ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የፍልስጤምን ፕሬዚደንት መሐሙድ አባስን በቫቲካን ተቀብለው ባነጋገሯቸው ወቅት፣ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የፍልስጤምን ፕሬዚደንት መሐሙድ አባስን በቫቲካን ተቀብለው ባነጋገሯቸው ወቅት፣ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የተጀመረው የሰላም ጥረት እንዲቀጥል አሳሰቡ

በቅድስት መንበርና በፍልስጤም መካከል ያለው ግንኙነት አስደሳች እንደሆነና በፍልስጤም የሚገኙ ክርስቲያኖች እንዲሁም መላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለፍልስጤም ሕዝብ የምታቀርበው ሐዋሪያዊና ማሕበራዊ አገልግሎቶች አዎንታዊ ይዘት እንዳላቸው አስታውሰው ይህም በሁለቱ መንግሥታት መካከል በ2007 ዓ. ም. የተደረገው ዓለም አቀፍ ስምምነት ውጤት እንደሆነ አስታውሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትናንት ህዳር 25 ቀን 2011 ዓ. ም. የፍልስጤምን ፕሬዚደንት መሐሙድ አባስን በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸው ታውቋል። ክቡር ፕሬዚደንት መሐሙድ አባስ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ ከተገናኙ በኋላ በቅድስት መንበር የመንግሥታት ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ከብጹዕ አቡነ ፖል ጋላገር ጋርም መገናኘታቸው ታውቋል።

በቅድስት መንበርና በፍልስጤም መካከል ያለው ግንኙነት መልካም እንደሆነ አስታውሰው በፍልስጤም የሚገኙ ክርስቲያኖች እንዲሁም  መላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለፍልስጤም ሕዝብ የምታቀርበው ሐዋሪያዊና ማሕበራዊ አገልግሎቶች አዎንታዊ ይዘት እንዳላቸው አስታውሰው ይህም በሁለቱ መንግሥታት መካከል በ2007 ዓ. ም. የተደረገው ዓለም አቀፍ ስምምነት ውጤት እንደሆነ አስታውሰዋል። አክለውም በፍልስጤምና በእስራኤል መካከል ተጀምሮ ባለው የእርቅ ጎዳና ላይ በቅድሚያ በፍልስጤም ሕዝብ መካከል ሰላምና እርቅ መውረድ ይስፈልጋል ብለው፣ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከከል የተጀመረው የሰላምና የእርቅ ውይይትም መልካም ውጤት እንዲያስገኝ ሁለት ራስ ገዝ መንግሥታት በሚለው ሃሳብ፣ ሁለቱ መንግሥታት ስምምነት ላይ እንዲደርሱ የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የጀመረውን የእርቅ መንገድ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሃሳባቸውን ተለዋውጠዋል።

የኢየሩሳሌምን የይገባኛል ጥያቄ በተመለከተ፣ የቅድስት ከተማ ኢየሩሳለም ማንነትና ዓለም አቀፋዊ እሴትነቷ በትክክል መቀመጥና መታወቅ እጅግ አስፈላጊ፣ ትኩረትም ሊሰጠው እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ የኢየሩሳሌም ከተማ በእምነታቸው ውስጥ የእምነት አባት ለሆነው ለአብርሐም ትልቅ ቦታን ለሚሰጡትና በሚገባ ለሚያውቁት ለሦስቱ ሐይማኖቶች ለክርስትና፣ ለእስልምናና የአይሁድ እምነቶች ታላቅ እሴት እንደሆነች ገልጸዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከፍልስጤም ፕሬዚደንት ከሆኑት ከክቡር መሐሙድ አባስ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ውስጥ የሚታዩን ሌሎች ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አስቸኳይ የሰላምና የውይይት ጥረቶችን ማድረግ እንደሚያስፈልና ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የሐይማኖት ወገኖች የጽንፈኝነትንና የአክራሪነትን ባሕርይ አስወግደው ለሰላም ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽዖን እንዲያበረክቱ አደራ ብለዋል።       

04 December 2018, 16:46