ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “ሕይወታችን ሊገነባ የሚገባው በክርስቶስ ዓለት ላይ ብቻ ነው”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዛሬው እለት ማለትም በኅዳር 27/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በእለቱ ከማቴዎስ ወንጌል 7:24-27 ላይ ተወስዶ በተነበበው “ቃሌን ሰምቶ በተግባር ላይ የሚያውለው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል” በሚለው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ባደርገው ስብከታቸው መናገር እና ማድረግ፣ አሸዋ እና ዓለት የተሰኙትን ቃላት በንጽጽር በመጠቀም እንደ ግለጹት “ሕይወታችን ሊገነባ የሚገባው በክርስቶስ ዓለት ላይ ብቻ ነው” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው በእለቱ የገለጹትን ሐሳባቸውን ለማጠናከር በማሰብ በትላንትናው እለት (በኅዳር 26/2011 ዓ.ም) ከትንቢተ ኢሳያስ 25፡6-10 ላይ እና በመቀጠልም ከማቴዎስ ወንጌል 15፡29-37 ተወስዶ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተመርኩዘው ሦስት ተነጻጻሪ የሆኑ ቃላትን በመጠቀም እና በማወዳደር ማናገር እና መተግበር፣ አሸዋ እና ዓለት፣ መዋጣት እና መውረድ (ውጣ ወረድ) በሚሉት ቃላት ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ ስብከት ማድረጋቸውን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

መናገር እና መተግበር

የመጀመሪያዎቹ ተነጻጻሪ ቅላት "መናገር እና መተግበር" የሚሉት ቅላት እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው እነዚህ ሁለት ተቃራኒ የሆኑ ቃላት በክርስትና ሕይወት ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ የሚንጸባረቁ እና የሚታዩ ቃላት መሆናቸውን ገልጸው ይህንን ሐሳባቸውን በሚገባ ለማስረጽ በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል፡. . .

በቃላት መናገር ማለት ያመነውን ነገር መግለጽ ማለት ነው፣ ነገር ግን ይህ ጥልቅ ያልሆነ ነገር ነው፣ በጉዞ መሃል ላይ የሚገኝ ነገር ነው፣ እኔ ክርስቲያን እንደሆንኩ እናገራለሁ፣ ነገር ግን አንድ ክርስቲያን ማድረግ የሚገባውን ነገር እየፈጸምኩኝ አይደለም ማለት ነው። እንዲሁ በቀላሉ ለመናገር ክርቲያን ክርስቲያን መሽተት ማለት ነው፣ እንዲያው ዝም ብሎ ለይምሰል መናገር ነው እንጂ የምናግረውን በተግባር ላይ አላውልም ማለት ነው። ኢየሱስ የሚያቀርብልን ሐሳብ ተጨባጭ የሆነ ነገር እንድናደርግ ነው። አንድ ሰው ቀርቦ ምክር ሲጠይቀን ሁሌም ተጨባጭ በሆነ መንገድ መመልስ ይኖርብናል። የምሕረት ተግባራት ተጨባጭ የሆኑ ተግባራት ናቸው።

አሸዋ እና ዓለት

እንዲሁም "አሸዋና አለት" የተሰኙ ቃላት በሁለት ተቃራኒ አቅጣጫዎች የሚገኙ ተቃራኒ የሆኑ ቃላት እንደ ሆኑ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አሸዋ “ጠንካራ የሆነ ነገር አይደለም” ይህም አንድ መሠረት የለሽ የሆነ የክርስትና ሕይወትን የሚያመልክት የንግግር ዘይቤ እንደ ሆነ ገልጸዋል። በተቃራኒው ደግሞ ዓለት የሚለው ቃል ጌታን እንደ ሚያመልክት ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

እርሱ ኃይላችን ነው። ነገር ግን ብዙ ጊዜ በጌታ የሚተማመኑ ሰዎች አይታዩም፣ ስኬታማ አይሆኑም፣ ተደብቀው ይኖራሉ ነገር ግን እነርሱ ጠንካራ የሆነ መሰረት አላቸው። ተስፋቸው የተመሰረተው በመናገር፣ በእብርት፣ በኩራት፣ በሕይወት ጉዞዋቸው ውስጥ ስልጣንን በመፈለግ አይደለም። ዓለታቸው ክርስቶስ ነው። የክርስትና ሕይወት በእርጋታ ወደ ፊት በመሄድ መሰረታቸውን ዓለት በሆነው በእግዚኣብሔር ላይ በመገንባት መልኮታዊ የሆነ ጥንካሬ እንድናገኝ ይረዳናል። የታይታ ነገሮች ላይ ወይም ዋጋ የለሽ፣ በኩራት የተሞሉ ነገሮች ላይ ሳይሆን ነገር ግን በእውነት ላይ በተመሰረተ መልኩ ሊሆን ይገባል።

ውጣ ውረድ

በሦስተኛ ደረጃ የቀረቡት ተነጻጻሪ ቃላት መውጣት እና መውረድ (ውጣ ውረድ) የተሰኙ ተቃራኒ ቃላት እንደ ሆኑ በስብከታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም የኩራተኞችን እና የእብሪተኞች እርምጃዎች ትሁት ከሆኑ ሰዎች እርማጃዎች ጋር በማነጻጸር የቀረቡ ቃላት መሆናቸውን ገልጸው ይህንንም በእለቱ በቀዳሚነት ከትንቢተ ኢሳያስ 26፡1-6 ላይ ከተጠቀሰው “በከፍታ የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፤ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፥ እስከ መሬትም ድረስ ያዋርዳታል፥ እስከ አፈርም ድረስ ይጥላታል።  እግር፥ የድሀ እግርም የችግረኛም እግር ይረግጣታል” በማለት ኢስያስ በትንቢቱ መናገሩን ገልጸው ይህንን ሐሳባቸውን በሚጋባ ለማብራርት በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል. . .

ይህ የነብዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ ክፍል እምቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፡ ጌታ ትሁታንን ያነሳል፣ በእየእለቱ በደል የሚደርሳብቸውን ሰዎች ከፍ ያደርጋል፣ እብሪተኞችን ግን ያዋርዳቸዋል፣ ሕይወታቸውን በእብሪት ላይ የገነቡ ሰዎችን ያዋርዳቸዋል፣ ኩራተኛ የሆኑ ሰዎች ብዙም አይዘልቁም በማለት ማርያም ከዘመርችው የምስጋና ጸሉት ጋር የሚመሳሰል ነው።

በዚህ በስብከተ ገና ወቅት ራሳችንን መጠየቅ የሚገባን ጥያቄዎች

በዚህ በያዝነው የስብከተ ገና ወቅት ለአስተንትኖ ይሆነን ዘንድ “የእኔ ክርስትና በቃላት ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው ወይ? የሕይወቴን መሰረት የተገነባው በጌታ ዓለት ላይ ነው? ወይስ በዓለም አሸዋ ላይ ነው? እኔ የዋሕ የሆንኩኝ ሰው ነኝ?፣ ሁል ጊዜ ዝቀተኛ የሆነ ስፍራ የምፈልግ ሰው ነኝ? ወይስ እብሪተኛ ኩራተኛ የሆንኩ ሰው ነኝ? የሚሉትን ጥያቄዎች በዚህ በስብከተ ገና ሰሞን በማንሳት ራሳችንን መመርመር እንደ ሚገባን ቅዱስነታቸው ከገለጹ በኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

06 December 2018, 15:26