ወጣቶች ባዘጋጁት የዋዜማ የጸሎት ፕሮግራም ላይ ይገኛሉ፣ ከወጣቶች ጋር በጋራ ጸሎት ያደርሳሉ።

እሁድ ጥር 19/2011 ዓ.ም

Photogallery

በፓናማ የሚካሄደው 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን በጥር 14/2021 ዓ.ም በይፋ ተጀመረ
23 January 2019, 15:57